Monday, 24 September 2012

ቅኝቱን ያልሳተው አዲሱ ሹመት ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን)

2004 ዓ.ም ሃገራችን ብርቅዬና በሞያቸው አንቱ የተባሉ እንዲሁም ለሃገራቸው ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ እጅግ ውድ ልጆችዋን እንዳጣች ሁሉ በስተመጨረሻው አዲሱ አመት ከመጥባቱ በፊት እንደ መጅገር ተጣብቀው የህዝብና የአገር ደም ሲመጡ፣ ሃብት ንብረትዋን ሲመዘብሩ የነበሩት እስከ እኩይ ምግባራቸው ላይነቁ እስከ ወዲያኛው ማሸለባቸው የታወሳል፡፡ በማለቂያው እነዚህን እኩይዎች ነቀለልን እንጂ በመለስና በሰርዓቱ ሃገርና ህዝብ ሲታመሱ ነው  አሮጌው ዘመን ያለቀው፡፡ ዘመኑን ሙሉ እሱና ጀሌዎቹ ያረቀቁትን የአገሪቱን ህገ-መንግስት  አክብሮ ማስከበር እርም ሆኖባቸው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን  ተጠቅመው የተደራጁ የድርጅት አመራሮችን እንዲሁም የመፃፍና የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ስለዴሞክራሲ፣ ስለፍትህ፣ ስለመልካም አስተዳደር እጦት የፃፉትንና ሌሎችንም ንፁሃን ዜጎች ሰብስቦ የተለመድው ማጎሪያ የወረወራቸው ዘረኛው መለስ ጀምሮ ባልጨረሰው 2004 ዓ.ም መጀመሪያ ነበር፡፡ ይህ አመት በኢትዮጲያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በርከት ያሉ ትህይንቶች የተስተናግዱብተ አመት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ’’ከሁሉም በፊት ነፃነትና ዴሞክራሲ ለዜጎች መልካም አስተዳደር፣ ፍትህና እኩልነት በሃገሪቱ ይስፈን፣ ህዝብ በተለይ ወጣቱ የአባቶቹን አደራ ይጠብቅ እያለ በመጨረሻም በቃኝ ፍትህ፣ እኩልነትና ነፃነት በሌለበት ሃገር አልኖርም ’’ ብሎ በራሱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን ያቃጠለው ሰመዓቱ የኔሰው ገብሬ በመለስ እና በጭፍሮቹ እንደ አእምሮ በሽተኛ የተቆጠረው በዚሁ በሸኘነው አመት ወርሀ ህዳር ነበር፡፡ ሌላው በዚህ ጉደኛ አመት ከተደረጉ ህዝባዊ እንቅሰቃሴዎች ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ያነሱት የደሞዝ ጭማሪና ተዛማጅ ጥያቄ በአትሌት ሃይሌና በአምባገነኑ መለስ በጥቂት ተፈርጆ ቢፌዝበትም የአንድ ስሞን አንኳር የሃገሪቱ መነጋግሪያ ጉዳይ ሆኖ አልፏል፡፡ ሌላው ምንም እንኳን በአፋኙ ስርዓት መልስ ባያገኝም የአምባገነኑን መንደር አስጨንቆና ፋታ ነስቶ እስካሁን ሲንከባለል ዘመን የተሻገረው የሙሰሊሙ ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ ለሟቹ ዘረኛው መለስም ሆነ ለቀሩት የስርዓቱ ጭፍሮች ትልቅ እራስ ምታት እንደሆነ እስካሁን ዘልቋል፡፡ በዚህም የሙስሊም ማህበረሰብ ባነሳው የመብት ጥያቄ ምክንያት ብዙ ወገኖቻችን በግፈኛው የመለስ ብድን በግፍ ተገለዋል፣ አካላቸውን አጠተዋል፣ ታሰረዋል፡፡ ከወራት በፊት በአርሲ አሳሳ የተካሄደው ጭፍጨፋ ፣ በደሴ የተደረገው የግፍ ብትር ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ በዘመኑ መጨረሻ እንደ አበደ ውሻ ሁሉንም ይነክስ የነበረው መለስ ዜናዊ መጀመሪያ በጀግናው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከዛም በመለአከ ሞት እስከተሸነፈ ጊዜ ደረስ የሚይዝ የሚጨብጠው እስኪያጣ እጅግ በገዘፈ መልኩ የአውሬነት ባህሪ ይስተዋልበት ነበር፡፡ ለዚህም ነው ለዘመናት ተከብሮ የኖረውን የዋልድባ ታሪካዊ ገዳም በልማት ስም እንዲታረስና አለም በቃን ብለው የመነኑ መነኮሳትመጠጊያና መሸሸጊያ እስኪያጡ የሳደዳቸው፡፡ በመሰረቱ ይህ ገዳም የሁሉም ኢትዮጲያዊያን፣ የጳጳሳት፣ የመምህራን፣ የመነኮሳት፣ የዘማሪያን መሰረት ከመሆኑም ባሻገር የሃይማኖት መገለጫ፣ በማንነታችን መኩሪያና ማሳያ፣ የታሪካችን አሻራ ከመሆኑም ባሻገር የተለያዩ የቅዱሳን ገድል ያለባቸው በርካታ መፅሃፍትንና የተለያዩ የኢትዮጲያ ሃገራችን ቅርሶች ያሉበት ገዳም ፣ ከተውልድ ትውልድ ሲወራረስ የመጣውንና የበቁ አባቶች ፀሎትና ምልጃ የማይለየውን ይህንን ቅዱስ ቦታ በልማት ስም የተተናኮለው በመጨረሻው የጣር ሰአቱ ነበር፡፡

