Thursday, 30 May 2013

“የመሬት ባላባቱ” ሚኒስትር!!



ምስጢሩን ያጋለጠው መሃንዲስ የት ደረሰ?
አቶ አባይ ጸሀዬ በዘመዶቻቸው ስም በርካታ መሬቶች መውስዳቸው፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ባስቀመጡት ሃላፊ አማካይነት በመሬት ንግድ ከፍተኛ ጥቅም ማግኘታቸው፣ ህጋዊ ሰነድና ካርታ ያለው ቁልፍ ቦታ ከባለቤቱ ተነጥቆ ለእርሳቸው ዘመድ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ። በየክልሉ ተመሳሳይ ንቅዘት አለ።
በህዝብና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ለአብነት የተጠቀሱት ንብረታቸው የተወሰደባቸው ሴት ወ/ሮ ጉዳያቸውን የትኛውም ቦታ ሲወስዱ መጀመሪያ ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው፣ በቀጠሮዋቸው ቀን ሲሄዱ ምን ምላሽ እንደማያገኙ ጠቅሰው  ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተጀመረው የምርመራ ስራ ይህንን ይመስላል።
ቀደም ሲል ተጠሪነቱ ለአቶ መለስ የነበረው የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና  ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬን “የመሬት ከበርቴው” የሚል ስም ሰጥተዋቸዋል። ስያሜውም የተሰጣቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ሲነግዱ ስለነበር ነው።
የኮሚሽኑ የጎልጉል ምንጭ እንዳመለከቱት አቶ አባይ ጸሀዬ መሬት ሲነግዱ እንደ ነበር የታወቀው በክፍለ ከተማው በተካሄደ ምርመራ ነው። በክፍለ ከተማው በጠራራ ጸሃይ የግለሰቦችን መሬት ሳይቀር እየቸበቸበ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ በደረሰው ተደጋጋሚ ጥቆማ መሰረት የሚመለከተው መምሪያ መነሻ ጥናት ያዘጋጅና ምርመራው እንዲጀምር ይታዘዛል።
በዚሁ መሰረት የኮሚሽኑ መርማሪዎች ስራቸውን ይጀምራሉ። የኮሚሽኑ ባለሙያዎች  ምርመራ እንደጀመሩ መሬት በህገወጥ መንገድ ሲቸበቸብ እንደነበር ይረዱና ከመሬት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ያሽጋሉ። የመሬት ልኬትም ሆነ ከመሬት ጋር የተያያዘ ስራ እንዳይሰራ ያግዳሉ። በተጨማሪም መሬት እየለኩ ሲሰጡ የነበሩ መሃንዲሶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራው በጥብቅ እንዲካሄድ ይደረጋል።
ክፍለ ከተማው ክልሉን ወደ ገጠር ቀበሌዎች እያሰፋ መሬት ይከልላል። መሬታቸው የተወሰደባቸው ደካማዎችን ቦሌ ክፍለ ከተማ ካሳ ለመውሰድ ሲንከራተቱ ማየት የተለመደ ነው። አራት ዓመት፣ አምስት ዓመት ከዚያም በላይ ካሳ ሳያገኙ የሚመላለሱ ደካሞች አሁን ድረስ አሉ። ባለንብረት ለንብረቱ ካሳ የሚከፍለው አጥቶ ይንከራተታል፤ መሬት የመንግስት እንደሆነ ያወጀው መንግስት በከፍተኛ ባለስልጣኖቹ አማካይነት መሬት አየር በአየር ይቸበችባል። ይህ የአሰራሩ ግድፈት ሲሆን ለአብነት የተጠቆመው ጉዳይ አስከፊነትና የወንጀሉ ርህራሄ አልባነት እዚህ ላይ ጎልቶ ይታያል።
አሳዛኝ የተባለው የምርመራ ውጤት ታሪክ የሚጀምርው እዚህ ላይ ነው። መሃንዲሶች በሙሉ ታስረው ተመረመሩ። ምርመራው በሙሉ ወደ አንድ ሰው ቢያመላክትም ያንን ሰው ደፍሮ የሚናገር ጠፋ። ይህን ጊዜ “ለምን” የሚል ጥያቄ ተነሳ። የመሬት አስተዳደር ሃላፊውና የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጉዳዩ የማይመለከታቸው ተደርጎ መወሰዱ፤  መሬት በህገወጥ ስለመቸብቸቡ በቂ መረጃና ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ፣ መሬታቸውን በግፍ ተነጥቀው ለሌላ ሰው የተሰጠባቸው እንዳሉ ተረጋግጦ ሳለ ካርታ ላይ የሚፈርሙትና ለመሃንዲሶች ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት የመሬት አስተዳደር እንዲታሰሩና እንዲመረመሩ አለመደረጉ በጓሮ ኮሚሽኑ የሚታማበት ጉዳይ ሆነ። “ጥርስ የሌለው አንበሳና የመለስ አሽከር” የሚለው የኮሚሽኑ ስም በስፋት ተነሳ!!
“ለፀረሙስና ኮሚሽን ሌላ ጸረ ሙስና ኮሚሽን” በሚል የክፍለ ከተማው ሰራተኛ የሆኑ ደብዳቤ በመጻፍ ወቀሳ ሰንዝረው ምርመራው በወጉ እንዲከናወን ጥቆማና አስተያየታቸውን ላኩ። አንዳንድ ስማቸውንና ማንነታቸውን የደበቁ ሰዎች ጉዳዩን ለግል ሚዲያና ለመንግስት መገናኛዎች እንደሚያቀብሉ ዛቱ። ማንም ምን ቢል የሚሰማም የሚደነግጥም ጠፋ።
ምርመራ ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ለአብነት የተቀመጠው ዛሬ ህንጻ በብድር ተገነብቶበት ከፍተኛ ኪራይ የሚሰበሰብበት ከመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው አዲሱ ጎዳና ዳር ላይ ያለ አንድ ቦታ ጉዳይ ሲጎተት ሚስጥሩን ገለጠው። የመረጃው ምንጭ እንዳስረዱት ምርመራውን የያዘው ባልደረባቸው እንደነገራቸው ምስጢሩ ሲገለጽ ማመን አቅቶት ነበር።
ለክፍለከተማው የመሬት አስተዳደር ሃላፊ ቅርብ ተጠሪ የሆነው መሃንዲስ ምርመራ ሲካሄድበት “እንግዲያውስ እውነቱ ይህ ነው” በማለት አብራራ። በግፍ የተወሰደው ከላይ የተገለጸው ቦታ የተሰጠው ለአቶ አባይ ጸሃዬ ዘመድ መሆኑን ይፋ አደረገ። መሬቱ የቀድሞው ባለቤቶች ለመሆኑ የሚገልጽ በቂ ማስረጃ እንዳለው ቢታወቅም አለቃው አዲስ የባለቤትነት ማስረጃ ቀደም ሲል እንደነበር ተደርጎ እንዲያዘጋጅ ባዘዘው መሰረት የሰው ንብረት አሳልፎ መስጠቱን አስታወቀ። ይህን ጊዜ ምርመራው ባስቸኳይ ወደ ሌላ መርማሪ እንዲዛወር ተደረገ።
የቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ አቶ መሠረት የአቶ አባይ ጸሃዬ የቅርብ የስጋ ዘመድ ሲሆኑ፣ በእርሳቸው ትዕዛዝና አጽዳቂነት በክፍለ ከተማው በርካታ ቁልፍ ቦታዎች ለዘመድ አዝማድ በሽርክና፣ ለባለ ገንዘብ በሽያጭ እንዲዘዋወሩ መደረጉ በምርመራ እንደታወቀ አስቸኳይ መመሪያ ተላለፈ።
መመሪያው እስረኛው መሃንዲስ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ፣ ምርመራውም እንዲቋረጥ የሚል ነበር። ከፍተኛ የሙስና ወንጀልና የስነምግበር ጉድለት መከሰቱን፣ በግፍ ንብረታቸውን ተቀምተው ባዶ እጃቸውን የቀሩ እንዳሉና፣ በማስፋፊያ ስም ቁልፍ ቦታዎች ከህግ ውጪ መተላለፋቸውን ይፋ ለማድረግ ሰፊ ጊዜ ወስዶ የተሰራው ስራ ሙሉ በሙሉ ይፋ ሳይሆን ተዳፈነ። የተልከሰከሰ የስራ ሪፖርት እንዲቀርብ ተደርጎ ፋይሉ ተዘጋ። ከእስር የተፈታው መሃንዲስም ደብዛ ጠፋ። የአገር ደህንነት ከበርካታ ተመሳሳይ ወንጀሎች ጋር ጉዳዩን እንደያዘው የጎልጉል ዘጋቢ አረጋግጧል።
የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የአቶ አባይ ዘመድ እንኳንስ ሊታሰሩ በእድገት የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ አማካሪ ሆነው አዲስ አበባ አስተዳደር ተመደቡ። ዋና ስራ አሰፈጻሚው የፌደራል ስራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ተሰጣቸው። በአሁኑ ወቅት የከንቲባው አማካሪ የሆኑት የአባይ ጸሃዬ ዘመድ መሬትን አስመልክተው ኪራይ ሰብሳቢነት ስለመስፋፋቱ ክፍለ ከተሞችን ሰብስበው ይሰብካሉ። ስለ ሙስና አደገኛነት በየመድረኩ እንዲያስተምሩ ተደረገ። ድርጊቱ በርካቶችን አስቆጣ። በርካታ የወቀሳ ደብዳቤ ለኮሚሽኑ ጎረፈለት። በአካል ቀርበው ምስክርነት የሰጡና ኮሚሽኑ ሊመሰርት አቅዶት ለነበረው ክስ ምስክር ለመሆን የተስማሙ ደነገጡ።
ጉዳዩ እንዲዳፈን ስለተደረገበት ምክንያት ሲያስረዱ “በየትኛውም ደረጃ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በደህንነት ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና መካከለኛ ደረጃ ሃላፊዎች በግልጽ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸው በመረጃ ቢቀርብም ኮሚሽኑ እርምጃ የማይወስደው ሙስና አንዱ የስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ መንገድ በመሆኑ ነው” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
“ኢህአዴግን እያገለገሉ ያሉ ባለስልጣኖች ህወሃትን በሚገባ መከራከር የማይችሉትና በታዛዥነት እያጎበደዱ ለመኖር የሚገደዱት የገቡበትን የሙስና ማጥ ስለሚያውቁት ከተቃወምን እንታሰራለን” በሚል ፍርሃቻ መሆኑን የኮሚሽኑ ባልደረባ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጭ ተናግረዋል። ባለሙያው አያይዘውም “በአገሪቱ የተንሰራፋው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ከላይ እስከታች ተበለሻሽቷል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
“ባለሥልጣናትን በሙስና ማበስበስ” የስርዓቱ ዋንኛ የማኮሰሻና የማዋረጃ ስልት እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በማጣቀስ “አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ ባቀረብነው ቃለ ምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል። ኢህአዴግ ለትምህርት ውጪ አገር የላከቸውና ስማቸውን ለጊዜው መግለጽ ያልፈለጉት ተናጋሪ “ስርዓቱ በስብሷል” ባይ ናቸው።
“ባለኝ መረጃ መሰረት የኔ ስጋት እነዚህ ያለቀረጥ የሚነግዱ፣ ገንዘብ የሚያቀባብሉ፣ የገንዘብ ዝውውር ላይ የተሰማሩ፣ ድርጅት ያላቸው፣ በቅጽበት ተመንጥቀው ባለሚሊዮኖች የሆኑ፣ የባንክ ብቸኛ ተጠቃሚዎች፣ ሸቃጮችና አወራራጆች ከትንሽ እስከ ትልቅ ስራውን የሚሰሩት ከባለስልጣናት ጋር ነው። ከመከላከያ አመራሮች ጋር ነው። ከደህንነትና ከዋናው የስልጣን እርከን ጋር በመመሳጠርም ነው” በማለት ቃለ ምልልስ አድራጊው በውል የሚያውቁትን ተናግረዋል። አያይዘውም “ስርዓት ሲበሰብስ ልዩ ምልክቱ ትናንሽ መንግስታት ማቆጥቆጣቸው ነው። በኢህአዴግ መበስበስ አቶ መለስን ጨምሮ በርካቶች ይስማማሉ። ኢህአዴግ መዓዛውን አልቀየረም የሚሉት በአገሪቱ ድፍን ቆዳ ላይ የራሳቸውን መንግስት የተከሉ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው። እነሱ ክሬሙን እየላሱ ስለሆነ የመበስበስ አደጋ አይታያቸውም። ስለመበስበስ ለማሰብም ጊዜ የላቸውም። የበሰበሰው ነገር ሲናድ የሚበላው ግን አስቀድሞ እነሱን ነው። ምክንያቱም አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ በጣም ትልቅ ነው” በማለት ፍርሃቻቸውን ይገልጻሉ።
የፌዴራል መንግስት የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና በገለልተኛ ወገን አስጠንቶ ያገኘውና ይፋ የተደረገው ውጤት አስደንጋጭ መሆኑ ይታወሳል። በዚሁ ጥናት መሰረት ፖሊስ፣ ፍርድ ቤቶች፣ አጠቃላይ የፍትህ ተቋማትና ራሱ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀዳሚ ሙስና የተንሰራፋባቸው ተቋማት መሆናቸውን ማረጋገጡ፣ ተቋማቱም በጥናቱ ቅር መሰኘታቸውን በመግለጻቸው በዝርዝር ይቀርባል የተባለው ጥናት እስካሁን ይፋ ሊሆን አለመቻሉም ታውቋል፡፡
የፊታችን አርብ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ አቶ መለስ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለእርቸው ስለሆነ አዲስ በሚያቋቁሙት ካቢኔ ውስጥ መካተት የሌለባቸውን የነቀዙ ባለስልጣናት ለመለየት ፋይላቸውን ከኮሚሽኑ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

አባይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መደበቂያ አይሆንም!


በስዊትዘርላንድ የሚገኙ የሲቪክ ተቋማት፣ የፖለቲካ ሃይሎችና፣ የዴሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች ግብረ ሃይል የጋራ አቋም መግለጫ
በስዊዘርላንድ የምንገኝ የዕምነት ፣ የፖለቲካ እና የሲቪክ ማህበራት በጋራ በመሆን በሃገራችን ኢትዮጵያ እየደረሰ ያለውን አጠቃላይ የመብት ጥሰት እና ሃገርን የማውደም ዘመቻን በጋራ እንታገላለን።  በተለይም በአባይ ግድብ እና በሌሎች ግልጽነት እና ተአማኒነት በሌላቸው ልማቶች ስም የወገን ሃብት እና ንብረት ዘረፋ ይቁም የሚል ጥሪያችንንም እናቀርባለን።
እንደሚታወቀው በሃገራችን ኢትዮጵያ የመብት ጥሰቶች ከግዜ ወደ ግዜ እየተበራከቱ እና እየከፉ መጥተዋል።  ላለፉት 21 ዓመታት ሃገሪቷን በመግዛት ላይ ያለው ህውሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት የሃገሪቱን ህገ-መንግስትም ይሁን ሃገሪቱ የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ውሎችና ስምምነቶች ችላ በማለት በዜጎቹ ላይ ይህ ነው የማይባል የመብት ጥሰት እየፈጸመ ይገኛል።  የህዝቦች መብት እና ነጻነት በቅድምያ ሳይከበር በልማት ስም የሚደረግ ማንኛውም ተግባር ደግሞ ከየትኛውም ወንጀል ሁሉ የከፋ  ወንጀል ነው።  ሃገር ለህዝቦቿ የሰላም ከለላ እና መከታ ስትሆን እንጅ ህዝቦች ሰላማቸውን ፣ እረፍታቸውን ፣ መሸሸግያቸውን የሚነጠቁባት ፣ የሚገፈፉባት ፣ በስጋት እና በጭንቀት የሚኖሩባት ምድር ፈጽሞ መሆን የለባትም።  የሃገር ልማትም ሆነ እድገት ለህዝቦቿ እና ለዜጎቿ እንጂ ከቶም ለማንም ሌላ ፍጡር አይደለም።  መስረታዊ የሆነን የዜጎች መብት እንኳን ሳያከበር እና ሳያስከበር ፤ እጅግ የከፋ በደል በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለ ስርዓት ልማት ይቅደም በሚል ሽንገላ የሚደረግ ምዝበራ ተቀባይነት አይኖረውም።  የዜጎችን ሰብዓዊ-መብቶች ያላገናዘቡ የልማት ተግባራት ግብ እና ዓላማ የአፋኙን ስርዓት ጡንቻ ይበልጥ ለማፈርጠም እንጂ ፈጽሞ ልማት ነው ብሎ ማሰብ አይቻልም።
በልማት ስም የሚተገበረው የኢህአዴግ ፖሊሲ በአንድ በኩል ሃገሪቱን ከማትወጣበት የብድር አረንቋ የሚከት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለተወሰኑ ብሄር ተወላጆች የማያልቅ የሃብት መዛቅያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።  ሃገሪቱ በሙስና ተጨማልቃ ፣ ዜጎች በኑሮ-ውድነት መከራቸውን እያዩ እና የሚላስ የሚቀመስ ባጡበት የኑሮ ሂደት ውስጥ ልማታችን ባለሁለት አሃዝ እድገት አሳየ እየተባለ የሚዘመረው ለፌዝ ካልሆነ እውነት ነው ብሎ ለመቀብል የሚቻል አይደለም።  በእርግጥ ሃገሪቱ ባለፉት ሃያ አመታት ብቻ ከሃምሳ ቢሊየን ዶላር በላይ በእርዳታ እና በብድር ማግኘቷን ስንመለከት ልማቷ አደገች ከሚባልለት አሀዝ በላይ መሆን በቻለ ነበር።  ሆኖም የተወሰኑ የስርዓቱ አቀንቃኞች የግል ኪሳቸውን ሲያደልቡበት የኢትዮጵያ ገበሬ ግን ማዳበርያ እንኳን ለመግዛት በሬውን ሽጦ ወይንም መሬቱን በከፊል በአራጣ አስይዞ ነው።  የሃገራችንን እድገት ለመለካት ውስብስብ ስሌትና ጠመዝማዛ መንገድ መሄድ አያስፈልገንም።  ከረሃቡ ጥናት በሚማሩበት ጠረጴዛ ላይ የሚያንቀላፉ ተማሪዎችን በአንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሄዶ ማየት ይበቃል ከዚህ ሌላ ኑሯቸውን የቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ያደረጉ ቁጥራቸው ይህ ነው ተብሎ የማይገለጽ ከህጻን እስከ አዛውንት ያሉ ዜጎችን እንዲሁም ችግር ከቤታቸው ገፍትሮ በየመንገዱ ለልመና ያጋለጣቸውን አዛውንቶች እና አረጋውያን ማየቱ ለእድገታችን ምስክር ነው።
እንደ ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ሀቀኝነት (Global Financial Integrity) ድርጅት 2011 ዓመታዊ ዘገባ ከሃገሪቷ 11.7  ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከ2000 – 2009  ድረስ በ 10 ዓመታት ግዜ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ከሃገር መሸሹን ሲዘግብ ይህ መቀመጫውን ዋሽንግተን ያደረገው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በ2009 ብቻ 3.26 ቢሊየን ዶላር ከሃገር ኮብሏል ካለ ቡሃላ እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ ሂደቱ ተባብሶ ቀጥሏል ማለቱ ነው።  ይህ ገንዘብ ተጨማሪ ልመና ሳያስፈልገው ሶስት የአባይ ግድቦችን ሊገድብ ይችል ነበር።  ወትሮስ የስርዓቱ ዓላማ መች ልማት ሆነ እና? አባይን በመገደብ ሃገርን የማልማት ፣ ዜጎችንም ከችግር የማውጣት ሳይሆን በልማት ስም የኢትዮጵያን ህዝብ ሃብት እና ንብረት ለመዝረፍ የተጠነሰሰ ሴራ ነውና ህዝባችን ስርዓቱ እያደረገ ያለውን ወንጀል በትክክል ሊያውቀው እና ሀይሉን አስተባብሮ ሊያስቆመውም ይገባል።
ፖለቲካ ሳይሆን ዓላማችን ልማት ነው በሚል ስልታዊ አካሄድ እና ብልጣብልጥ ቋንቋ የስርአቱ ታማኞች እና አገልጋዮች የአባይን ግድብ ቦንድ ለመሸጥ ከላይ ታች ሲሉ ይታያሉ።  ህዝቦች የተረጋጋ እና ሰላማዊ የሆነ ኑሮ መምራት የሚችሉበት ስርዓት ሳይኖር ልማት ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል እነዚህ አካላት ሊገነዘቡት ይገባል።  ቦንድ  ለመሸጥ እንደተሯሯጡት ሁሉ የህዝቦችን በደል ፣ ሃገሪቷ ላይ የነገሰውን ዘረኝነት ፣ ስርዓት አልበኝነት እና ሙስና ይቁም ለሚለው ቅድምያ እንዲሰጡ እንጠይቃቸዋለን።  የዚህ የገንዘብ ማሰባሰብ አንድ አካል መሆን በህዝቦች የመናገር ፣ የመደራጀት ፣ የመጻፍ ፣ የማምለክ ፣ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ በሃገር የመኖርን እና ሃብት የማፍራትን ነጻነት በመግፈፍ ላይ ላለ ስርዓት እገዛ ማድረግ በመሆኑ በታሰሩ እና እየታሰሩ ባሉት ፣ ከሃገር በሚሰደዱ እና በሚገደሉ ኢትዮጵያውያን ላይ በጋራ የግፍ በትር ካነሱት ጋር በቀጥታ መተባበር በመሆኑ ከእንደዚህ አይነት የወንጀል ተሳታፊነት እንዲታቀቡ ለማስገንዘብ እንወዳለን።  ዜጎቹን እያሰቃየ ላለ ስርዓት እድሜ ማራዘምያ እና ፖለቲካዊ ግብአት ለሚደረግ የገንዘብ ማሰባሰብያ ጥረት ተሳታፊ መሆን ታሪክ ተጠያቂ መሆን ነው።
በአባይ ወንዝ ላይ ሃገራችን ኢትዮጵያ ያላትን መብት ማስጠበቅ ፣ አባይንም ይሁን አገሪቱ ያሏትን ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች በተገቢው ጥቅም ላይ በማዋል ህዝቧቿን ከድህነት ለማውጣትና ሃገሪቱን የማልማትና ለማበልጸግ በሚደረግ ጥረት ሁሉም የበኩልን ማበርከት እንዳለበት እናምናለን።  ሆኖም ግን አባይ እንዲገደብላቸው የምንሻላቸው ዜጎች ቅድሚያ በገዛ ሃገራቸው የመኖር ፣ ተዘዋውረው የመስራትና ሀብት የማፍራት ፣ የፖለቲካም ሆነ በሌሎች የህይዎት ዘርፎች በእኩልነት ተሳታፊ የመሆን ፣ የማሰብ እና ሀሳባቸውን በነጻ የመግለጽ ፤ የማምለክ ፣ የማመን ቅርሶቻቸውን የማስጠበቅ እንደዚሁም እምነታቸውን በነጻነት የመተግበር የማስፋፋት መብቶቻቸው በቅድሚያ ሊከበሩላቸው ይገባል።  ዛሬ የእስር-ቤት ቋንቋ ኦሮምኛ በሆነበት ሂደት ኦሮሞ ስለሆኑ ከየዩኒቨርስቲው የሚባረሩ ተማሪዎች ባሉበት ሃገር ፣ አስራ-ስምንት ወራት ድምጻችን ይሰማ በማለት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ለሚያቀርቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ምላሽ የግፍ እስር እና ግድያ በሆነበት ሂደት ፣ ብሄራቸው አማራ ስለሆኑ ብቻ ከየቅያቸው የሚፈናቀሉ ንጹሃን ዜጎችን ማሰቃየት እና ማጉላላት እየተካሄደ ባለበት የዘረ ማጥፋት እና ማጽዳት ሂደት ፣ በአፋር ፣ በቤኒሻንጉል እንዲሁም በጋምቤላ እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ በሙሉ እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት ባለበት ተጨባጭ ሁኔታ ድርሻችን መሆን ያለበት የዜጎች መብት ይከበር የሚለው ቅድምያ ሊሰጠው ይገባል።
ከግብ የሚደርስና ዘላቂነት የሚኖረው ልማት ሁሉን ያካተተ መሆን የሚጠበቅበት ሲሆን ግልጽነትም (transparency) ሊኖረው ይገባል።  ከዚህ አንጻር የአባይ ግድብ ገና ከአጀማመሩ ዓለም ዓቀፍ የጨረታ ስርዓትን (international tendering principles) ያልተከተለ ሆኖ እናገኘዋለን።  ያለጨረታ ኮንትራክት የተሰጠው የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ድርጅት ከዚህ በፊት በጊቤ ቁጥር-2 ስራ ላይ ተሳትፎ ስራዎችን ያበላሸ እና ከፍተኛ ወጪ ያስወጣ ድርጅት ነው።  ይህ ስራ ለእንደዚህ አይነት ድርጅት ሲሰጥ ማየት ዋናውን አላማ ጥያቄ ውስጥ ከማስገባቱ በተጨማሪ አሰራሩ በሙስና የተዘፈቀ መሆኑን እንዳንጠራጠር ያደርገናል።  ቅዲሚያ መከናወን የነበረባቸው የዲፕሎማሲና የቴክኒክ ስራዎች ሳይከናወኑ ወደ ስራ መግባት አንድም አገራችንን ወደ ጦርነት አውድማ ጎትቶ ማስገባት ሲሆን ሁለትም የሀገርን እና የህዝብን ንብረት ፣ ጉልበትና እውቀት ማራከስ ነው።  ከተባለው ዋና ተቋራጭ ድርጅት በተጨማሪ በቁሳቁስ አቅራቢነት የተሰለፉት ከአንድ ብሄር እና ክልል የተወጣጡ እንደ ኤፈርት ያሉ ድርጅቶች መሆናቸው ምን ያህል አድሎ እና ዘረኝነት የነገሰበት ሃገር እንደተመሰረተች የሚያሳይ ግልጽ ሂደት ነው።
በመጨረሻም በልማትም ስም ይሁን በሌላ ዘዴ በመጠቀም ሃገራችን እና ህዝቦቿን ያሏቸውን መልካም እሴቶች ለማጥፋት ፣ በሃይማኖቶች መሃከል ሳይቀር በመግባት ያለንን የህዝቦች ተከባብሮ ፣ ተሳስቦና ተቻችሎ የመኖር ዘይቤን አደጋ ላይ በሚከት መልኩ ስርዓቱ የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በጥንቃቄ እንድንከታተል ፣ ለሃገራችን ሰላም መረጋጋት እና ብሎ ለቀጠናው መረጋጋት ሁላችንም በኢትዮጵያዊነት ወኔ እና ስሜት በአንድነት እንድንነሳ እንጠይቃለን። በመሆኑም በአባይ ስም በሀገር ውስጥ ካለው ምስኪን ሕዝብ ከወር ደመወዙ እንዲቆረጥ የሚደረገውንም ሆነ ከዲያስፖራው የሚሰበስበው ገንዘብ መብቶችን ለማፈን የካድሬዎችን ቁጥር ለመጨመር እና የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ለማፈን በቀጥታ ስለሚጠቀምበት በጋራ እንታገል።
“አባይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መደበቂያ ና የአምባገነኖች እድሜ ማራዘሚያ አይሆንም “!!!
ድል ለኢትዮጵያ!  ድል ለኢትዮጵያዊያን!

Tuesday, 8 January 2013

“የጅብ እርሻ ነገር ሳያድግ በቡቃያው” ከሙሼ ሰሙ (የኢዴፓ ፕሬዚደንት)