ቅኝቱን ያልሳተው አዲሱ ሹመት ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን) 21/09/2012
በተጨማሪም በዚሁ ባሳለፈነው አመት በደቡብ ኢትዮጲያ በጉራ ፈርዳ ለአመታት የኖሩ የአማራ ተወላጆች ከነቤተሰቦቻቸው በሃገራቸው የመኖር መብታቸው ተቀምተው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው ሃብት ንብረታቸውን ተነጥቀው እንደ ዘበት ’’አገራችሁ ሂዱ’’የተባሉት የዴሞክራሲ እና የፍትህ አባት እየተባለ የሚዘመርለት መለስ ዜናዊ አውቆ እና ፈቅዶ ነው ፡፡ ይህም ያሳለፍነው አመት አንድ ትእይንት ሆኖ አልፏል ፡፡ በሌላም በኩል መለስና ግብራበሮቹ በቃኝን የማያውቁ በመሆናቸው የሃገርና የህዝብን ሃብት እንደ ግል ንብረታቸው ከመቀራመትም ባለፈ ደሃ በመሆናችን በኛው ስም ለምነው ካገኙት ገንዝብ ላይ ሁሉ ይስረቃሉ፡፡ የዓለም የፋይናንስ ኢቴግሪቲ (Global financial integrity) ባደረገው ጥናት መሰረት እንደ እ.አ.አ ከ2000 እስከ 2009 ባለው 9 አመታት ውስጥ 11.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጲያ በህገወጥ መንገድ ተዘርፎ ከሃገር መውጣቱን ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ይህ ገንዘብ በኢትዮጲያ ሲመታ ምን ያህል ነው? ምንስ ሊሰራ ይችል ነበር በላችሁ በማሰብ አትታመሙ፡፡ በአጠቃላይ ወያኔ ላለፉት ሃያ አንድ አመታት ሰራሁ የሚለንን መንገድ፣ አነፅኩ የሚለንን ህንፃ ፣ ገነባሁ የሚላቸውን ማንኛውንም ግንባታዎች ከሶስት እጥፍ በላይ ሊከውን የሚችል ገንዘብ በሟቹ መለስና በዙሪያው ባሉ የወያኔ ሰወች እንደተመዘበረ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ከላይ ለመጠቆም የሞከረኩት ሁሉ ለአንድ ሚሊዮን ጊዜ በተለያዩ ሁኔታዎች የተነገሩና ሁሉም ስው የሚያቀው እውነታ ነው፡፡ ታዲያ እነኚህንና የተቀሩትን የዘረኛው መለስ ገድሎች ከሞተም በሗላ ሲሰርቅ አብረው በሰረቁት፣ ሲገድል ተማክረው በገደሉት፣ ፍትህ ሲያጎድል እና ንፁሃን ዜጎችን በግፍ፣ በሃይል ሲረግጥ ብርጭቆ እያጋጩ ደስታቸውን በገለፁ፣ የሴራው ተባባሪ በሆኑት ሁሉ ወይም በእሱ ብልሹ አሰራር ተለጣፊ ሆነው ኑሮአቸውን ያደራጁ፣ የመለስን ጩኸት ሲያስተጋቡ የነበሩ በቀቀኖች ጌታቸውን የሚያንቆለጳጰሱበት ቃላት አጥሮአቸው ተቸግረዋል፡፡ስንት ንፁሃን ዜጎች በየእስር ቤቱ ያጎረውን ሰውዬ…. የፍትህ እና የዴሞክራሲ ተሟጋች፣ ሃገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ የሸጠ እና እጅ መንሻ የሰጠውን…. ባለ ህራህይ፣ ለሃገር አሳቢ አርገው ሲስሉት እጀጉን የደንቃል፡፡ መለሰ የፍትህ እና የዴሞክራሲ አባት ከሆነ አሁን በሚነገርለት መጠን የዜጎችን መብት ያከበረና ያስከበረ ከነበረ የሽብሬ እና የነበዩ መገደል ትክክል ነበር ማለት ነው?፣ እስክንድር እና አንዱአለም እንዲሁም ሌሎች ንፁሃን ዜጎች በእስር መማቀቃቸውስ አግባብ ነው? መቼም ይህንን ለማወቅ ጠቢብ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ በመሰረቱ በአለም ላይ ከብዙሃኑ በተሻለ አስተሳሰብ ያለው ሰው ለመሆን ሁለት አማራጮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው እና ከባዱ የተሻለ ከሚያሰቡ ሰወች የተሻለ ሆኖ መገኘት ሲሆን ሁለተኛው እና በጣም ቀላሉ ደግሞ ደደቦችን በዙሪያህ በመሰብሰብ የተሻለ ሆኖ መታየት ነው፡፡ እናም በኔ አመለካከት ሟች መለስ ሁለተኛውን አማራጭ ተክኖበታል ለዚህ ነው ያልፈጠረበትን ያልሰራውን ገድል እየተረኩ በማህበር ተደራጅተው በደቦ አልቅሰው ሲያላቅሱ የከረሙት፡፡ ለዚህ ነው ሃገር ምድሩን ማቅ አሰለብሰው የለቅሶ ከተት አወጁት፡፡የመለስን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ የግፍና የአፈና ስርዓትን የሚያወድስ ወይም አርአያ አድርጎ የሚከተል ቅኝቱን ያልሳተ አዲሱ ሹመት የተሻለ ነገር ይዞ ይመጣል ማለት ከንቱ ቅዠት ነው፡፡ መለሰ በዘረጋው የዘረኝነትና የጥላቻ ሀዲድ ሊዘውሩን እንሆ አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝ ነግሰውብናል፡፡ በቃን ካላልን አሁንም ሊገዙን ሽርጉድ የሚሉት ያው የሟቹ መለስ ቅጥቅጦች ናቸው፡ ጉልቻ ቢለወጥ ነው ነገሩ . . . . . . . . . ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ ሞት ለወያኔ ለአሰተያየቶ፣-ftih_lewegen@yahoo.com