 
ከሙሼ ሰሙ (የኢዴፓ ፕሬዚደንት)
በአንድ ወቅት ወደ ሰሜን ሸዋ ለቅስቀሳ ከተላከው የቅንጅት አመራር ቡድን ጋር ተመድቤ ቅስቀሳውን ካጠናቀቅን በኋላ፣ ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር የመወያየት እድል ገጥሞኝ ነበር፡፡ በቅስቀሳው እጅግ ደስተኛ የነበሩት አርሶ አደሮችን ማንን ትመርጣላችሁ ለሚለው ጥያቄ የሰጡኝ መልስ “ቅንጅትን” የሚል ነበር፡፡
ቅንጅትን በመምረጣቸው ቅንጅት መንግስት ከሆነ እንደማያሳፍራቸው አብራርቼ ምስጋናዬን ሳልጨርስ አንዱ አርሶአደር፡- “ይስሙኝ ጌታው-- ለኛ የመንግስት ለውጥ የምንሻው ለውጥ ፍለጋ አይደለም። ለውጥ ከአምላክ ብቻ መሆኑ ከገባን ውሎ አድሯል። ለዚህ ከቅንጅት የምንጠብቀው አንዳችም ለውጥ የለም፡፡ ጉዳያችን ያለው ከወዲህ ነው፡፡ ይሰሙኛል ጌታው” አሉኝ በድጋሚ፡፡ “አሮጌው መንግስት ወድቆ አዲሱ ሲተካ እንኳን ስልጣኑ መሬቱም ፈጥኖ አይረጋለትም፡፡ ታድያ አዲሱ መንግስት ጊዜ ፈጅቶ ርብራቡን አደላድሎ፣ እርካቡን ቆንጥጦ መግረፍ እስኪጀምር እንዲያው ቢያንስ ለሶስት አራት ዓመት ያህል ፋታ ስለምናገኝ ነው፡፡ ምን በላችሁ፣ ምን ጠጣችሁ፣ ድረስ ወጉ አይቀርብንም፡፡ እንዳው በተስፋ እንጠግባለን፡፡ ልጆቻችን በሰላም ቀያቸው ገብተው ይወጣሉ፡፡ ግብሩም አይጎዳንም፡፡ ስራም አንፈታም፡፡ ከብቱም ሰዉም መቅኖ አያጣም” አሉኝ፡፡
በጊዜው ጉዳዩን ያለ አርምሞ በሳቅ በፈገግታ እንደዘበት አልፌዋለሁ፡፡ ስምንት ዓመት መሆኑ ነው እንግዲህ፣ በጊዜ ሂደት ግን አርሶ አደሮቹ ከገሃዱ ዓለም የተማሩት እውነታ ዛሬ ፍንትው ብሎ እየታየ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ሃያ አንድ ዓመት የስልጣን ዘመን በኋላ፣ ዛሬም ስለኑሮ ውድነት፣ ስለትራንስፖርት ችግር፣ ስለመብት ጥሰትና ስለጋዜጠኞች መታፈን፤ በግዳጅ የኢህአዴግ አባል ስለመሆን፣ ስለአስከፊ ሙስናና በስልጣን መባለግ፣ ስለአስተዳደራዊ በደል፤ በአጠቃላይ ስለ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እያሰላሰልን እንድንኖር መገደዳችን የታሪካችን አስከፊ ገጽታ ነው፡፡ ስለመልካም ነገሮቻችን ለመወያየት እንችል ዘንድ ኢህአዴግ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮቻችንን አቅም በፈቀደ ፈትቶ ወይም ለአማራጭ ፖለቲካ ተገቢውን እውቅና ሰጥቶ ቢሆን ኖሮ የፍጥጫ ፖለቲካ ተረት መሆኑ አይቀሬ ነበር። እንዳለመታደል ሆኖ ግን ይህ ሳይሆን ቀረ፡፡ እሱም ሳያንስ ልዩነቶቻችን እንደተጠበቁ ሆነው፣ በዜጎች ገንቢና መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ክፍት የነበሩ ዝንባሌዎች እንዲሁም መልስ በሌለበትም ቢሆን ለመደማመጥ የነበረው እድል ተቀለበሰ፡፡ እንዲያ ባይሆንማ ኖሮ በመልካም ፋይዳዎቻችን ላይ መነጋገር ጭርሱኑ ቀርቶ፣ በችግሮቻችን ላይ ብቻ እንድናተኩር ባልተገደድን ነበር፡፡
ዛሬም በፍጥጫ ፖለቲካ ውስጥ ሆነን ለተቃውሞ ትኩረት የመስጠታችን ምስጢር፣ በኢህአዴግ እንደምንታማው ለተቃውሞ የተለየ ፍቅር ስላለን አይደለም፡፡ መብቶቻችንና ጥቅሞቻችን ከሕገ መንግስት አንቀጽነት ወጥተው በተግባር መረጋገጥ ስላልቻሉና ሃገራዊ ፋይዳችንና አንድነታችን በየእለቱ ፈታኝ ጥያቄ ውስጥ እየገባ በመዳከሩ እንደሆነ ኢህአዴግ ጠንቅቆ እንደሚያውቅ እገነዘባለሁ፡፡
የማያቋርጥ ውትወታችንና የተቃውሟችን ምስጢር ግን ጥያቄዎቻችንና ፍላጎቶቻችን በተግባር አለመሟላታቸው ብቻ አይደለም፡፡ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻችን በቁርጠኝነት መንፈስ ቢጤኑ ያላቸው ሃገራዊ ፋይዳ እየታወቀ፣ በኢህአዴግ በኩል መፍትሔ የማያሻቸው ተራ ነገር ተደርገው መወሰዳቸው ጭምር ነው፡፡ ይህን በቅጡ ለሚያጤን ኢትዮጵያዊ፣ ኢህአዴግ ወደደም ጠላም ቁርጠኝነቱና የአሳታፊነት በሩ ይበልጥ እየሰፋ ሄዶ ወደ ምሉዕነት ካልገሰገሰ፤ የእርግማንና የማጥላላት ፖለቲካው በመቻቻልና እውቅና በመስጠት እንዲሁም በመከባበር እስካልተተካ ድረስ ለሚቀጥሉት በርካታ ዓመታትም ቢሆን የተቃዋሚዎች ታሪክ ድህነትን፣ የኑሮ ውድነትን፣ ስራ አጥነትነትን፣ የመብት ጥሰትንና ማህበራዊ ቀውስን መታገልና ማራገብ ሆኖ እንደሚቀር ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ይህ ደግሞ የገንቢ ፖለቲካ መለኪያም ሆነ መልካም አስተዳደር የሚፈጥረው ትሩፋት መገለጫ እንደማይሆን አምናለሁ፡፡
ለምን ይሄ ይሆናል ? ከሃያ አንድ ዓመት ሕገ መንግስታዊ ስርዓት በኋላ፣ ዛሬም መብቶቻችን ቁልቁል እየተደፈቁና በኢህአዴግ ወቅታዊ ፍላጎት ይሁንታ ልክ እየተሰፈሩ የሚሰጡበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ ዛሬም መጎልመስ ያቃተው በነጻነት የማሰብና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ጥያቄ ከበርካታ መሸራረፍ በኋላ፣ በጸረ ሽብርተኝነት ሕጉ አማካኝነት ቀለበት ውስጥ እንደወደቀ ይገኛል፡፡ የሃገራችን ኢኮኖሚ ልማትን እንጂ ዜጎችን ማማከል ባለመቻሉ ሁላችንንም በእኩልነት ማገልግል ተስኖታል፡፡ ሕገ-መንግስታችን ዜጎች ሁሉ እኩል ናቸው ቢልም በብዙሃኑ ድሃና በሕገ ወጥ መንገድ በከበሩ ጥቂት ሃብታሞች መካከል ያለው የኑሮ ልዩነት ሊቀራረብ በማይችልበት ደረጃ በእጅጉ ተራርቋል፡፡ “ኢኮኖሚያችን በሁለት ዲጅት ቢያድግም” የኑሮ ውድነቱና የገቢ ልዩነታችን ሰማይ ነክቷል፡፡ ሃገር በመዋጮ ይለማ ይመስል፤ ማብቂያ የሌለው የመዋጮ ጥያቄ፣ ከኪስ ብርበራ ባልተናነሰ ሁኔታ እየተፈታተነን ይገኛል፡፡ ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎቻችን ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘታቸው ስለሚጎላ ችግሮቻችንን ከስረ-መሰረቱ መቅረፍ አልቻሉም፡፡ የትራንስፖርት ችግር ጊዜያዊ መፍትሔን በመሻት ላይ ያተኮረ በመሆኑ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ስላልተቻለ ዛሬም ውጣ ውረዱና እንግልቱ ተስፋ አስቆራጭ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ “ቢፒአርና ካይዘን” ወይም ሌሎች መሰል የማኔጅመንት አሰራሮች ተዘረጉ ቢባልም፣ አስተዳደራዊ ፍትሕና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማግኘት ከባድ ዋጋ የሚያስከፈል ፈተና ነው፡፡ ፀረ-ሙስና ቢቋቋምም ሙስና የበርካታ ባለስልጣኖቻችንና ባለሟሎቻቸው የኑሮ መደጎሚያና የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ መስክ ሆኗል፡፡ ጉቦ የኑሮአችን አካል ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ አዲስ ጥሪት መቋጠርም ሆነ ባፈራነው ጥሪት መተማመን ከንቱ ምኞት ነው፡፡ በገንዘባችን የገዛነውና ከዘመናት ጀምሮ ከቤተሰቦቻችን የወረስነው መሬትና የመኖርያ ቤት “ለህዝብ ጥቅም” በሚል ሶሻሊስታዊ መፈክር በሕግ ተነጥቀናል፡፡
ከተሞክሮአችን ስንነሳ፣ ኢህአዴግ ዘመናት ለቆጠሩና ቀስፈው ለያዙን ውስብስብ ችግሮች እራሱን ብቸኛ መፍትሄ ሰጪ ከማድረግ ይልቅ የችግሮቹን ታሪካዊ ዳራ አንጥሮ በማውጣት፣ የችግሩም ሆነ የመፍትሄው ባለቤትነትን የጋራ በማድረግ ልዩነቶችን ማክበርና አማራጮችን መቀበል ቢችል ኖሮ፣ ምንኛ በታደልን ነበር፡፡ እራስን “ሁሉ በኩሉ” አድርጎ በመሳል አማራጭ መፍትሄዎች በተነሱ ቁጥር በተነካሁ ባይነት መንፈስ፣ አላስፈላጊ ትግል ውስጥ መግባት ለውጤትም ሆነ ለለውጥ አያበቃም፡፡ ከውጥረት በሚመነጭ መንፈስ ቁጥር ስፍር የሌላቸውና ምሉዕ ያልሆኑ አቋራጭና ጊዜያዊ መፍትሄዎችን በመደርደር አማራጭ ሃሳቦችን ማጥቃት ለኢህአዴግም ሆነ ለሌላው የሚበጅ አይደለም፡፡ በዜጎች መሐል አላስፈላጊ ውዝግቦችን በመፍጠር ልዩነቶችን እያጎሉ ግጭትን ማካረርም ለልማትና ለእድገት የሚያሻንን ጊዜ ከማባከን ያለፈ ፋዳ የለውም፡፡
ኢህአዴግ ከዚህ ባሕርይው በመነጨም ቀስፈው ለያዙን መሰረታዊ ጥያቄዎች ዛሬም ከሃያ አንድ ዓመታት የስልጣን ዘመን በኋላ የሚሰጠን መልስ “ጥሩ እየሰራን ስለሆነ ተስፋ አድርጉና ታገሱን” የሚል ነው። ከምኞት በመለስ መፍትሄውን መዋጥ የሚተናነቀን ትዕግስታችን ዳቦ፣ ትራንስፖርትና የስራ እድል ሊሆን የሚችልበት ተአምራዊ አጋጣሚ ስለሌለ ብቻ ነው። ለዘመናት የዘለቀው የኢትዮጵያ ችግር በኢህአዴግ ጉልበትና አቅም ብቻ የሚፈታበት ዕድል ቢኖር ኖር መታገሱ ባልከፋ ነበር፡፡ ክፋቱ ግን ይሄ እውን ሊሆን የሚችልበት እድል ፈፅሞ እንደሌለ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ለችግሮቻችን በጋራ መፍትሔ የመሻት ዕድሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጥበቡን ቀጥሏል፡፡ በዚህ ላይ ኢህአዴግ ትዕግስታችን እንዲቀጥል የሚፈልገው ለተጨማሪ አርባና ሃምሳ ዓመታት ወይም ከዛም በላይ መሆኑ ደግሞ ይበልጥ አሳሳቢው ጉዳይ ነው፡፡ በኢህአዴግ “የልማት ጎዳና” ሃያ አንድ ዓመታትን አሳልፈናል፡፡ ይህ እንግዲህ የአንድ ጎረምሳ እድሜ ነው፡፡ በዚህ የኤሊ ጉዞ ውስጥ እየዳህን ስርነቅል ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጥ መጠበቃችን ሳያንስ፣ ሌላ አርባና ሃምሳ ዓመታት ሊጨመርብን መታቀዱ ጭካኔ የተሞላበት በደል ነው፡፡ ለመሆኑ ተስፋ የምናደርገውና አሁንም ኢህአዴግን በተስፋ የምንጠብቀው ለምን ይሆን? ምሬታችን የምር ስላልገባው ወይስ ለአብዮታዊ ዴሞክራሲ የማይተናነቅ መፍትሔ እስኪያገኝ ድረስ? ያለተቀናቃኝ ለዘመናት በስልጣን ላይ መዝለቁ እስኪረጋገጥለት ወይስ አንዳች ተዓምራዊ ሃይል መፍትሄ በራዕይ እስኪያሳየው ድረስ? ይሄንንም በቅጡ ብናውቀው እኮ በጠበቅን ነበር፡፡
ሆኖም ምንም ሳንጨብጥ በባዶ ተስፋ ልንጠብቅ የማንችልበት በርካታ ተጨባጭ ምክንያቶች አሉን፡፡ አልሰማንም እንጂ የኑሮ ውድነቱን መሸከም አቅቶናል፤ የዋጋ ንረቱ መፈናፈኛ አሳጥቶናል፤ ምሳ በልተን እራት መድገም ካቃተን ሰንብተናል እያልን ነው፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎችና ቃል አቀባዮቹ ግን “የምን የኑሮ ውድነት፤ የምን የዋጋ ንረት- ቁርጥ ቤት፣ ክትፎ ቤትና ድራፍት ቤት ተጨናንቆ እያየነው!” ትሉናላችሁ፡፡ የኑሮ ውድነት አለ የሚሉት ጭፍኖች ናቸውም እንባላለን፡፡ እኛ ደግሞ ቁርጥ ቤት፣ ክትፎ ቤትና ውስኪ ቤት የሚያጨናንቁት የናንተ ሙሰኞች እንጂ እኛን አይመለከትንም ባይ ነን፡፡ በአሁኑ ወቅት የሚከፈለን ደሞዝ በአማካይ አንድ ሺሕ አምስት መቶ ብር ነው፡፡ የቤት ኪራይ አንድ ሺህ ብር፤ ምሳ በቀን አርባ ብር፣ በወር አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር ነው፡፡ መዋጮና ቤተሰብን፣ እንዲሁም ለጤናና ለክፉ ቀን የሚቆጠበውን ጨምሩበት፡፡ እንዴት ተደርጎ ይሆን ውስኪና ክትፎ ቤቶትን የምናጨናንቀው? ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ ይሏል ይሄ ነው፡፡
ይህ እንግዲህ ከተማ ውስጥ ያለው ችግር ነው፡፡ ወደ ገጠር ሲገባ ደግሞ የባሰ መሆኑ አሌ አይባልም፡፡ ዛሬም የማይካደው ሐቅ ቢኖር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን አርሶ አደሮች ሕይወት በየዓመቱ በልማት ጀግናነት የሚሸለሙት ጥቂት አርሶ አደሮች እንደማይወክሉት ነው፡፡ በአንጻራዊነትም ቢሆን የተሻለ ደሞዝ ተከፋይ የሆነውን ከተሜ እንኳን የሚያንገዳግደው የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት፣ በአርሶ አደሩ ሕይወት ላይ ምን ያህል አዳጋች ፈተና እንደሚጋርጥበት ለመገመት አንዳችም ፍልስፍና አያሻውም፡፡
የስልጣን ዘመን ባልተገደበበት ሁኔታ በተገደበ አቅምና ዝግጁነት ውስጥ ሆኖ ለዘመናት መዝለቅ የሚሻ መንግስት፤ ዓይነተኛ ስራው በስታቲስቲክ ላይ የሚመሰረት የመረጃ ርብርብና የአዕምሮ ጥቅጠቃ ነው፡፡ የተመዘገበው እድገት የዜጎችን መሰረታዊ ችግር የፈታ ነው ወይ የሚለው ጥያቄ እንዲነሳ አይፈለገም። ዋናው ጉዳይ በስንት ፐርሰንት አድገናል የሚለው ብቻ ነው፡፡ የሚፈጠረው የስራ እድል ዘለቄታዊና አስተማማኝ፤ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የተረጋገጠ ነው ወይ የሚለውም እንዲነሳ የሚሻ የለም፡፡ እድገቱ ኢኮኖሚያዊ ክፍትትን ይሞላል አይሞላም የሚለውም አይፈተሽም፡፡ “ስራ እየሰራሁ ነው” በሚል ተስፋ የተሞላና በምርጫ የሃይል አሰላለፍ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ “ሕዝባዊ መንፈስ” መፈጠሩን ማረጋገጥ ብቻ በቂ ነው፡፡ ኢኮኖሚያዊ ተመላሽ የሌለውና ጊዜያዊ ችግርን የሚቀርፍ መፍትሄ የቱንም ያህል የዜጎችን አቅም ይበርብር እንጂ በመፍትሄነት ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል። ፖሊሲን ለለውጥ አመቻችቶ በመቅረጽ ፖሊሲው በሚፈጥረው የስራ እድል አማካኝነት ተጨማሪ የስራ እድልን የሚፈጥር እቅድን ከመንደፍ ይልቅ ከአንዱ ሃብት ላይ ወይም የእለት ገቢ ላይ ቀንሶ የሌላውን ኑሮ ማካካሻ ማድረግ አማራጭ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ ሁሉ ሳያንስ ሰጭና ከልካይ የሆነ ልማታዊ መንግስት ግዙፍነቱ በሚፈጥርበት ቀርፋፋነት፣ ልክ የሌለው ቀዳዳና ክፍተት እየታገዘ ብክነት፣ ዝርክርክነት፣ ሙስና፣ አልፎ ተርፎ የሃላፊነትና የተጠያቂነት መላላት ሲጨመርበት ጉዞው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ ያኔ በበር የገባ የስምንት ዓመት ልማት በመስኮት መሽሎኩ አያጠራጥርም፡፡
የሕግ የበላይነትና አስተዳደራዊ ፍትሕ ወይም መልካም አስተዳደር በሕገ መንግስቱ ውስጥ የተረጋገጡ መሰረታዊ መብቶች ናቸው፡፡ እነዚህ መብቶች ዜጎች የእርስ በርስ ግንኙነታችንን በሰላማዊ መንገድ መምራት እንድንችል ሁኔታዎችን በማመቻቸት፣ ፍትሕንና መልካም አስተዳደርን በማስፈን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታችንን ማረጋገጥ መቻላቸው አንዱና መሰረታዊ ፋይዳቸው ነው። ከዚህ የሚልቀውና ዓይነተኛ ፋይዳቸው ግን የሕግ የበላይነትና አስተዳደራዊ ፍትሕን በማስፈን፣ የታጠቀ ሃይል የሚያዝ መንግስት ዜጎች ላይ ሊያደርስ ከሚችለው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቃትና ተጽእኖ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ መከላከልና መጠበቅ ነው፡፡
በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር በገፉ ሃገራት ዜጎች የስልጣን ምንጭና የስርዓት ባለቤት ናቸው፡፡ ከዚህ እምነት በመነጨም መንግስት ስልጣን የሚያገኘው በሕግ ለተወሰኑ ዓመታት በውክልና ነው፡፡ በውክልና በሚያገኘው ስልጣን አማካኝነት ለዜጎች፣ ለሃገርና ለስርዓቱ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ ከስርዓቱ ጋር የማይጋጩ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ያቃልላል፡፡ ዜጎችን ከውስጣዊና ውጫዊ ጥቃት ይጠብቃል፡፡ ሉአላዊነታቸውንና ሰላማቸውን ያረጋግጣል፡፡ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ለዜጎች ጥቅም ብቻ ዘብ ይቆማል፡፡
በዲሞክራሲያዊ ጎዳና ብዙ ርቀት ባልሄዱ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ግን የመንግስት ሚና ከዚህ ለየት ያለ ነው፡፡ ዜጎች ባሳለፉት የአፈና ዘመን በተፈጠረባቸው ተጽእኖ ምክንያት መንግስትን፣ ሃገርንና ስርዓትን አደባልቀው ማየታቸው የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ የሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ ፈጣሪ ኢህአዴግ በመሆኑና በሌላ ተቃዋሚ ፓርቲ ሃገሪቱ የመተዳደር እድል ባለማግኘቷ ምክንያት፣ ልዩነቱን ለመረዳት እስከሚያዳግት ድረስ ስርዓት፣ መንግስት፣ ሕዝብና ሃገር የተደበላለቁ ናቸው። በዚህም ምክንያት መንግስት ሲፈተሽ፣ ሲመረመር፣ ሲብጠለጠል፣ ሃገርና ስርዓት ይፈርሳል፤ ብጥብጥ ይነሳል፤ ሁከት ይነግሳል፤ የሚል ስጋት በመንግስታት ዘንድ መነሳቱ የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ስጋቱ ውሎ አድሮ መብትን በቁጠባ ማቃመስን፣ የመብት ጥያቄዎችን በጥርጣሬና በጎሪጥ ማየትን በማስከተል ለፍጹም የመብት ረገጣና አፈና አቀባብሎ መስጠቱ ግልጽ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ ድርጊት ቀስ በቀስ ስር እየሰደደ በመጠናከሩ ሕገ መንግስታዊ የመብት ቁጠባው የመንግስት መብት ይሆኗል፡፡ ቀጥሎም ኢህአዴግ የማይነካበት፣ የማይወቀስበትና የማይከሰስበት ማማ ላይ እንዲሰቀል መንስኤ ሆኗል፡፡ ዛሬ ላይ፣ ኢህአዴግ ፍርሃትና የግንዛቤ እጥረት የፈጠሩትን ክፍተቶች ተጠቅሞ መንግስትን፣ ስርዓቱንና ሃገርን ዘለግ ሲልም ሕዝብን ተክቷል፡፡ በአጠቃላይ የኢህአዴግ መሰረታዊ ችግሮቹ የማይፈተሹና ድርጅቱም የማይወቀስ ወይም ተቃውሞ የማይነካው ሆኗል፡፡
የመብት ገፈፋን፣ የመልካም አስተዳዳር እጦትን፣ ኢኮኖሚያዊ ድቀትን፣ ድህነትንና የአስተዳደራዊ ፍትሕ መመናመንን ተከትሎ በመንግስት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ሃገርንና ስርዓትን እንደ መናድ ሙከራ እየተቆጠሩ፣ ጠያቂዎቹን ገና ከጅምሩ በማሸማቀቅ አጀንዳ ማስጣል የተለመደ ጉዳይ ነው። ውስብስብ የሕግ መሰናክሎቹ ሳይታከሉባቸው ዜጎች መብቶቻቸውን፣ ጥቅሞቻቸውን አልፎ ተርፎም ሕይወታቸውን ባላሰቡት ሁኔታና በድንገት ሲነጠቁ በመኖራቸው፣ ዛሬም ኑሮአቸውን የቆቅ አድርገዋል። ከመሞት መሰንበት መፈክራቸው ሆኗል፡፡ ቀላል በማይባሉ ዜጎች ዘንድ ከስራ ከመፈናቀል አቀርቅሮ መኖር፣ እሺ ባይነትና አድርባይነት ዋጋ እንዳላቸው አማራጮች መታሰብ ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ በራስ ተነሳሽነት በራስ ላይ የሚፈጸም(Self inflicted) ተንበርካኪነትና እሺ ባይነት በበርካታ ዜጎች ዘንድ መስፈኑን ጠንቅቆ የተረዳውና የዜጎች ሃሞት መፍሰሱ የገባው ኢህአዴግም፣ ፍርሃቱንና ሃሞት መፍሰሱን የስልጣን ዘመኑ መደላድል አድርጎ መጠቀሙን ችሎበታል፡፡
መንግስታት በውክልና የተሰጣቸውን ስልጣን በአግባቡ ተጠቅመው፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ጥቅሞች ማረጋገጥ ካልቻሉ ኃላፊነታቸውን በብቃት አልተወጡም ከማለት ውጭ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡ ሃላፊነቱን በብቃት መወጣት ያልቻለ መንግስት ደግሞ ኃላፊነቱን በብቃት ሊወጣ ይችላል ተብሎ ለታመነበትና በዴሞክራሲዊ ምርጫ በሕዝብ ይሁንታ ለሚመረጥ አካል ስልጣኑን ማስረከብ አለበት፡፡ ምርጫ በማጭበርበር፣ በማሸማቀቅና በኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሕዝብን ድምጽ መግዛት ለዛሬ ያውል ያሳድር ይሆናል እንጂ ለዘለቄታው ግን መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡
ኢህአዴግ እንደፖሊሲ አቅጣጫ ይከተለውም አይከተለውም ዜጎች በውስብስብ ችግር መታሰራቸው ሳያንስ፣ መንግስት ከዜጎች ጫንቃ ሊያወርዳቸው በሚገቡ ዘመናዊ ጭቃሹምና ምስለኔዎች መብቶቻቸው እየተረገጡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ሊመጣ ይችላል ተብሎ የሚተረክለትን ኢኮኖሚያዊም ሆነ አስተዳደራዊ ለውጥ በትዕግስት ሊጠብቁ አይገደዱም፡፡ በኢኮኖሚያዊም ሆነ በፖለቲካዊ መስፈርት ሊለኩ የሚችሉ ጥቅሞቻቸው ነገ ሳይሆን ከዛሬ ጀምሮ መከበርና መረጋገጥ አለባቸው፡፡ ነገ ሁልጊዜም ሌላ ቀን ነው፡፡ ስልጣን ለዜጎች ፍትሕና ርትዕን በማጎናጸፍ፣ ሁለንተናዊ ጥቅሞቻቸውን የሚያረጋግጥ መሳርያ እንጂ የሹመኞችን ህይወት ማበልጸጊያና የባለሟሎቻቸው መጠቃቀሚያ መሳርያ መሆን የለበትም፡፡
ከላይ ለማየት እንደተሞከረው አምባገነን መንግስታት መብት ለማፈን መሳርያ ከሚያደርጓቸው ስልቶቻቸው መካከል አንዱ ዜጎች የሚያነሷቸውን የመብት ጥያቄዎች ስርዓትን ከመናድ ጋር በማቆራኘት፣ ህዝብን በተጽእኖና በማሸማቀቅ መብቱን የማይጠይቅ፣ አማራጭ የማይሻና መድረሻ የለሽ ጥገኛ አድርገው መግዛት መቻላቸው መሆኑ ጥርጥር ለውም፡፡
ኢህአዴግ “ሕዝባዊ መንግስት” ስለሆንኩ ሕዝቡ “የኔ ነው” የሚል መሰረት የሌለው የተዛባ እምነት አለው፡፡ ሕዝብ ሲል በምን ዓይነት ተጨባጭ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ ሕዝብን ይዞ እየተጓዘ እንደሆነ በቅጡ ለመረዳት የቻለ አይመስልም፡፡ ኢህአዴግ አመነም አላመነም በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን በነጻ መንፈስ ልቡ የተሞላና አንገቱን ቀና አድርጎ የሚራመድ፣ መብቱንና ግዴታውን ጠንቅቆ የሚረዳ፣ የራሱን መብት ለማስከበር የሌሎችን መብት የማይፃረር፣ ሳይሸማቀቅ ለምርጫ ወጥቶ ከአማራጮች ውስጥ ጥቅሙን መሰረት አድርጎ እነእገሌን እመርጣለሁ የሚለውን ዓይነት ሕዝብ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡
በግምት ለምርጫ ከደረሱ ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች መካከል ስድስት ሚሊዮን አባል አለኝ በሚለው ኢህአዴግ ስሌት መሰረት፣ የዜጎች የነፍስ ወከፍ ትስስር ሲሰላ፤ በየአምስቱ ዜጎች መካከል አንድ የኢህአዴግ አባል እንዳለ ውጤቱ ይነግረናል፡፡ ስድስትም አስርም ሚሊዮን አባል መመልመል የፓርቲዎች መብት ነው የሚሉ በርካታ የዋሆች እንዳሉ እገምታለሁ፡፡ የዋህ ያልኳቸው በሌላ ምክንያት ሳይሆን ያልተረዱት ወይም ሊረዱት የማይፈልጉት ነገር እንዳለ ስለምገምት ነው፡፡ ኢህአዴግ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አባላትን መመልመል የሚችለው ልዩ የምልምላ ሙያ ስላለው አይደለም፡፡ ይልቁንም ቅድም ከጠቀስኳቸው ጉዳዮች በተጨማሪ ሁሉንም የመንግስት መዋቅሮች ጨምሮ መንግስታዊና ሕዝባዊ ተቋማትን የፓርቲ ስራ መዘወርያ ማሽን ስላደረጋቸው መሆኑን ግልጽ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በማንኛውም መስፈርት ጤናማ ምልመላ ሊባል አይችልም፡፡ በእርግጥ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ጉዳይ በፓርቲው ፍልስፍናና ፖሊሲዎች ተጠምቀው፤ በአስተሳሰብ ድጋፍ ከኢህአዴግ ጋር የተሰለፉ አባላት ጉዳይ እንደተጠበቀ ቢሆንም፣ ቀላል የማይባሉ አባላቱ ግን ዘለቄታ ላለው ጥቅማቸው ሳይሆን ለእለት ኑሮአቸው ሲሉ በኢህአዴግነት የሚመለመሉ መሆኑን የመልማዮቹና የተመልማዮቹ ልብ በቅጡ እንደሚረዳው በቂ ግንዛቤና ተመክሮ በሁላችንም ዘንድ መኖሩን አልጠራጠርም ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘመናት የነገሰና ስር የሰደደ ድህነት፣ ስራ አጥነትና ማህበራዊ ቀውስ የተንሰራፋባት ሃገር ናት፡፡ ኑሮ ያደቀቃቸው ዜጎች ከመተዳደር ለመገዛት የተመቹ መሆናቸው ዓለም የመሰከረው እውነታ ነው። የስራ እድል፣ ትምህርት፣ የቀበሌ ራሽን፣ የጤና አገልግሎት፣ የመሰረተ ልማት ፍጆታ፣ የመኖርያ ቤት አቅርቦት በገዢው ፓርቲና በመንግስት ችሮታ ስር በተያዙባት ኢትዮጵያ፤ የኢህአዴግ አባል መሆን በተለይ ደግሞ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ማህበረሰብ የመብት ጉዳይ ሳይሆን አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ በ2002 ምርጫ ኢህአዴግ 99.6 በመቶ ማሸነፍ ባልቻለ ነበር፡፡
ጤናማና ሚዛናዊ በሆነ ዴሞክራሲያዊ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ውስጥ አንጻራዊ ብልጫ ማስመዝገብ ፍትሐዊ ነው፡፡ ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ስድስት በመቶ በምርጫ ማሸነፍ ግን በመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ ላይ ትልቅ ችግር መኖሩን ጠቋሚ ነው፡፡ ለንጽጽር ስለማይመች በዴሞክራሲ የበለጸጉት ሃገራትን የምርጫ ውጤት መፈተሹ የማይሞከር ነው፡፡ ይህም ሆኖ በሁለንተናዊ የድል ባለቤትነታቸው የሚተማመኑት ሶሻሊስቶችም ቢሆኑ ብቻቸውን እንደተወዳደሩ እያወቁ፤ የማይደግፋቸው ማህበረሰብ ሊኖር እንደሚችል ቀልባቸው ስለሚነግራቸው የምርጫ ውጤታቸውን ከዘጠና አምስት በመቶ በላይ አያሳድጉም፡፡ ከዚህ አኳያ ኢህአዴግ ለዴሞክራሲው ይቅርና ለቀልቡና ለጥላው እንኳን መታመን ያልቻለ ድርጅት መሆኑን ምርጫ 2002 በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡
ሕዝቦች የስልጣን ባለቤቶች ናቸው፡፡ የምርጫው ውጤትም በእጃቸው ላይ ነው፡፡ እናም ሁላችንም የምርጫ ካርድ እንውሰድ፡፡ ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻና ፍትሐዊ እንዲሆን የበኩላችንን ጥረት እናድርግ። ምርጫ ዘጠና ሰባት ያሳየንን የሕዝብ ጉልበት በተግባር ላይ እናውለው፡፡ አሁንም ከተደራጀንና በነቂስ ለምርጫ ከወጣን እንዲሁም በስፋት ከታዘብን ማሸነፍ በእጃችን ያለ አማራጭ መሆኑን አንዘንጋ። የፊታችን ሚያዝያ በሚካሄደው የአካባቢና የአዲስ አበባ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ኢህአዴግን በምርጫ ማሸነፍ ይቻላል - ከአዲስ አበባ መስተዳደር፡፡
ምርጫው ነጻ ሊሆን እንደማይችል ከሂደቱ ከተረዳን፤ መራጮች ያለመምረጥ መብታችንን ተጠቅመን ከምርጫ መታቀብ አስፈላጊ ስልት ነው። ኢህደአዴግን መምረጥ የሚፈልገው ማህበረሰብ ከሃምሳ ፐርሰንት በታች ሊሆን እንደሚችል የምርጫ 2002 እውነታ ያስረዳል፡፡ ከበርካታ ምርጫ የማጭበርበር ድርጊት በኋላም፣ ከ45 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ኢህአዴግን አልመረጠም፡፡ በዚህ መንገድ ምርጫው በቂ የህዝብ ይሁንታ ( Vote of confidence) የሌለውና ከሃምሳ ፐርሰንት በታች የሚሆኑ የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎቹ ውጤት ብቻ መሆኑን ማሳየት ይቻላል፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ

Friday, 4 January 2013

የ21 ዓመት ፀረ-ኢትዮጵያዊ፣ ፀረ-ኦርቶዶክስ እና ፀረ-ብሔረ አማራ አምባገነናዊ እና ዘረኛ አመራር (ከ Freedom4Ethiopia ጦማር)

የ21 ዓመት ፀረ-ኢትዮጵያዊ፣ ፀረ-ኦርቶዶክስ እና ፀረ-ብሔረ አማራ አምባገነናዊ እና ዘረኛ አመራር posted by Aseged Tamene

በጣሊያን ወረራ ጊዜ የወያኔው መለስ ዜናዊ አያት አቶ አስረስ ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት የመጡትን ጣሊያኖች እየመሩ አርበኞችን ሲያስጨፈጭፉ የነበሩ ባንዳ ስለነበሩ፣ ፋሽስት ጣሊያን በአርበኞች ተጋድሎ ድል ተነስቶ ነፃነትን ካስመለሱ በኋላ፤ የአገሬው አርበኛ እና ሕዝብ ተሰባስቦ “ለአቶ አስረስ ሚስት የዳረ ጥቁር ውሻ ይውለድ” ተብሎ ቢማማሉባቸውም አቶ አስረስ የመለስን አባት አቶ ዜናዊ አስረስን ወለዱ። ከዚያም ጥቁር ውሻ ውለዱ የተባለው እርግማን በአቶ ዜናዊ አስረስ ደርሶ፤ አቶ ዜናዊ አስረስ ከወ/ሮ አረጋሽ ገብረልዑል በግንቦት 1 ቀን 1947 ዓ.ም. ጥቁሩን ውሻ መለስ ዜናዊን ወለዱ።
ጥቁሩ ውሻም /መለስ ዜናዊ/ ከባንዳ ቤተሰቡ በወረሰው ቂም በቀል፣ በዘር ጥላቻ አጋንንት እና መርገም ተለክፎ አደገ። መሰል ባንዳ ጓደኞቹ – ከነስብሃት ነጋ በረከት፣ ስምዖን እና ሌሎቹ ጋርም ጫካ ገባ። የዋሁ የኢትዮጵያ ሕዝብም የባንዳዎቹ የማስመሰያ ጩኸት እውነት መስሎት ድጋፉን ሰጣቸው እና ጥቁሩ ውሻ ለስልጣን በቃ። በእስስታዊ አስመሳይነቱ የተካነም ጥቁር ውሻ ሆነና “ኢትዮጵያ የምትባልን አገር፣ ኦርቶዶክስ የሚባልን ሃይማኖት፣ አማራ የተባለን ብሔር”፤ ቢቻል ከምድረ ገጽ ለማጥፋት፣ ካልሆነም አንኮታኩቶ ለመጣል የበቀል ሰይፉን ጀመረ፤
• ለዘመናት በቋጠረው ቂምና በቀል፤ መሰል ዘረኛ ጓደኞቹን ሰብስቦ፣ የጎሳ ፖለቲካውን መርዝ በመንዛት፣ አገር የሚያስገነጥል እና የአንድ ጠባብ ጎሳን የበላይነት የሚያረጋግጥ፣ የጥላቻ እና ዘረኛነት ልክፍት ያለበት፣ በተለይ አማራውን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ፣ “ትግራይ እስክትለማ – ሌላው አገር ይድማ” ብሎ የተነሳና የቀሪውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕድገት እና ብልጽግና የሚያኮስስ፣ ለማይተባበሩት የትግራይ ተወላጆች እንኳ ግድ ቀርቶ ርህራሄ የሌለው – የሃውዜንን ጭፍጨፋ እና የ77ቱን የድርቅ እርዳታ ስንዴ ታሪክ ያስታውሷል ፣ ሕወሃት የተባለ የአንድ ጠባብ ጎጠኛ እና ፋሽስታዊ ዘረኛ ኤምፓየር መሠረተ፣
http://tassew.files.wordpress.com/2011/07/tplf_manifesto_-_1968_e-c.pdf በዚህ ሊንክ ያለውን የሕወሀትን የ1968 (በኢትዮጵያ አቆጣጠር ) የመገንጠል እና የፀረ-አማራ የፖለቲካ ፕሮግራምን ይመልከቱና በኤርትራና አሰብ መገንጠል፣ በባድሜ፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ የአገራችንን ድንበር እንዴት እንዳስቆረሰ፤ በአርባጉጉ፣ በበደኖ፣ በሐረር፣ ወዘተ በአማራው ላይ የተፈጸመውን ጅምላ ጭፍጨፋ ልብ ይበሉ::
• ጥቁሩ ውሻ እና አውሬው ሕወሃትም ከጉዲፌቻ አባታቸው ከሻዕቢያ በሚሰጣቸው መመሪያ መሠረት፤ ከ3000 ዓመት በላይ የታሪክ ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን – ታሪኳን እንደ ድንበሯ ቆራርጠው የ100 ዓመት ብቻ አደረጉት፣ ያገኙትን የታሪክ አሻራ የሆኑ ማሥረጃዎች እና ቅርሶች ሁሉ በቻሉት መጠን አወደሙ፣
• ጥቁሩ ውሻም ለኖህ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን፣ የምህረትና የሰላም ቃልኪዳን ምሳሌ የሆነችውን፣ አያት ቅድመ አያቶቻችን ኢትዮጵያውያን አርበኞች፤ አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍስሰው ከፋሽስትና ከጠላት ጠብቀው ያቆዩዋትን፤ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማችንን፤ ከባንዳ አያቱ በወረሰው የፋሽስቶች የጥላቻ ስድብ እና ንቀት “ጨርቅ” ብሎ አንቋሸሻት፣
• ኢትዮጵያ የምትባልን አገር የመበታተን ተግባሩን ኤርትራንና አሰብን በማስገንጠል አንድ ብሎ ጀመረ፣
• ቀጥሎም በፊት የወሎ ክፍለ ሃገር አካል፣ በኋላም በራስ ገዝነት ራሷን ችላ ትተዳደር የነበረችውን አሰብን አስገንጥሎ፤ ኢትዮጵያን ያለ ወደብ አስቀረ፣ ዛሬ ለጅቡቲ በቀን ከ 3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለወደብ ኪራይ ይከሰከሳል፣ ከአሰብ ጅቡቲ ከ300 ኪሜ በላይ ስለሚርቅም ተጨማሪ የመጓጓዣ ወጭ እና የኑሮ ውድነት አስከትሏል፣
• አሰብ የነበረውንም የነዳጅ ማጣሪያ አብሮ ከአሰብ ወደብ ጋር ለእናቱ ዘመዶች ለኤርትራ በማስረከቡ፤ የነዳጅ ድፍድፍ በርካሽ እየተገዛ ይጣራ የነበረውን የነዳጁም ተረፈ ምርት ለአስፋልት ሬንጅ እና ለሌሎች ዕቃዎች ምርት ይውል የነበረውን፤ ዛሬ ኢትዮጵያ የተጣራ ነዳጅ እና ሬንጅ በውድ ዋጋ በዶላር እንድትገዛ በመገደዷ የነዳጅ ዋጋ እየናረም የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፣
• በእምየ ምኒሊክ ጥረት ከጅቡቲ-አዲስ አበባ የተዘረጋው የምድር ባቡር እድሜ ሳይገድበው እየተንገዳገደ፤ ከ100 በላይ ባለተሳቢ መኪኖች የሚያጓጉዙትን ቁሳቁስ፤ በአንድ ጊዜ በአንድ መኪና ወጭ ጠቅልሎ ያመጣልን የነበረውን ባቡር በማኮላሸት፣ በትራንስ ኢትዮጵያ ኩባንያ ስም የሚንቀሳቀሱት የሕወሃት የደረቅ ጭነት ማመላለሻ መኪኖች እንዲሸቅሉበት እና የሸቀጦች የትራንስፖርት ዋጋ እንዲንር እና የኑሮ ውድነት እንዲከፋ አስደረገ፣
• አማራው ላይ የቋጠረውን ቂም ለመበቀል በአርባ ጉጉ እና በበደኖ በፕላን የተቀነባበረ የእጅ አዙር የጅምላ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ አስደረገ፣
• አማራውን ነፍጠኛ እና ትምክህተኛ እያለ የሌላው ጎሳ እንዲነሳበት፣ የበሬ ወለደ የጥላቻ ዘመቻ በአፄ ሚኒሊክ ላይ በሰፊው በመክፈት እና በሰፈራ ሄደው የሚኖሩትን ዜጎች የአማራ ተወላጆችን አስወጡ በማለት ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲፈናቀሉ አስደረገ። ከተለያዩ ክልሎች በቅርቡም በ2004 ዓም. ከደቡብ ክልል እንዲፈናቀሉ ከአስደረገ በኋላ አማራዎች አይደሉም ምሥራቅ ጎጃሞች ናቸው አለ፣ ቀደም ሲልም በአማራው ላይ ነፍጠኛ ትምክህተኛ የሚል ቅጽል ስም አሰጥቶ የጥላቻ መርዙን ከረጨ በኋላ አማራውን ሳይሆን ሰሜን ሸዋዎችን ነው ብሎ ለመከፋፈል ሞከረ፣
• በሰሜን ምዕራብ ጎንደር እና በወሎ ክፍላተ ሃገራት በኩል ያሉትን ሰፋፊ እና ለም ወረዳዎች ቆርሶ ተወላጁን እና ነዋሪውን አማራ በግዴታ አፈናቅሎ ወደ ትግራይ ክልል አጠቃለለ፣
• በምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል በቦታው ያሉትን ኢትዮጵያውያንን፣ በተለይም አማራውን በማፈናቀል፤ ለአማራ ብሔር ጥላቻ ባለው የሕወሃት ዘረኛው የጎሳ ፓርቲ ታዛዥ በሆነው የአገው ዘር እንዳለበት በሚታማው ወሎየ ነው በተባለው በደመቀ መኮነን ፈራሚነት፤/በወቅቱ የአማራ ክልል ም/ፕሬዚዳንት ስለነበረ እና ለዚያ አገር ቆርሶ የመሸጥ ውለታው የሚኒስቴርነት አሁን ደግሞ የም/ጠ/ሚኒስቴርነት ማዕረግ የተሰጠው/ ከ60 ኪሜ በላይ ወደ ውስጥ ከ1000 ኪሜ በላይ ርዝማኔ ያለው ለም የእርሻ መሬት እና አፄ ዮሐንስ አንገታቸውን የተሰየፉላትን የዮሐንስን ከተማን ጨምሮ ለሱዳን ገፀ-በረከት ሰጠ፣
• ደርግ የሠራውን ወያኔ እያፈረሰበት እና በቀን በሚሊዮን የሚቆጠር ወጭ ለጦርነት እያወጣ፣ ያለምንም እርዳታ እና ብድር የሠራውን በፓዌ የጣና በለስን፣ በጋምቤላ የአልዌሮን እንዲሁም በጎዴና ሌሎች አካባቢዎች የሠራቸውን ሰፋፊ የመስኖ ፕሮጀክቶች 21 ዓመት ሙሉ ውሃቸው በከንቱ እንዲፈስስ እና የእርሻ መሬቱ በጫካ እንዲወረር፣ በአገሪቱም የምርት እድገት እንዳይኖር አደረገ፣
• ዘረኛው የሕወሃት ፓርቲ ሥልጣን ሲይዝ ከ18 ዓመት በታች ዕድሜ የነበራቸው የገበሬ ልጆች በወቅቱ መሬት አላገኙም ነበር። ዛሬ ቢያንስ 38 ዓመት ይሆናቸዋል። ከዚህ ዕደሜ በታች ያለው እና ጎጆ ወጥቶ የሚኖር አርሶ አደር በሙሉ የሚያርሱት መሬት አጥተው፣ በጋምቤላ እና ፓዌ የሚገኘውን ሰፋፊ የመስኖ ቦታዎች ለአረቦች እና ለህንዶች ሰጠ – ለዚያውም ምርቱ ለአገር ውስጥ ፍጆታ ለማይውል እና የጋምቤላ እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳያምኑበት እና ሳይቀበሉት፣
• የዘረኛ ፖለቲካየን አልተቀበላችሁም በሚል በሽህዎች የሚቆጠሩ የአማራ አርሶ አደሮችን “ቢሮክራት” የሚል ቅጽል ስም በመስጠት መሬታቸውን ነጥቆ፣ ከነቤተሰቦቻቸው ጦም እንዲያድሩ ፈረደባቸው፣
• ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እንዳይኮራ “ለወላይታው የአክሱም ሃውልት ምኑ ነው” ብሎ ዘረኛነቱን በይፋ አሳወቀ፣
• ከትግራይ ብሔር ውጭ ያለውን የንግዱን ማህበረሰብ በግብር ሰበብ አዳክሞ የንግድ እንቅስቃሴው በአንድ ጎሳ እጅ ውስጥ እንዲወድቅ አደረገ፣
• በ17 ዓመት የትጥቅ ትግል ወቅት በወያኔ እና በደርግ በኩል ያልሞተ የወታደር ቁጥር በባድሜ ሰበብ፣ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ60 ሽህ በላይ ንፁሃን ዜጎችን ከአስጨፈጨፈ በኋላ፣ ለኤርትራ እንዲሰጥ አስደረገ – ለዚያውም ኢትዮጵያ ልታሸንፍበት የምትችለውን ማስረጃ አልቀበልም ብሎ የወደቀ እና በአድዋ ጦርነት የተሻረ የጣሊያንን ማሥረጃ በመምረጥ- ለዚያውም ኢትዮጵያ በይገባኝ የመጠየቅ መብት እንዳይኖራት አስቀድሞ ፍርዱ ይግባኝ እንዳይኖረው በመማፀን – ለዚያውም ኢትዮጵያውያን የሕግ ባለሙያዎች ጥብቅና በነፃ እንቁም እያሉ በብዙ ሽህ ዶላር ለኢትዮጵያ ደንታ የሌለው ሰላቶ ጥብቅና እንዲቆም በመግዛት፣
• በሳሊኒ አማካይነት ጎጃም ድንበር የነበረውን የጣና-በለስን ከፍተኛ የመስኖ ፕሮጀክት በማፈራረስ ማሽነሪውን ዘርፎ ሱር ኮንስትራክሽን ብሎ ካምፓኒ መሠረተ፣ ለመስኖ ሥራው ደጋፊ ቱቦ ማምረቻ የነበረውን የፕላስቲክ ፋብሪካ በፕራይቬታይዜሽን ስም ወረሰው፣ በተመሳሳይ መልኩ በመላ አገሪቱ /በተለይም ጎንደር በጎጃም በወሎ በወለጋ በከፋ በአርሲ ክፍላተ ሃገራት/ ሜካናይዝድ እርሻ ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ጀምረው የነበሩትን የገበሬዎች አምራቾች የህብረት ሥራ ማኅበራት እና የመንግሥት እርሻዎች አፈራርሶ ማሽነሪዎቹን ወደ ኤርትራ በማጓጓዝ ኢትዮጵያ ወደ ጥንታዊውና ኋላቀሩ የማረሻ እርሻ እንድትመለስ እና የተጀመረው ዘመናዊው የግብርና ዘዴ 21 ዓመት ወደ ኋላ እንዲሄድ አደረገ፣
• የማያነቡ ዓይኖች የማይጽፉ እጆች አይኖሩም ብሎ ደርግ የጀመረውን የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ ዘግቶ ማይምነት እንደገና እንዲስፋፋ አደረገ፣ የትምህርት ፖሊሲውንም ደረጃ በማውረድ “ዓላማችንን ተቀብሎ ያሳካልን እንጅ ዘበኛም ቢሆን ሚኒስቴር አድርገን እንሾማለን” ብሎ ደንቆሮ የትምህርት ሚኒስቴር በመሾም ደንጋይ ፈላጭ የምሁር ደንቆሮ ያስፈለፍል ጀመረ – ደንጋዩዋ /ኮብል ስቶንዋ/ እንኳ ባቅሟ የተማረ ይጥረበኝ ትበል
• የሚሠሩ እጆች እንጅ የሚሰርቁ እጆች አይኖሩም ብሎ መንጌ ቢፎክር በስርቆት እና በውንብድና ስልጣን ላይ ፊጢጥ ያለው መለስ ዜናዊም “መሥረቅም ሥራ ነው – እስካልተያዙ ድረስ” በማለት በይፋ በማወጅ እና በሙስና የተካነ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለይስሙላ አቋቁሞ አገሪቱን ለዘራፊዎች ዳረጋት፣
• አፄ ሚኒልክ ጊዮርጊስን አብረው አስሸክመው ወደ አድዋ በመዝመት ጣሊያንን ድል ማድረጋቸው ያንገበገበው የባንዳው የልጅልጅ “ለአማራው -ነፍጠኛ የሚል ስያሜ፣ ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ደግሞ የነፍጠኛ ምሽግ” እያለ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለማጥፋት ከኦርቶዶክስ እምነተ – አምልኮ ውጭ የሆኑ “ድንግል ማርያም ከአዳም የተወረሰው የውርስ ሃጢያት አለባት” ብለው የሚያምኑ፣ የጣሊያን ባንዳዎችን እምነት የሚያራምዱ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ደንብ እና ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች አሿሿም ሥርዓት ውጭ፣ ዘረኛ ፓትርያርክ ሾሞ፤ መጽሐፍ ቅዱስ በቀላል አማርኛ ይተርጎም በሚል ሰበብ የኦርቶዶክስን እምነት በሚበርዝ መልኩ የትርጉም ለውጥ አስደረጉ፣ ይህንን የተቃወሙትን ታላላቅ የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንት አስደዱ፣ በስውርም አስገደሉ፣ ገዳማትና ቤተክርስቲያናት እንዲቃጠሉ፣ ንዋዬ ቅድሳት እንዲዘረፉ አስደረጉ፣ በልማት ሰበብ የዋልድባ ገዳም እና በአካባቢው የሚገኙ ቤተክርቲያናትን ለማፈራረስ ሥራ አስጀመረ፣ መነኮሳቱን አስደበደበ፣ አሳሰረ፣ አስሰደደ፣
• ከ1997 ምርጫ በኋላ የትግራይ ተወላጆች ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር ተከባብረው እና ተስማምተው ሲኖሩ በጥላቻ ቅናት በመብገን “መርካቶ ገጀራ ተወደደ – ምክንያቱም ትግሬዎችን ለመጨፍጨፍ” በማለት መለስ የተለመደ የኢንተር- ሃምዌይ ሽብር ፈጠራ በማውራት፣ ይህም ትልቅ ዜና ሆኖ የቪኦኤዋ አዳነች ፍሥሓዬ አወያይ ሆና “እንዴት አንድን ጎሳ ለማጥፋት እንዲህ ይደረጋል?” የሚል ተከታታይ ፕሮግራም እንድትሠራ ተደርጎ የትግራይን ሕዝብ ከወገኑ ከኢትዮጵያውያን እንዲነጠል ሞከረ፣
• አረመኔው መለስ ዜናዊ፤ እንደ እነሱ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ያልጠላ ትግሬዎች ላይ የተቀነባበረ የጥፋት ዘመቻ በማካሄድ ሃውዜንን በደርግ ጀቶች በማስደብደብ ንጹሃን ዜጎችን /ሕፃናትን፣ እናቶችን፣ አባቶችን/ በጭካኔ አስደበደበ፤ በ1977 ድርቅ ጊዜ የትግራይን ሕዝብ በግድም በውድም ወደ ሱዳን ሄደው እንዲሰፍሩ አስደርገው፣ ለነፍስ ማዳን የመጣውን የእርዳታ ምግብ ሰርቀው በመከዘን፣ ሕዝብ በረሃብ እየረገፈ እህሉ ለብልሽት እንዲዳረግ፣ የተረፈውንም በመሸጥ የትራንስፖርት መኪኖች ገዝተው በህዝቦች ህይዎት ላይ ነገዱበት፣
• የአማራውን እና የኦሮሞውን ሕዝብ ቁጥር በረቀቀ ዘዴ ለመቀነስ እንዲቻል የጤና ኤክስቴንሽኖች በቤተሰብ ምጣኔ ሰበብ የቤት ለቤት የወሊድ መከላከያ እደላ በሰፊው እንዲሠሩ ተደረገ ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ክሊኒክም የውርጃ ሥራ ብቻ ስለሚሠራ የውርጃ ሕጉን በፓርላማ በማጽደቅ በአማራውና በኦሮሞው ላይ ስውር የዘር ማጥፋት ዘመቻ ከፈተ – በትግራይ ያለው የቤተሰብ ምጣኔ ሥራ የላላ እንደሆነ ለጥቁሩ ውሻ ቀርቦለት ሲመልስ – “ተውት ይወለድ የሚበላ ሆድ ብቻ ሳይሆን የሚያስብ ጭንቅላት እና የሚሠራ እጅ ይዞ ነው የሚወለደው” አለ። ታዲያ በአማራውና በኦሮሞው ላይ ብቻ ለምን? ለዚያ ነበር የአማራው ብሔር ቁጥር በአንድ ጊዜ ወርዶ ዘጭ ያለው!
ግን ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የቃል ኪዳን አገሩ ነችና ሊጎበኛት ፈቀደ እና ቀንደኛ ነቀርሳዎቿን ጥቁሩን ውሻ መለስ ዜናዊን እና ተጋዳላይ ጳውሎስን በጉጠቱ ነቅሎ ጣላቸው! አሁንም ኢትዮጵያውያን በርትተው ከጸልዩ እና ፈጣሪያቸውን ከተማፀኑ ጠላቶቻቸውን ይበታትንላቸዋል።
ብሔራዊ እርቅ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ዕድገት እና ብልጽግና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች!!!
ጥቁሩን ውሻ የነቀለ ሃያሉና ሕያው እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!! አሜን!!!
posted by Aseged Tamene

Saturday, 22 December 2012

የህወሓት የብረት መዳፍ(ተመስገን ደሳለኝ)