Sunday, 23 September 2012

የሞቱት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ቢሆኑስ ኖሮ? በሕግ አምላክ (ከስዊድን)

አቶ መለስ ዜናዊ Meles Zenawiሰው ሆኖ መኖር፣ ኖሮ - ኖሮ መሞት አይቀርም። ቢሆንም ገና በህይወት ያለ ሰውን ቢሞት ኖሮስ ብሎ የቀብር ስነሥርዓቱን መግለጽ በባህላችን አልተለመደም። ስለዚህም በርዕስ ምርጫዬ ኮሎኔል መንግሥቱ ቤተሰቦቻውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው እንደማይቀየሙኝ ተስፋ አደርጋለሁ። በርካታ ሰዎች በምስል አቅርቦትና በድምፅ ቀርፃ ያዩትንና የሰሙትን አስመልክቶ የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነሥርዓት እፁብ ድንቅና ወደርየለሽ ነው ይላሉ። እኔ ግን ወደርየለሽ የሚለውን አባባል አልጋራቸውም። ምክንያቱም ...

ሰው ሆኖ መኖር፣ ኖሮ - ኖሮ መሞት አይቀርም። ቢሆንም ገና በህይወት ያለ ሰውን ቢሞት ኖሮስ ብሎ የቀብር ስነሥርዓቱን መግለጽ በባህላችን አልተለመደም። ስለዚህም በርዕስ ምርጫዬ ኮሎኔል መንግሥቱ ቤተሰቦቻውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው እንደማይቀየሙኝ ተስፋ አደርጋለሁ። በርካታ ሰዎች በምስል አቅርቦትና በድምፅ ቀርፃ ያዩትንና የሰሙትን አስመልክቶ የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነሥርዓት እፁብ ድንቅና ወደርየለሽ ነው ይላሉ። እኔ ግን ወደርየለሽ የሚለውን አባባል አልጋራቸውም። ምክንያቱም ...