 
(ተመስገን ደሳለኝ)
የድህረ-መለስ ዝግመተኛውና መቋጫ ያጣው የፖለቲካ ማዕበል፣ አሁንም አዳዲስ ክስተቶችን ማሳየቱን አላቋረጠም፡፡ ዝነኛው ‹‹የመለስ
ራዕይ›› መፈክርም ግንባሩን የታሰበውን ያህል ወደ አንድ ለማሰባሰብ አቅም ያጠረው ይመስላል፡፡ ጥገናዊ ለውጦቹም እንዲሁ አትራፊ
መሆን አልቻሉም፡፡ መሀል አራት ኪሎ በሚገኘው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ግድግዳ ላይ የተሰቀለው የመለስ ፎቶም ‹‹ሸምጋይ››
አልሆናቸውም፡፡ በብሄር ተኮር ፍላጎት የሚወዛወዘው የኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስትም ለሁለት ወር ከአስር ቀን ያህል ያለ ሚንስትሮች
ምክር ቤት (ካቢኒ) ስልጣን ላይ የቆየ ቢሆንም፣ ህዳር 20/2005 ዓ.ም. ካቢኔውን ሲያቋቁም ሁለት ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ
ሚኒስትሮች እና ሶስት ሚኒስትሮችን ለፓርላማው በማቅረብ እንዲሾሙ አድርጓል፡፡ በዚህ ፅሁፍም የሁለቱን ምክትል ጠቅላይ
ሚንስትሮች ሹመት ከህገ-መንግስቱ አኳያ ያለውን ህጋዊነት እና ከሹመቱ ጀርባ ያሉ ፖለቲካዊ መግፍኤዎችን እንዳስሳለን፡፡
ስንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች?
በኢትዮጵያ አውድ ስለስልጣን ስንነጋገር ለህጋዊነቱ ማረጋገጫ የሚሆነን በራሱ በገዥው ፓርቲ ‹‹ፊታውራሪነት›› በ1987 ዓ.ም.
የፀደቀው ህገ-መንግስት ነው፡፡ ስለዚህም የሶስቱ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሮች ሹመት ምዘና መነሻም ይህ ይሆናል፡፡
ህገ-መንግስቱ በአንቀጽ 9 በግልፅ ‹‹የሕገ-መንግስት የበላይነት›› በሚል ርዕስ፣ በቁጥር ሶስት ላይ ያስቀመጠው እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹በዚህ ህገ-መንግስት ከተደነገገው ውጭ በማናቸውም አኳኋን የመንግስት ስልጣን መያዝ የተከለከለ ነው፡፡››
እንግዲህ ይህ ድንጋጌ በግልጽ በመቀመጡ ይመስለኛል የ‹‹ሶስቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች›› ሹመት ‹‹ኢ-ህገ-መንግስታዊ›› የሚል
የተቃውሞ ወጀብ የከበበው፡፡ የዚህ ተጠየቅም ሄዶ ሄዶ የሚያርፈው ህገ-መንግስቱ ላይ በመሆኑ፣ መከራከሪያ የሚሆነው ህገ-መንግስቱ
ስለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሿሿም በአንቀፅ 75 ላይ ያስቀመጠው ነው፡፡ በዚህ አንቀፅ መሰረትም አንድ እንጂ፣ ሶስት ምክትል
ጠቅላይ ሚኒስትር መሾም አይቻልም፡፡ በተጨማሪም ህገ-መንግስቱ በእንዲህ አይነቱ ድንገቴ የውስጥ አብዮት በሚነሳበት ወቅትም ቢሆን
የሁለቱ ምክትሎቹን የመሰለ ሹመት እንዳይኖር በር የዘጋ ነው፡፡ የህግ ባለሙያዎች ትንታኔም ‹‹በህግ ያልተገለፀ ነገር፣ እንዳልተፈቀደ
ይቆጠራል›› ሲል ይህንን ሀሳብ ያጠናክራል፡፡
አዲሱ ሹመትም ያፈረሰው የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 75 ‹‹ስለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር›› በሚል ርዕስ ስር የገለፀው እንዲህ ይላል፡-
1. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ሀ) በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፣
ለ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ተክቶት ይሰራል
መቼም እንዲህ ተብራርቶ የተቀመጠ ህግን ‹‹ለትርጉም አሻሚ ነው›› ልንለው አንችልም፡፡ ምክንያቱም ይህ አንቀጽ ሌላ ቀርቶ ‹‹ወዘተ››
እንኳ ብሎ ያልተገለፀ ስልጣን አልሰጠም፡፡ በአናቱም ‹‹ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ እንዲህ ያደርጋሉ፣ ይህንን ይቆጣጠራሉ፣ በክላስተር
ይታቀፋሉ…›› ሲል የደነገገው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ንቅፈ-ክበብ ግልፅና አጭር ነው ማለት ነው፡፡
ይኸውም ‹‹ዋናው በሌለበት ጊዜ ተክቶ መስራት››፣ እና ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተለይቶ የሚሰጠውን መተግበር››፡፡ ከዚህ አኳያም
ነው በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ ‹‹የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ›› እና ‹‹የኢኮኖሚ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ››
የሚለው የሁለቱ ሰዎች ሹመት ህገ-መንግስታዊ ዕውቅና የለውም ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርሰን፡፡
በእርግጥም ጉዳዩን በጥቅሉ ስናየው የሁለቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት የህገ-መንግስት ድጋፍም ሆነ ተቀባይነት ሊኖረው
እንደማይችል ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህም ሹመቱ ሊያያዝ የሚችለው ከፖለቲካ ውሳኔ ጋር ብቻ ነው፡፡ በዚህም ሕገ-መንግስቱ በይፋ ተጥሷል፡፡
ይህ ማለት ስርዓቱ ከህግ-ውጭ ሲሰራ ይህ የመጀመሪያው ነው እንደ ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም የኢህአዴግ የኋላ ታሪኩ የሚነግረን
ዘመኑን ሙሉ ህገ-መንግስቱን እንዳሻው ሲጥሰው፣ አሳስቶ ሲተረጉመው፣ ሲያሴስነው፣ ሲገፋው እንደነበር ነው፡፡ ይህን የሚያደርገው
የፖለቲካ ጠቀሜታውን በማስላት ነው፡፡ አሳዛኙ ነገር ግን ይህ ህገ-መንግስት ህልውናው የሚገለፀው ተቀናቃኞቹን ለማጥቃት ባስፈለገ ጊዜ
ብቻ መሆኑ ነው፡፡ (በድህረ ምርጫ 97 ለእስር የበቁት የቅንጅት አመራሮች ‹‹ህገ-መንግስቱን ለመናድ አሲረዋል›› በሚል ክስ ነው፡፡
እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙ፣ አንዱአለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ፣ እነ ጄኔራል ማሞ ተፈራ… የመሳሰሉትም ቃሊቲ የተወረወሩት ‹‹ህገ-
መንግስቱን ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል›› ተብለው እንደሆነ ይታወሳል)
የሆነ ሆኖ ህገ-መንግስቱ በአቶ መለስ ዘመን እንደ ግለሰብ፣ እንደ ህወሓት እና እንደ ኢህአዴግ በተደጋጋሚ ጊዜያት ሲጣስ ተመልክተናል፡፡
ለምሳሌ በ93ቱ የህወሓት ክፍፍል ወቅት መለስ ራሳቸው ህወሓት ውስጥ የተፈጠረውን የልዩነት ችግር ለመፍታት ሲሉ ‹‹የህወሓት ህገ-
ደንብ ድርጅቱን ከአደጋ ስለማይከላከለው፣ ከህግ ውጭ ተጉዘን በህገ መንግስቱ መጠቀም መቻል አለብን›› ብለው በአደባባይ
ተከራክረዋል፡፡ የተከራከሩበትንም ወደተግባር መቀየራቸው ይታወሳል፡፡ የተቃወማቸውም አልነበረም፡፡ ይህን የሰውዬውን መከራከሪያ
አሁን ለተከሰተው ኢ-ህገ-መንግስታዊነት የህወሓት ሰዎች እንዴት እንዳዋሉት አንድ መላምት ልንሰጥ እንችላለን፡፡ እንደሚታወቀው፤
ኢህአዴግ ላረቀቀው ህገ-መንግስት ተከብሮ መኖር ራሱን ብቸኛ ዕምነት የሚጣልበት ቡድን አድርጎት ያስባል፡፡ ‹‹እኛ ከሌለን ሀገሪቱ
ትበታተናለች›› የሚለው ፍልስፍናው፤ እርሱ በስልጣን ላይ ካልቆየ ህገ-መንግስቱ በአንድ ምሽት ብትንትኑ ሊወጣ እንደሚችል ከልቡ
እንዲያምን አድርጎታል፡፡ ስለዚህም፤ በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረውን ሽኩቻ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድም ቢሆን ማርገብ ካልተቻለ ፓርቲው
ሊፈራርስ ከዚያም እነርሱ እንደሚያምኑት ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ሊያበቃለት ይችላል፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊትም ፓርቲውን ኢ-ህገ-
መንግስታዊ በሆነ መንገድ በማቆየት፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን መጠበቅ ያስፈልጋል የሚል ይሆናል፡፡ እንግዲህ የአቶ መለስ
ተተኪዎችቸውም እናስቀጥለዋለን የሚሉት ‹‹ሌጋሲ›› በዋናነት ህግ መጣሱን እንደሆነ እያሳዩን ነው፡፡
ይህንን የስርዓቱ ድርጊት በማስረጃ ለማሳየት ያህል የሚከተሉትን የህግ ጥሰቶች ማንሳት እንችላለን፡፡ የሰላሳ ሰባቱ ከፍተኛ ወታደራዊ
ሹመት አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱም ህገ-መንግስቱ የጄነራሎችን የማዕረግ አሰጣጥ የሚፈቅደው በጠቅላይ ሚንስትሩ አቅራቢነት ሲሆን ብቻ
ነው፡፡ እዚህ ጋር ያለው የህግ ጥሰት ለመኮንኖች የተሰጠው ሹመት አቶ መለስ ህይወታቸው አልፎ ተተኪ ጠቅላይ ሚንስትር
ባልተመረጠበት ወቅት መሆኑ ነው፡፡ ኃይለማርያም ደሳለኝ ‹‹ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር›› ተብለው የቆዩበት ጊዜም እንዲሁ ህገ ወጥነት
ነው፤ ህገ-መንግስቱ ‹‹ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር›› ለሚባል ሹመት እውቅና አይሰጥምና፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብለው ሳይሾሙም
ለሁለት ወር ያህል ሀገሪቱ ያለመንግስት የቆየችበት ጊዜም የዚሁ ተመሳሳይ የህግ ጥሰት ነው፡፡ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው
ከተሾሙ በኋላ ካቢኔያቸውን ሳያቋቁሙ እስከ ህዳር ሃያ ቀን ድረስ የቆዩበት ሁኔታም ኢ-ህገ-መንግስታዊ ነው፡፡
የሹመቱ አደጋ
ስርዓቱ ጉልበታም መሪውን በሞት ከተነጠቀ በኋላ የተለያዩ ክፍተቶች ተፈጥረውበታል፡፡ እነዚም ክፍተቶች በሂደት በከፍተኛ ደረጃ
ተስፋፍተው ሊጠራርጉት እንደሚችሉ ስጋት ላይ በመውደቁ ይመስለኛል-የህገ-ወጡ ሹመት አላማ፡፡ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮቹን
ብዛት ከአንድ ወደ ሶስት ከፍ ያደረገው ይህ ሁናቴ እንደ አንድ መፍትሄ በመውሰዱ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ አካሄድ በአራቱ ፓርቲዎች
ውስጥ ለተፈጠረው የኃይል ሽኩቻ እንደ እሳት ማጥፊያነት ካልጠቀመ በቀር ዘላቂ መረጋጋትን ማስፈን አያስችልም፡፡ እንዲያውም
በግልባጩ አደጋውን ሊያባብሰው ይችላል፡፡ ምክንያቱም ማዓከላዊ መንግስቱ በህገ-መንግስቱ ውስጥ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይኖር
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተክቶት ይሰራል›› የሚለውን ድንጋጌ የመተግበር ግዴታ ውስጥ ቢገባ ለመተግበር ከባድ ነውና፡፡ መላ ምቱን
ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ አቶ ኃይለማርያም፣ የአቶ መለስ ዕጣ ቢያጋጥማቸው ማን ነው የሚተካቸው? የሚል ጥያቄ ቢነሳ ሙክታር ከድር
ወይስ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ወይስ ደመቀ መኮንን? ግልፅ የሆነ ነገር ስለሌለ ‹‹እገሌ ይተካል›› ማለት አይቻልም፡፡ ምክትሎቹ
በተመሳሳይ ደረጃ ያሉ ይሁኑ ወይም የተለያዩ አልተነገረም፡፡ ይህ ደግሞ ሶስቱም እኩል የአልጋው ወራሽ ሆነው ሊፋጠጡ የሚችሉበትን
ዕድል ያሰፋዋል (ቢያንስ እንዲህ አይነት አደጋዎች ቢከሰቱ እንደ መውጫ በር ለመጠቀም ‹‹ተቀዳሚ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር…››
የሚል አንደኛው ከሁለቱ ሚኒስትሮች የሚለይበት ደረጃ ቢሰጥ ወይም ሁለቱ ምክትሎች ለአንደኛው ምክትል ተጠሪ ለማድረግ
አለመሞከሩ የሰዎቹን ችኮላ በግላጭ ያሳያል፡፡ ምናልባት ደመቀ ቀድመው የተሾሙ በመሆናቸው ብኩርናውን ይወስዱ ይሆናል ተብሎ
ታስቦም ከሆነ አሁንም ይህ የቢሆን ምልከታ ህገ-ወጥነቱ ከማባባስ ውጪ የሚጨምረው አንዳች ነገር የለም)
በአናቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩን የመተካቱ ስራ ከታሰበው በተቃራኒ ሄዶ ቀላል ቢሆን እንኳ ምክትሎቻቸው ብቁ አይደሉም፡፡ በልምድም
በተቀባይነትም፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የፓርቲው ግዙፍ አደጋዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህ
የስልጣን ሹመት የብሄር ተዋፅዖን ለማቻቻል የተደረገ ሊሆን ይችላል የሚለው መከራከሪያ ከኢህአዴግ ሁለንተናዊ ባህሪ ጋር ሲዛመድ
አንድ ከባድ መዘዝ ይዞ ሊመጣ ይችላል፡፡ ፓርቲው እስከአሁን ከሄደበት መንገድ አንፃር ከውስጡ አንድ ብቸኛ ጡንቸኛ ሰው መምጣቱ
ላይቀር ይችላል፡፡ የዴሞክራሲ ማዕከላዊነት የፓርቲው መርህ እና በድህረ-93 መንግስታዊ ተቋማት እንጂ የፓርቲው ጠቀሜታ በአቶ
መለስ ስልጣን ጠቅላይነት የተነሳ እየሟሸሹ መጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአቶ መለስ አርቃቂነት ፓርቲው በሀገሪቱ ላይ ሊከውናቸው
ያሰባቸው የተንሻፈፉ የልማታዊ መንግስት ፅንሰ-ሀሳቦች የአንድን ጉልበታም መሪነት መምጣት የግድ ይላሉ (መለስ ይህን ጉዳይ ተቋማዊነት
ለማልበስ መሞከራቸው ሳንዘነጋ) በዚህን ወቅት የትኛው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አልያም ከየትኛው ብሄር የሚነሳ ሰው ወደዚህ
መንበር ይመጣል? …መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው፡፡ መቼም ከህወሓት ለሚነሳ ሰው የሌሎቹ ብሄር አባላት እንደበፊቱ በዝምታ ያዩታል ማለቱ
ያስቸግራል፡፡
ሌላኛው የአዲሱ ሹመት አደጋ የስልጣን ተዋረድን ለመጠበቅ ወይም በሚኒስትሮች መካከል ተግባብቶ ለመስራት እንቅፋት መሆኑ ነው፡፡
የስራ ልምድ እና ቀደምትነትን (ሲነየሪቲን) መሰረት ያደረገ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ከ15 አመታት በላይ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሆነው
በመስራት በቦታው ላይ የዳበረ ልምድ ያላቸው ሶፊያን አህመድ፣ አሁን ተጠሪነታቸውም ሆነ ሪፖርት የሚያቀርቡት ለጠቅላይ ሚኒስትር
ሳይሆን፣ ‹‹የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ›› ሆነው ለተሾሙት (በልምድም በቀደምትነትም ከእርሳቸው በእጅጉ ለሚያንሱት)
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ኃላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት እንቅፋቶች መፍጠሩ አይቀርም፡፡
ምናልባትም በእንዲህ አይነት ልዩነት የተነሳ በሁለቱ ባለስልጣኖች መካከል ቅሬታ ወይም አለመግባባት ቢፈጠር ችግሩ ከእነርሱ አልፎ
የድርጅቶቻቸው ኦህዴድ እና ህወሓት የመሆን ዕድል አለው፡፡ እዚህ ጋ ሊነሳ የሚችለው ሌላው የሹመቱ ኢ-ህገ-መንግስታዊነት በራሱ
በህገ-መንግስቱ አንቀፅ ሰባ ስድስት፣ በቁጥር አራት እና ስድስት ላይ ‹‹የሚንስትሮች ምክር ቤት›› ስልጣን ተብሎ የተቀመጠው ፋይናንስን
እና ኢኮኖሚን የሚመለከተው ለዶ/ር ደብረጽዮን መሰጠቱ ነው፡፡ …እናም እነዚህ ብጥስጣሽ ምክንያች እርስ በእርሳቸው የሚጋመዱበት
አጋጣሚ ከተፈጠረ አደጋው እውን ይሆናል፡፡
ከሹመቱ ጀርባ
ትልቁ ጉዳይ ኢህአዴግ በዚህ ደረጃ ህገ-መንግስቱን ንዶ፣ አዲስ የስልጣን ቦታ ለመፍጠር ያስገደደው ምንድር ነው? የሚለው ይመስለኛል፡
፡ ከዚህም አኳያ የተወሰኑ ነጥቦችን ከሹመቱ አንጓ ውስጥ እንምዘዝ፡፡
ደህና! ኃይለማርያም ደሳለኝ ተሿሚዎቹን ለተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ባፀደቁበት ወቅት ‹‹ምክንያቴ›› ብለው ከዘረዘሩት እንነሳ፡-
‹‹የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ለማጠናከር፣ ያስፈፃሚነት ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ ለማድረግ የተጀመረው ጥናት በመጠናቀቁ፣ በጥናቱ
በርካታ ልምዶች በመቀመሩ፣ በአዲሱ ትውልድ የኢህአዴግ አመራር የመተካካት ሂደትን መሰረት በማድረግ አስፈፃሚ አካል ለማጠናከር
ዓላማ ያደረገ…››
ይህ ምን ማለት ነው? ምክንያትስ ብሎ ማን ይሆን ያዘጋጃው? ይህ ሁኔታ ሰዎቹ ምን እየሰሩ ነው ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡
የምክንያቱ ቅሽምና የሚጀምረው በተገለፀው ዝባዝንኬ ነገር ብቻ አይደለም፣ በዝርዝሩ ውስጥ ‹‹ህገ-መንግስቱን መሰረት በማድረግ››
የሚል ነገር ለይስሙላ እንኳ ባለመካተቱ ነው፡፡ መቼም ይህ ምክንያት ሌላውን ቀርቶ ራሳቸውንም ሊያሳምን አይችልም፡፡ ባይሆን በግልፅ
እንዲህ ቢሉ የተሻለ ነበር፡-
‹‹እኔ እንደ መለስ ዜናዊ ሀገር ለመምራት የሚያስችል አቅም ስለሌለኝ፣ ስልጣኔን ህገ-መንግስቱ ከሚፈቅደው ውጪ አከፋፍያለሁ፤ ወይም
መለስ ዜናዊ ስልጣን ጠቅልለው የያዙ አምባገነን ስለነበሩና አሁን ደግሞ እርሳቸው ስለሌሉ ዴሞክራሲያዊ አሰራር ተከትለን የስልጣን
ክፍፍል አድርገናል››
ይህ ቢያንስ ለአንድ ሀይማኖታዊ መፅሄት በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ላይ ‹‹እኔም እንደ ዳዊት ጨርቄን ልጣልለት›› እያልኩ እዘምርለታለሁ
ካሉት አምላካቸው ጋር እንዳይቀያየሙ ያደርጋቸው ነበር፡፡
የሆነ ሆኖ ከዚህ ሹመት ጀርባ ያደፈጠው እውነታ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የፖለቲካ ሽኩቻ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መምጣቱን
አመላካች ያደረገው ይመስለኛል-በተለይም በህወሓት እና ኦህዴድ ውስጥ፡፡ ይህ ማለት ግን ህወሓትና ኦህዴድ ተቃቅረዋል ማለት
አይደለም፡፡ በእኔ እምነት ቅሬታ አለ ብዬ የማስበው በሁለቱም ድርጅቶች በራሳቸው ውስጥ ነው-በላይኛው የአመራር አባል እና
በካድሬዎች መካከል፡፡
በዚህ ከተስማማን የህወሓት ብቸኛ ችግር የሚመስለኝ መካከለኛና የበታች ካድሬዎቹ ‹‹መሪዎቻችን በደምና አጥንት ያገኘነውን ስልጣን፤
በመተካካት ስም አስወሰዱብን›› የሚል ግሩምሩምታ ከማሰማታቸው ነው የሚተሳሰር ነው፡፡ እናም ከዚህ አንፃር ሊሆን ይችላል ድርጅቱ
ከህገ-መንግስቱ ይልቅ የፖለቲካ ጉልበቱን ለመጠቀም የተገደደው፡፡ የኦህዴድ የውስጥ ንትርክም የዚሁ ተመሳሳይ ነው፡፡ ‹‹ኦሮሞ መቼ
ነው በቁመቱ ልክ ስልጣን የሚይዘው?››፡፡ ለዚህም ነው ይህ አይነቱ የብዙሀኑ ካድሬ ቅሬታ በሰፊው ከተዛመተ ከራሱ አልፎ አባል
ድርጅቶችንም ጠራርጎ የሚያጠፋ አብዮት ሊቀሰቅስ ይችላል የሚል ስጋት የገባቸው ‹‹አስማት ማሳየት›› የማይሳናቸው የህወሓት ወሳኝ
የአመራር አባላት፣ ኢ-ህገ-መንግስታዊ በሆነ አካሄድ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ ለኦህዴድ በመስጠት ለቅራኔው ጊዜያዊ
ማስተንፈሻ መዘየዱ ተሳክቶላቸውል፡፡
‹‹ህወሓት እየመጣ ነው!››?
በርከት ያሉ የፖለቲካ ተንታኞች ‹‹ህወሓት ወደ ስልጣን እየመጣ ነው›› የሚል አንድምታ ያለው ትንተና እያቀረቡ ነው፡፡ ይህ ግን ስህተት
ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ህወሓት መጀመሪያውንም የትም አልሄደምና (ከመንግስታዊነት ይልቅ ብሄር ተኮር ገፅታ ያላቸው መከላከያ፣
ደህንነት፣ ኢኮኖሚ…የመሳሰሉት በመለስ ዘመንም ሆነ መለስ ካለፉ በኋላ በፓርቲው የብረት መዳፍ ስር እንደዋሉ ናቸው)፡፡ እነዚህ
ተቋማት ደግሞ ለህልውናው እና የበላይነቱን ለማስከበር ወይም እንደ ተቺዎች አገላለፅ ‹‹ለፖለቲካ አስማቱ›› ቁልፍ የስልጣን መገልገያ
መሳሪያዎች መሆናቸው አያከራክርም፡፡ እናም ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው ለህወሓት
የሚጨምረው የፖለቲካ ጉልበት የለም፡፡ ባይሾሙም የሚያጎሉት ነገር የለም፡፡ መጀመሪያውንም የተቀነሰ ነገር አልነበረምና፡፡
ይህ አንድ እውነት ነው፡ ድርጅቱ በመለስ ሞት የተነሳ በተፈጠረበት የፖለቲካ መሳሳት ችግር ላይ መውደቁ ደግሞ ሌላ እውነት ነው፡፡
ህወሓት ፩
የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ደመቀ መኮንን ወደ ስልጣን በመምጣታቸው የህወሓት አመራር የተሰማው ቅሬታ
አልነበረም፡፡ ምክንያቱም የኃይለማርያምም ሆነ የደመቀ ሹመትን የቀመረው ራሱ ህወሓት ነው፡፡ ከዚህም ተነስተን የቅሬታ እና የተፈነገልን
ስሜት የበረታው በመካከለኛና በታችኛው ካድሬ ሰፈር ነው ወደሚል መደምደሚያ እንደርሳለን፡፡ እዚህ ጋ እንደ አይነኬ ነገር ተሸፍኖ
ማለፍ የሌለበት አንድ ጉዳይ አለ፡፡ ይኸውም ጥቂት ሚዲያዎች እንደሚሉት ‹‹የትግራይ ህዝብ ስልጣን ለምን ከትግራይ ሰው ተወስዶ
ለወላይታ ተሰጠ›› የሚል ተቃውሞ የሌለው መሆኑን ነው፡፡ በእርግጥ የዚህ አይነቱ ፍረጃ የትግራይ ህዝብንና ህወሓትን አንድ አድርጎ
ከመመልከት አባዜ የሚመጣ ስለሆነ ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም የጠመንጃው አስተዳደር በኦሮሞ ወይም በአማራ ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣
ትግራይንም የሚጨምር ነውና፡፡ ህወሓት ወላይታን በጊንጥ እየገረፈ፣ ትግራይ ሲደርስ በልምጭ አይቀይረውም፡፡ ወጥ አምባገነን ባህሪይ
የተጠናወተው ነውና፡፡ (ይህንን በህወሓት ውስጥ የተፈጠረውን የተገፋን ስሜት በማጋጋሉ ረገድ ለድርጅቱ የንግስቲቷን ‹‹ሸረሪት›› ያህል
ተፅእኖ ፈጣሪ የነበሩትና በአቶ መለስ የተንገዋለሉት የአቦይ ስብሃት ነጋ እጅ ያለበት ይመስለኛል)
የሆነ ሆኖ ህወሓት በኢህአዴግ ውስጥ ያለውን ተጽእኖ በመጠቀም ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን ህገ-መንግስታዊውን አሰራር ባልተከተለ
መልኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ያደረገው፣ ለካድሬዎቹ ‹‹የሞትንም እኛ፣ ያለንም እኛ! ተረጋጉ›› የሚል መልዕክት
ለማስተላለፍ ሊሆን ይችላል፡፡
ህወሓት ፪
ህወሓት ከመለስ ህልፈት በኋላ በ1993 ዓ.ም. ከድርጅቱ ተባረው ከወጡት አመራር (የእነስዬ፣ ተወልደ ቡድን) ጋር ዕርቅ ፈጥሮ በጋራ
እንዲሰራ ከካድሬውና ከደጋፊው ግፊት እየበረታበት እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ይህ እውነት ከሆነ ደግሞ የህወሓት የመከራ ወራት እየተቃረበ
መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ምክንያቱም የ93ቱ ልዩነት ከድርጅቱ በወጡት የአመራር አባላት እና በአቶ መለስ መካከል ‹‹ለኃይል የበላይነት››
የተደረገውን ትግል ተከትሎ የመጣ እንጂ እንደ ድርጅት የተስተዋለ ወይም በርዕዮተ-ዓለም አለመስማማት የተከሰተ አይደለም፡፡ እናም
አሁን ያለው የህወሐት አመራር ‹‹የመለስን ራዕይ አስቀጥላለሁ›› በሚል ከሚያቀነቅነው መፈክሩ አኳያ ‹‹ከነስዬ ቡድን ጋር ታረቁ››
የሚለው ውትወታ ሲደመርበት ፓርቲውን ቅርቃር ውስጥ ይከተዋል፡፡ መለስ ራሳቸው በክፍፍሉ ወቅት ‹‹ህወሓትን ከአናት ያበሰበሱ››
በሚል የወነጀሏቸውን የአመራር አባላት ወደ ድርጅቱ እንዲመለሱ በማድረግ ‹‹ከመለስ ራዕይ ጋር ወደፊት›› እየተባለለት ካለው ፖለቲካ
ጋር ማስታረቁ የሚቻል ነው ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡
ይህም ሁኔታ በሁለት መንገድ ህወሓት ላይ ተጽእኖ ያሳደረ ይመስላል፡፡ የመጀመሪያው ‹‹አሁን ያለው የህወሓት አመራር አቅም ስለሌለው
ከተባረሩት የቀድሞ አመራር ጋር እርቅ በመፍጠርና ወደ ድርጅቱ እንዲመለሱ በማድረግ አቅሙን ማጠናከር አለበት›› የሚለውን
የካድሬዎቹን ጉትጎታ አልሰማም ማለቱ አስቸጋሪ ስለሚሆን ነው፡፡ በእርግጥ ህወሓት ለዚህ ግፊት ምላሽ ይሆን ዘንድ ደብረጽዮንን ህገ-ወጥ
በሆነ መንገድ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ እንዲይዙ በማድረግ፣ ለሀሳቡ አቀንቃኞች ‹‹ጠንካሮች ነን!! እነስዬ አያስፈልጉንም!!
ባስፈለገን ጊዜ የፈለግነውን ስልጣን መያዝ እንችላለን!!›› የሚል ስውር መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የሹመቱ ህጋዊ አለመሆንም ትንተናውን
በደንብ የሚያጠናክር ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ከኃይለማርያም ጀርባ ያለው ጠንካራ የህወሓት መዳፍ በፈለገ ጊዜ የፈቀደውን ለማድረግ
ህገ-መንግስቱም ሆነ የተቀጥላ ፓርቲዎቹ ፖለቲካዊ ጉልበት ሊያቆመው እንደማይችል ያሳየበት አጋጣሚ ነውና፡፡ (በነገራችን ላይ ሰሞኑን
ለመጀመሪያ ጊዜ እነስዬ የህወሓት ጉባኤን ረግጠው ሲወጡ የሚያሳየው የቪዲዮ ሙሉ ፊልም ‹‹We will never forget this day››
/መቼም የማንረሳው ዕለት/ ከሚል መልዕክት ጋር በተለያዩ ሚዲያዎች እንድናየው መለቀቁ የተፈጠረውን ውጥረት የሚያሳይ
ይመስለኛል)
ሁለተኛው የሹመቱን ፖለቲካዊ አንድምታ የሚያመላክተው ‹‹ከእነ ስዬ ጋር ካልታረቃችሁ ውርድ ከራሴ›› ለሚሉ ካድሬዎች እና
ደጋፊዎች በክፍፍሉ ዘመን፣ ከመለስ ይልቅ ከእነ ስዬ ጎን ቆመው የነበሩትን ደብረጽዮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ ‹‹ከጀርባ
እነሱም ከጎናችን ናቸው›› የሚል ነጠላ ዜማ በመልቀቅ ግፊቱን ለማቀዝቀዝ የተደረገ የሚያስመስሉ ነገሮች መኖራቸው ነው፡፡
(እንደሚታወቀው ደብረጽዮን ከክፍፍሉ በፊት በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ‹‹የመምሪያ ኃላፊ›› የነበሩ ሲሆን፣ ክፍፍሉን ተከትሎ
አሰላለፋቸው ከድርጅቱ ከተወገዱት ጋር በመሆኑ፣ በአቶ መለስ ትዕዛዝ ከሀላፊነታቸው ተነስተው፣ በትግራይ ክልል የአንድ ወረዳ
አስተዳዳሪ ተደርገው መወርወራቸው ይታወሳል፡፡ ሰውዬው የወረደባቸውን ‹‹መዓት›› ችለው ድምፃቸውን በማጥፋት እስከ ዶክትሬት
ዲግሪያቸው ድረስ መማር እንደቻሉና በሂደት ፀባያቸውን አርቀው፣ ግለሂሳቸውን አውርደው፣ በአቶ መለስ የመጨረሻ ዘመን አካባቢ ወደ
ስልጣን ሊመጡ ችለዋል)
ህወሓት ፫
ሶስተኛው የሹመቱ የቢሆን ምልከታ (ሴናሪዮ)፣ አቶ መለስ ህይወታቸው ባለፈ ጊዜ ህወሓትን ችግር ውስጥ የከተተው ጉዳይ ዳግም
እንዳይፈጠር ለመከላከል ታስቦ የተደረገው ነው፡፡ እንደሚታወሰው የሰውየውን መሞት ተከትሎ ህወሐት በህግም ሆነ በአሰራር ቦታውን
ሊወርስ የሚችልበት ምንም አይነት ክፍተት አልነበረውም፡፡ ምክንያቱም ቦታው በቀጥታ የሚገባው ለምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ
ኃ/ማርያም ደሳለኝ ነውና፡፡ ስለዚህም ከዚህ በተወሰደ ትምህርት በቀጣይ እንዲህ አይነት ሁናቴ ቢፈጠር ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፣
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትን መንበር ይዞ መጠባበቅ ለነገ የማይባል የቤት ስራ በመሆኑ ይመስለኛል፣ ደብረጽዮንን በምክትል ጠቅላይ
ሚኒስትርነት ወደ ስልጣን ማምጣት ያስፈለገው፡፡
እዚህ ጋ የሚነሳው ሌላኛው መላ-ምት፣ የህወሓት ዕቅድ ደብረጽዮንን ለድንገቴ ለውጥ ተጠባባቂ እንዲሆኑ አድርጎ አስቀመጠ እንጂ፣
በሚቀጥለው ምርጫ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመጡ ይፈልጋል የሚል አለመሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ህወሓት እንደ አቶ መለስ
አይነት ድንገተኛ ተፈጥሮአዊ አደጋ ካልተፈጠረ በስተቀር፣ ወቅቱን ጠብቆ በሚቀጥለው ጊዜ በሚካሄደው ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትሩን
ቦታ መልሶ ለመያዝ የሚፈልገው በደብረጽዮን በኩል ሳይሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርጎ ባስሾማቸው ቴዎድሮስ አድሀኖም ሊሆን
እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶች አሉ፡፡
ይህንን መከራከሪያ የሚያጠናክርልን ቴዎድሮስ አድሀኖም እስከ አዲሱ ሹመታቸው ጊዜ ድረስ በሰሩበት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር መስሪያ
ቤት የተሻለ የተባለለት ተቋማዊ ለውጥ ያመጡ (በአንፃራዊነት ከሌሎች ተቋማቶች የእርሳቸው የተሻለ እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሮለታል)
ሆነው ሳለ ወደ ሌላ ኃላፊነት መቀየራቸው ነው፡፡ እናም ህወሓት ሹመቱን ሀገሪቱን ለመጥቀም እና የተሻለ ስራ ለመስራት አቅዶ የሰጠው
ቢሆን ኖሮ፣ ሰውዬው በሀላፊነታቸው ቢቀጥሉ ይበልጥ ጠቃሚ መሆናቸውን ከማንም የተሻለ ስለሚያውቅ፣ ልምድ ካካበቱበትና
ውጤታማ ሆነውበታል ከተባለው ሀላፊነታቸው ወደ ማያውቁት አዲስ ስራ ባልቀየራቸውም ነበር፡፡ ይህ ያለአንዳች ቅድመ-ዝግጅት
ድንገት በነሲብ የተደረገም አይመስልም፡፡ ምክንያቱም ብርሃነ ገብርክርስቶስ በትጥቅ ትግሉ ዘመን የህወሓት የውጭ ግንኙነት ሠራተኛ፤
እንዲሁም ከድል በኋላ በአሜሪካ እና በቤልጂዬም አምባሳደር ሆነው ከመስራታቸውም በላይ፣ ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ ምክትል የውጭ
ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው እየሰሩ በመሆናቸው ለቦታው ከቴዎድሮስ በእጅጉ በላቀ ሁኔታ መመጠናቸው ሌላውን ቀርቶ የህወሓትን
ተቀናቃኞቹ ሳይቀር ስለሚያሳምን ኃላፊነቱን ለእርሳቸው ይሰጥ ነበር፡፡
እናም ህወሓት በቀጣይ በምዕራባውያንም ሆነ በበርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ‹‹የተሻሉ›› እንደሆነ የሚነገርላቸውን ቴዎድሮስ አድሀኖምን
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታ ላይ አስቀምጦ፣ ከእጁ ላመለጠው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን እያዘጋጃቸው ይመስላል፡፡ ሬኒ
ሌፎርት የተባለ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የረዥም ጊዜ አጥኚም ‹‹Ethiopia: Meles rules from beyond the grave, but for how
long?›› በተባለ ጽሁፉ ይህንን ሁኔታ ‹‹ኃይለማርያም በህወሓት ዘንድ እንደ ሽግግር ጠቅላይ ሚኒስትር ነው የሚታዩት›› በማለት
አብራርቶታል፡፡ በዚህም ቴዎድሮስ አዳህኖም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ሆነው ‹‹ሰውነታቸውን እያፍታቱ›› ያሉት ህወሓት
የቤት ስራውን አጠናቅቆ ወደ ቤተመንግስቱ እንዲገቡ እስኪያመቻችላቸው ነው የሚለው ሙግት ጠንክሮ የሚወጣ ሆኗል፡፡
በእርግጥ ይህንን አይነቱን ‹‹ቼዝ›› ለመጫወት ብአዴንም የህወሓትን ያህል ምኞት ያለው ይመስለኛል፡፡ ሆኖም ምኞቱ ‹‹ያለጠንካራ
መዳፍ›› ብቻውን የሚፈጥረው ነገር ያለመኖሩ ‹‹እጅ ሰጥቶ›› እንዲቀመጥ ሳያደርገው አልቀረም፡፡ ይህ የህወሓት አቅም በዚሁ የሚቀጥል
ከሆነ፣ ፖለቲካውም በተመሳሳይ መንገድ መጓዙን ይቀጥላል፡፡ …ኢትዮጵያስ በፓርቲው የብረት መዳፍ ስር እስከ መቼ ልትቀጥል ይገባል?