ምክንያቱም የአቶ መለስ የቀብር አሸኛኘትና አፈጻጸም ወደር የማይገኝለት ነው ሊባል የሚችለው ከየትኛው መሪ የቀብር ስነሥርዓት ጋር ተወዳድሮ ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳ አባባሉን ኢተዓማኒ ያደርገዋልና። ለዚህም ነው የሞቱት ኮሎኔል መንግሥቱ ቢሆኑ ኖሮስ ምን ዓይነት ትዕይንተ ሕዝብ ይታይ ነበር? የሚለውን ግምታዊ አስተሳሰብ በዓይነ ህሊና ለማሳየት የምሞክረው።

በቅድሚያ ግን የአቶ መለስ ዜናዊ እልፈተ ህይወትን ምክንያት በማድረግ ወያኔ (ኢህአዲግ) ለዓለም ሕዝብ ሊያሳይ የፈለገው ትዕይንተ ሕዝብ አሁንም የሕዝብ ንቀትን አመላካች ክንውን መሆኑን ማስመር እፈልጋለሁ። ህወሓትና አጫፋሪዎቹ አባቱን በድንገት እንዳጣ ህጻን ልጅ ”አባቴ! አባቴ!” ብለው እያለቀሱ የሸኙትን ያህል በውስጣዊ ሳቅ የተሰናበቱትም ያንኑ ያህል በርካቶች ናቸው። በለቅሶም በሳቅም ያልኩበት ምክንያት አለኝ። ሁሉንም ነገር አንተ እንዳልክ፣ ካንተ ወዲያ ለኢትዮጵያ፣ ካንተ ወዲያ ለእኩልነትና ለነፃነት ተሟጋች፣ የለም እያሉ በጨለምተኝነት ”አምላኪ መለስ” የነበሩት ቀቢፀ ተስፈኞች አዎ በእጅጉ አዝነዋል። እናም ከልብ አልቅሰው ተሰናብተዋል።

አንድነት፣ እኩልነት፣ ነፃ ምርጫ፣ ... ወዘተ የሚባለውን ስንክሳር ተዉትና በማናቸውም ሲስተም ገብታችሁ መዝረፍ ትችላላችሁ ተብለው አንድ ሺህ ብር ቆጥረው የማያውቁት ቢልዮን ብር በባንክ፣ ሚልዮን የኪስ ገንዘብ የያዙት አግበስባሾችም በእጅጉ አዝነዋል፣ እናም በደንብና በሥርዓት አልቅሰዋል። እነዚህኞቹ ዕንባ አይደለም ቢቻል ደምም ቢያለቅሱ አይወጣላቸውም። ስለዚህም ምርር፣ ስቅስቅ ብለው አልቅሰዋል። ከትግሬ መወለድ ልዩ ፍጥረትና ልዩ ክብር እንዳለው በአደባባይ ላይ በትዕቢትና በትምክኽተኛነት በመነገሩ የትናንቱን ኑሯቸውን ምንም ባይለውጠውም በትግሬነታቸው ብቻ ዘራፍ ሲሉ የነበሩትም ከሌሎች እኩል አልቅሰው ቀብረዋል። እነዚህኞቹ ደግሞ ምንም አላገኙ፤ ምንም አላጡ፣ ነገር ግን መለስ በመሞታቸው ሁሉም ጣቱን የሚቀስርባቸው እየመሰላቸው በሥነልቡና ፍርሃት ተሸማቀው በዕንባ ሲራጩ ተስተውለዋል። በአንፃሩም መሬቱ ይቅለላቸውና አቶ መለስ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ ግማሽ ልባቸው ወደ ኤርትራ፣ ግማሽ ልባቸው ወደ ትግራይ፣ የሥልጣን ልባቸው ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ተከፋፍሎ ሚዛናዊ ዳኝነታቸው ተዛብቶባቸዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያዊነት ደብዛን ለማጥፋት በፈፀሙት ብሔራዊ ስህተቶች አንጀቱ ሲቃጠል የነበረው፤ ነገር ግን ውጣና ቅበር የተባለው ህዝብም በእውን እያለቀሰ ከማለት በውስጡ እየሳቀ ሸኛቸው ቢባል ከእውነታው የራቀ አይሆንም። ምክንያቱም ሰው እንዲያለቅስም እንዲስቅም የሚያነሳሳው ኑሮው ነውና።