Friday, 21 December 2012

የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት(ከፕ/ር መስፍን ወልደማርያም)

በአለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ እስላም ኢትዮጵያውያን ማካሄድ የጀመሩት ትግል በዓይነቱም፣ በስፋቱም፣ በአስተሳሰቡም፣ በስሜቱም እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአገዛዙ ጋር ከተደረጉ ትግሎች በጣም የተለየ ነው፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትግሉ ለሃይማኖት ነጻነት ነው፤ ስለዚህም በአገዛዙ በኩል የፖሊቲካ ዓላማና የፖሊቲካ መልክ እየተሰጠው ሲሆን በእስልምና ምእመኖቹ በኩል ግን ትግሉን ከፖሊቲካ የጸዳ ለማድረግ ግሩም የሆነና የተሳካ ጥረት እያደረጉ ነው፤ ሁለተኛ የትግሉ ስልት ፍጹም ሰላማዊ በመሆኑ የአገዛዙን የጉልበት ስልት እያከሸፈ ያጋለጠው ይመስላል፤ አንዱና ዋነኛው የትግሉ ሰላማዊነት መግለጫ በቤተ መስጊድ መወሰኑ ነው፤ ይህ ስልት አዲስ አይደለም፤ በብዙ የአረብ አገሮች የሚጠቀሙበት ነው።የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት
ተፋላሚዎቹ ያልተገነዘቡዋቸው አንዳንድ ጉዳዮች ይታዩኛል፤ አንደኛ እስልምና በጎሣ የታጠረ ባለመሆኑ ከወያኔ/ኢሕአዴግ የአመራር መሠረት ጋር የመቃወም ዝንባሌ ያሳያል፤ እስልምና አብዛኛዎቹን፣ በተለይም ትልልቅ የሚባሉትን ጎሣዎች ሁሉ በተለያየ ደረጃ የሚያቅፍ ነው፤ ስለዚህም አንዳንዶች የእስልምና መሪዎች ሌሎች (ማለት – ክርስቲያኑ) አልተቀላቀሉንም እያሉ የሚያላዝኑበትን ቆም ብለው መመርመር ያሻቸዋል፤ ክርስቲያኑ በተለይ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ያሉበትን ሁኔታ በትክክል መረዳት ያስፈልጋል፤ እስላሞች ገና ቀደም ብለው ከብዙ ዓመታት በፊት በተደረገ ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹እስላሞች በጎሣ አይከፋፈሉም›› በማለት የገለጹትን ቁም-ነገር አገዛዙ የረሳው ወይም እስላሞቹ ረስተውታል ብሎ ያሰበ ይመስላል፤ አለዚያ እንዲህ ያለ የከረረ እልህ ውስጥ የገባበትን ምክንያት ለመረዳት ያዳግታል፤ ይቺ ባቄላ ያደገች እንደሆን የሚያሰኝ ነገር ለብዙዎች ሰዎች ምንም አልታየም፤ በጉልበት የማይጨፈለቅ ምንም ነገር የለም ከሚል እምነት ተነሥተው ከሆነ ስሕተቱ እየታየ ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ የእስላሙ ኅብረተሰብ ገና በጠዋቱ በጎሣ የመከፋፈሉን አመራር እንደማይቀበለው በማያጠራጥር መንገድ የገለጠ ይመስለኛል፤ ነገር ግን ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች የጎሣ ትግላቸውን ወደቤተ እግዚአብሔር አምጥተው የተከፋፈሉና የተዘጉም ቤተ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ ይህ የሚያሳፍር ነው፤ ቤተ መስጊዶች እዚህ ደረጃ አልወረዱም፤ እስልምና በጎሣ አይቀደድም፤ እስላሞች ሁሉ የአላህ ልጆች ናቸው፤ በቤተ መስጊድ የሚሰበሰበው ሁሉ በአላህ ልጅነቱ ነው፤ ስለዚህም በመሀከላቸው ልዩነት የለም፤ ይህ የእስላሞች አቅዋም ሃያ ዓመት ተፈተነ፤ የማይበገር ሆነ፤ ስለዚህም ከጎሣ አስተሳሰብ ወጥቶ ሌላ ቀዳዳ መፈለግ ግዴታ ሆነ፤ አል-ሀበሽ አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው።
እስቲ ጉዳዩ ለሁላችንም ግልጽ እንዲሆንልን ወደክርስትና ዞረን እንየው፤ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከነገ ጀምሮ የሉተራን ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ተከተሉ ቢባል አንደኛ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን (ካለች) ምን ትላለች? ሁለተኛ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ምን ይላሉ? ሦስተኛ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 ‹‹መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤›› የሚለው በጤና አለ ወይ? ብሎ መጠየቅ የማይቀር ይሆናል፤ መልሶቹስ ምን ይሆናሉ?
ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ስዒረ ሊቀ ጳጳስ እንደተደረገ አሁን ታወቀ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱም፣ ምእመናኑም፣ ማንም ምንም ያለ የለም፤ የተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ሊቀ ጳጳስ የሻረው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ዛሬ እግዚአብሔር ተገለጠልኝ በማለት ሊቀ ጳጳስዋን የሻረባትን ቤተ ክርስቲያን ትቶ ወደሌላ ተገልብጦአል፤ የተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን አባል በነበረበት ጊዜ የሠራውን ኃጢአት ዛሬ የሌላ ቤተ ክርስቲያን አባል ሆኖ እውነቱን ገልጦልናል፤ ታምራት ላይኔ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ከለቀቀ በኋላ የክርስቶስን ጸሐየ ጽድቅነት መረዳቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚያሳፍር ነው፤ ከዚያም በላይ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን አሁንም እውነቱን አላወጣችም፤ አንድም ለሹመት ያኮበኮበ ጳጳስ የክርስቶስን ጸሐየ ጽድቅነት አምኖና ተቀብሎ እውነቱን ለመናገር የደፈረ አልተሰማም፤ ጴጥሮሳዊነት ከጴጥሮስ ጋር ተቀብሮአል አንበል? ይበልጥ ያሳፍራል፡፡
የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ለንጽጽር አመጣሁ እንጂ ዋናው ነገሬ በእስልምና ሃይማኖት ላይ ነው፤ ድርቅና ቁልጭ ያለው እውነት እስልምና አስፈላጊውን መስዋእት ከፍሎ በሰላማዊ መንገድ ጎሠኛነትን ተቃወመ፤ ተቋቋመ፤ አሁን ደግሞ አንደኛ በእስልምና ምእመናን ላይ እንዲጫን የታቀደውን አዲስ የእስልምና ዓይነት አንቀበልም በማለትና ሁለተኛም የእስልምና ካህናትን የምንመርጠው ራሳችን ምእመናኑ ነን፤ ሦስተኛም የእስልምና ካህናቱ ምርጫ የሚካሄደው በመንፈሳዊ ቦታ በቤተ መስጊድ ነው እንጂ በፖሊቲካ ቦታ በቀበሌ አይደረግም አሉ፤ በጎሣ አንከፋፈልም ብለው ጥንካሬያቸውን ያሳዩትን እስላሞች በሃይማኖት ለመከፋፈልና ካህናቶቻቸውን ራሳቸው በየመስጊዳቸው እንዳይመርጡ መከልከል በግልጽ ሕገ መንግሥቱን መዳፈር ነው።
ሁለተኛው ቁም-ነገር አገዛዙ በየቀበሌው ያካሄደው ከሕዝብ ፈቃድ ውጭ ለሆነ ምርጫ እስላሙ ኅብረተሰብ የሰጠው ሰላማዊ መልስ የማያዳግምና የሚያስደንቅ ነው፤ በአገዛዙ ስልት በተመረጡት ሰዎች በሚተዳደሩ ቤተ መስጊዶች ውስጥ አንሰግድም በማለት መስጊዶቹን ባዶ ማድረጋቸው አገዛዙን ራቁቱን አቁሞ ስሐተቱን ያጋለጠው እውነተኛ ሰላማዊ ትግል ነው፤ በቅርቡ ሦስት የአፍሪካ፣ አንድ የእስያ፣ ሁለት ዓለም-አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ ኃይለ ማርያም ኢትዮጵያ ለዓለም-አቀፍ ሕጎች የገባችውን ቃል ኪዳኖች ሁሉ እንድትጠብቅ ከመቼውም የበለጠ ጥረት ማድረግ እንዳለባት የሚገልጽ ረጅም ደብዳቤ ተልኮላቸዋል፤ ለመብቶቻቸው የቆሙ ሁሉ፣ ጋዜጠኞችም ይሁኑ የሃይማኖት ሰዎች በሽብርተኛነት እየተከሰሱና እየተፈረደባቸው ወህኒ ቤት በመግባታቸው ፍርድ ቤቱንም ወህኒ ቤቱንም ጎብኝተው የሄዱት የስዊድን ጋዜጠኞች በሚያሳፍር ሁኔታ ለዓለም አጋልጠውታል።
የቤቴ መቃጠል ለትኋኑ በጀኝ ያለው ቂል ሰው ነው፤ ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ያለው ሰው ሰነፍ ነው፤ ቂልነትም፣ ስንፍናም ለመሪዎች አይበጅምና እግዚአብሔር በጎ መንፈሱን ያሳድርባቸው፤ ያሳድርብን።

የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥ ማነው?(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

በከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው ለረጅም ዓመት አገልግለዋል፤ ከዚያ ከለቀቁ በሁዋላ በጥብቅና ሙያ እየሰሩ ይገኛሉ። ታዋቂው የህግ ባለሙያ አነጋጋሪ በሆኑ የኢህአዴግ የፈጠራ ክሶች ዙሪያ ለተከሳሾች ጥብቅና በመቆምና በድፍረት በመሙዋገት ይታወቃሉ። በ1997 ከአንድ የፈጠራ ክስ ጋር በተያያዘ ለተከሳሾች ጥብቅና ቆመው ነበር፤ በፌደራል ጠ/ፍ/ቤት በተሰየሙ ዳኛ ተብዬዋች ተግባር ክፉኛ የተበሳጩት እኚህ የህግ ባለሙያ በወቅቱ እንዲህ አሉኝ፥ «በንጉሱ ዘመን ነው፤ በአ.አ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ልንመረቅ ሽር ጉድ እንላለን። የምንወደው የህግ መምህራችን የኛን ሁኔታ ታዝቦ ኖሮ…አንድ ጥያቄ አቀረበልን፤ “ አሁን ሳያችሁ በደስታ እንደተዋጣችሁ ነው፤ በመመረቃችሁ ደስተኛ ናችሁ ማለት ነው?… “ ሁላችንም በጥያቄው ተገርመን ..< እንዴት መምህር?..በጣም ደስተኞች ነን ፤ > አልነው። ደግሞ ጠየቀን ፥ “ሁላችሁም ደስተኞች ናችሁ?”..ሲለን..< አዎን ደስተኞች ነን > አልነው በአንድ ድምፅ። በጣም አዝኖ እንዲህ አለን ፥ < ሕግ በሌለበት አገር ህግ ተምራችሁ ..ሕግ የምታስፈፅሙ ይመስል፥ እንዲህ መደሰታችሁና መመፃደቃችሁ ታሳዝናላችሁ.!>… ዛሬ የበለጠ የመምህራችን ንግግር ታወሰኝ፤ እውነትም ሕግ በሌለበት አገር…»ሲሉ ታዋቂው የህግ ባለሙያ ያወጉኝን ለመጣጥፌ መንደርደሪያ ማስቀደሜ ያለምክንያት አይደለም።

                        ጠ/ሚ/ር ተብለው የተቀመጡት ሃ/ማሪያም ደሳለኝ የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነቱ ስልጣን አልተቀበሉም። ቀደም ሲል ይህ ስልጣን በአቶ መለስ እጅ ነበር። እንዲያውም የከፍተኛ ጄኔራሎች ሹመት በተመለከተ ቀደም ሲል የነበረውን ሕግ በመሻር ስልጣኑን ጠቅልለው የያዙት አቶ መለስ ነበሩ። ይህ የተደረገው ከ1993ዓ.ም ወዲህ ነበር፤ ከዚያ በፊት ግን የጦር አዛዦችን ሹመት የሚያቀርበው ጠ/ሚኒስትሩ ሲሆን የሚያፀድቀውና የሚሽረው ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ነበር። ፕ/ት ነጋሶ ከስልጣን ለመልቀቅ የወሰኑበት አንዱ ምክንያት ይህው ነበር። ከሳቸው እውቅና ውጭ ጠ/ሚ/ሩ ጄኔራሎችን በማባረራቸው እንደነበር ይታወሳል። ከዛ በሁዋላ አቶ መለስ ስልጣኑ ሙሉ በሙሉ የጠ/ሚ/ሩ እንዲሆን የሚያስችል ህግ አውጥተው አረፉት። የሚሽሩትም የሚሾሙትም እርሳቸው ሆኑ።

ባለፈው ጊዜ ጠ/ሚ/ር ሳይኖር 34 ጄኔራሎች መሾማቸው ተነገረ፤ አስገራሚና አነጋጋሪነቱ እንዳለ ሆኖ ለዚህ የተሰጠው መልስ ይበልጥ አስቂኝ ነበር። «ቀደም ሲል በጠ/ሚ/ሩ የተዘጋጀ ነው» ብለው በረከት ተናገሩ። ከተሾሙት መካከል መለስ ለሹመት ለአፍታ ሊያስቡዋቸው የማይችሉ መኮንኖች መኖራቸው የበረከት መልስ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ታዛቢዋች በወቅቱ አስተያየት የሰጡበት ነው።

አሁን ደግሞ « የጦር ሃይሎች አዛዡ ማነው?» ተብሎ ቢጠየቅ መልስ የለም። ሕጉን እንቀበል ቢባል እንኩዋን ስልጣኑ በጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም እጅ አይደለም። አሁን አገሪቱዋን የሚመራው የጦር ሃይሉ ጠ/አዛዥ ማነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳ ተጨባጭ መልስ መስጠት አይቻልም። ስልጣኑ በዘፈቀደ የተለያዩ የሕወሓት ጄኔራሎች እና ባለስልጣናት እንዲሁም ከመጋረጃው ጀርባ ባደፈጡ የድርጅቱ ባለስልጣናት እጅ እየተሽከረከረ እንዳለ መረጃዋች ይጠቁማሉ። ለመጥቀስ ካስፈለገ ባለፈው ወር በሳሞራ ቀጭን የስልክ ትዕዛዝ የተነሱት ጄኔራል…በአስገራሚ ሁኔታ እንዲመለሱ የተደረገው ከጀርባ ሆነው አንድ ቡድን በሚያሽከረክሩት ስብሃት ነጋ እንዲሁም ሌሎች ተከታዮቻቸው ርብርብ ነው። በተነሱት ጄ/ል የተተኩት እንዲነሱ የተደረገውም በዚሁ ቡድን ጣልቃ ገብና ሕገ-ወጥ ውሳኔ ነው። ሕግ፡አዋጅ…የሚባል ጨርሶ አይሰራም!! ከዚህ በተጨማሪ 3 ጄኔራሎችን ጨምሮ በርካታ የበታች መኮንኖች ታግደው..ውሳኔ እየጠበቁ ነው፤ ከታገዱት ከኦህዴድ ወገን ይበዛሉ። ይህ ሁሉ እየተደረገ ያለው በጄ/ል ሳሞራና ከሳቸው ጋር በተሰለፉ የቡድን አባላት ሲሆን በተቃራኒ ያለው ቡድንም የራሱን የማባረርና የማስመለስ ድራማውን ገፍቶበታል።

ይህ ሁሉ የሚከወነው የሃ/ማሪያምን በአዋጅ የተቀመጠ ስልጣን በአደባባይ በጡንቻ በመውሰድ ወይም በመግፈፍ ነው። ጠ/ሚ/ሩ < ለምን?..እንዴት.. ከኔ እውቅና ውጭ..? > ብለው ለመጠየቅ ይቅርና የሚያስቡት አይመስልም። አይተው እንዳላዩ መሆንን መርጠዋል። ከዚህ ይልቅ የመለስን «ካባ» አጥልቀው « ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አስመራ ሄጄም ቢሆን እነጋገራለው፤ እደራደራለው» ማለቱን ተያይዘውታል። ይህም ቢሆን የርሳቸው ውሳኔ ሳይሆን ከጀርባ ያለው ሃይል የቆየ ፍላጐትና እመነት ነው። ብዙ ወገኖችን ያስገረመው ጉዳይ ባለስልጣናቱ ለሻዕቢያ ባለስልጣናት የሚያቀርቡት ልምምጥ የሚታይበት የድርድር ጥያቄና ተማፅኖ፥ በአገር ውስጥና በውጭ ላሉ ተቃዋሚዎች ለአንድ አፍታ ሊቀርብ ቀርቶ ያለመታሰቡ ነው። ከዚህ ይልቅ «ድርድር አይታሰብም» ከሚለው አንስቶ..«የሻዕቢያ ተላላኪዎች፡ ፀረ-ሰላም ሃይሎች..አሸባሪዎች..» የሚል ያልተጨበጠ ታርጋ እየለጠፉ መወንጀል፡ መዝለፍና እስር ቤት መወርወርን ስራዬ ብለው የገፉበት ተጨባጭ እውነታ ነው የሚታየው። የገዢዎቹ ሃሳብና ድርጊት እንደሚጋጭ የሚሳየው « ሻዕብያን ፀረ ሰላም ሃይሎችን በዋና አዛዥነት የሚመራና የሚያሰማራ..»እያሉ እየፈረጁ፥ በአንፃሩ ለሻዕብያ የድርድር ጥያቄ አቅራቢዎች ደግሞ እራሳቸው መሆናቸው ብዙዎችን ያስገረመ ሆኖዋል። ሲጠቃለል፥ ኢህአዴግ ራሱ ላወጣውና ለሚመፃደቅበት «ሕገ መንግስትና አዋጅ» ተገዢ መሆን አልቻለም። ይባስ ብሎ ሁሉም አዛዥና ፈላጭ ቆራጭ ሆኖዋል። የአቶ ሃ/ማሪያም ስልጣንና ሚና ውሉ አልለየም። የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ዋና አዛዥ ከአገሪቱ ቁልፍ ስልጣኖች ዋናው ነው። ማን ጋር ነው? የሚለውን ጥያቄ ከላይ ለማመላከት ተሞክሮዋል። ጥያቄው ግን አሁንም መነሳቱ ይቀጥላል። ጠ/ሚ/ሩ አውቀው ተኝተዋል። ይህ ስልጣን በየፊናው የሚያዝበት ስለበዛ..ወዴት ሊወስድ ይችላል?..የሚለው ለመገመት አያዳግትም። እየታየ ያለውም ይህንኑ ግምት የሚያጠናክር ነው!!