በሌላ መልኩ የአቶ መለስ ተለዋዋጭ ባህሪም ከአንድ መንግሥትና ፓርቲ መሪነት ወደ ሁለንተናነት እየተለወጠ በመምጣቱ ሁሉንም ነገር እርሳቸውና እርሳቸው ብቻ የሚያቅዱና የሚወስኑ በመሆናቸው ከአመራር ውጪ ሆኖ በጀሌነት አብሯቸው የነበረው ባለሥልጣን ሳይቀር ላይ ላዩን በጥቁር ልብስ ተዠብኖ ቢታይም ውስጡ ግን ”አብዝቶት ነበር ይበቃዋል!” በሚል በአዲስ ተስፋ ተሰናብቷቸዋል። ወጣም ወረደ አቶ መለስ ዜናዊ አስከሬናቸው ከቤተ መንግሥት በክብር ወጥቶ በሕዝባዊ አጀብ የተቀበሩ የዘመናችን መሪ በመሆናቸው በዚህ ዕድለኛ ናቸው። በዚህ ምክንያትም ቀብራቸው ዕፁብ ድንቅ በሚባል ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ ተፈጽሟል። ነገር ግን የርሳቸውን ሥርዓተ ቀብር ወደር የማይገኝለት ለማለት ለሌላ መሪ የተደረገውን ወይንም ሊደረግ የሚችለውን ሥርዓት መቃኘት ንፅፅሩን ሚዛናዊ ያደርገዋል። ለዚህም ነው የሞቱት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ቢሆኑስ ኖሮ? ያልኩት። ለመሆኑ እኒህ ሰው በበትረ ሥልጣናቸው ላይ እያሉ ቢሞቱ ኖሮ ደርግ (ኢሠፓ) ምን ምን በማለት አጅቦና አዝኖ ቀብራቸውን ያስፈጽም ነበር?

”ውድ ጓድ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም፣
የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ፣
የኢህዲሪ ፕሬዘዳንትና የአብዮታዊ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣
  • • ሲወርድ ሲዋረድ የቆየውን የኢትዮጵያን አንድነትና ዳር ድንበር አስከብሮ ለማቆየት በየማዕዘኑ ከተነሱ ጠላቶች ጋር የተደረገውን ፍልሚያ የመሩ የጦር መሪያችን፣
  • • በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲፈጠሩና ህዝቡ እንዲነቃ፣ እንዲደራጅና እንዲታጠቅ ያስቻሉ አሻግሮ ተመልካች፣
  • በገባርና በጢሰኛ መካከል ተንሰራፍቶ የነበረውን ኋላ ቀር ግንኙነት በጥሰው መሬት ለአራሹ ያደረጉ የድሃው ገበሬ አባት፣
  • የሶማሊያ ተስፋፊ ጦርነትን “እናት ሀገርህ ተደፍራለች! ተነስ፣ ታጠቅ፣ ዝመት፣ ...” በሚል ብሔራዊ ጥሪ ሕዝባዊ ሠራዊትና መደበኛ ጦር በማዝመት ድል መትተው የሀገር ክብርና ዳር ድንበርን ያስከበሩ የጦር አዝማችና መሪያችን፣
  • የውበት ፈርጣችን የሆኑትና በአንድነትና በፍቅር ተሳስረው የሚኖሩ ልዩ ልዩ ብሔረሰቦች እንዲታወቁ፣ እንዲጠኑና መብታቸውም እንዲከበር የሚያስችል የብሔረሰቦች ኢንስቲትዩትን ያቋቋሙ የእኩልነት በር ከፋች፣
  • በሕዝብ የመኖሪያ አቅራቢያዎች የመሠረታዊ ሸቀጦች ማከፋፈያንና የፍትሕ አካላትን (ፍርድ ሸንጎ) አቋቁመው የነጋዴ ብዝበዛንና የፍርድ ቤት ውጣውረድን ያስቆሙ ተቆርቋሪ ዜጋ፣
  • መኃይምነትን በማጥፋት ዘመቻ ዓለም አቀፍ አድናቆትን ያተረፉ አስተማሪያችን፣
  • ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ የመገናኛ አውታሮችንና አስተዳደራዊ ልማቶችን በሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት በአቻነት ያስፋፉ የልማት መሐንዲሳችን፣
  • የኢትዮጵያን ታሪካዊና ዙርያ ክብ ጠላቶች ለመመከት የሚያስችልና ምዕራባውያንን በከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለ የመከላከያ ኃይል የገነቡ የዘመናችን አፄ ቴዎድሮስ፣ … ወዘተ … ወዘተ …"

እየተባለ አሁን አቶ መለስን ለመሰናበትና ለመቅበር በደብዳቤ ጋጋታ ከወጣው የስም እዝንተኛ በእጅጉ የላቀ ትዕይንተ ሕዝብ በታየ ነበር። ለዚህ ነው ወደር የማይገኝለት የቀበር ስነሥርዓት ለማለት ከማን ጋር ተነፃፅሮ በማለት የጠየቅሁት።

አቶ መለስ ዜናዊ እንደማናቸውም ሰው በአንድ የታሪክ አጋጣሚ የሀገር መሪነት ሥልጣን ጨብጠዋል። እንደማንኛውም መሪም ጠንካራና ደካማ ጎኖች ታይተውባቸዋል። በመሪነት ዘመናቸው አፍላ ምዕራፍ ላይ በመደራጀት መብት፣ በነፃ ፕሬስ፣ በነፃ መሰብሰብና በመሳሰሉት በተለይም በ1997 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2005) ቅድመ ምርጫ ወቅት ተስፋ ሰጭና በጎ ጅምሮች ቢታዩም ውለው አድረው ብሔራዊ ኃላፊነት በጎደለው ትዕቢት የፈፀሟቸው የታሪክ ጠባሳዎች እጅግ በርካቶች ናቸው። እናም እንደዚህ ማለት ይቻላል፣

አቶ መለስ ዜናዊ፣
የኢፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣
የኢህዲግ ሊቀመንበርና የጦሩ የበላይ አዛዥ፣
  • የቆየውን የኢትዮጵያውያን አብሮነትና ብሔራዊ ስሜት በጎሣ ፖለቲካ ተክተው በተጋድሎ አንድነቷ ተጠብቆ የቆየችው ሀገር እንድትበጣጠስና ለእርስ በርስ ጦርነትም እንድትመቻች፣ የመከፋፈልና የመፈራረስ የመሰረት ድንጋይ የሆነውን ሕገ መንግሥት አውጥተው ያፀደቁ ናቸው።
  • የኢትዮጵያን የባህር ወደብ ለሻዕቢያ እጅ መንሻ ከመስጠት አልፎ መጠነ ሰፊ የሀገሪቱ አካል ተቆርሶ ለኤርትራ እንዲሰጥ በጥፋት የስምምነት ፊርማቸው ያጸደቁ መሪ ናቸው።
  • በህይወት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለሱዳን ምንደኞች በመስጠት የክልሉን ገብሬ ያፈናቀሉና ብሔራዊ ክብር ያሳጡ ግድየለሽ ናቸው።
  • ትጥቅ አልባ ተቃዋሚ ሠልፈኞችን በቅልብ ጦራቸው ያስረሸኑና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ተለጣፊ ስም በመስጠት በእስር እንዲሰቃዩ አመራር የሰጡ የሰብዓዊ መብት ረጋጭ አምባገነን ናቸው።
  • ዛሬ በሚታየው የሰለጠነ ፖለቲካ ሥርዓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያላቸውን አማራጭ ለህዝብ አቅርቦ በማስወሰን ፈንታ የተቃዋሚዎችን ጽ/ቤት በመዝጋት፣ መሪዎችን በመግደልና በማሰር የሕዝብ ድምጽን በገሀድ በመዝረፍ ሥልጣንን በብቸኝነት ይዘው ዲሞክራሲን ያፈኑ የስም መሪ ናቸው።
  • ለውጤት የማይነሳሳ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያደርግ የትምህርት ፖሊሲ በማውጣትና የሥራ ዕድል ባለመፍጠር ተስፋ የቆረጠና ችግር መፍታት የማይችል ትውልድ እንዲበራከት ያደረጉ ምሁር አምካኝ መሪ ናቸው።
  • ለዘመናት የብዙኀን ተቆርቋሪ ዜጎች ጥያቄ የነበረው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ተቀልብሶ የገጠር መሬት ለህወሓት/ኢህአዲግ የፖለቲካ መሣሪያነት እንዲውል ለማድረግ በመንግሥት ቁጥጥር ስር አውለው ገበሬውን ማዕከል አድርገናል በሚሉት ፍልስፍና የኢትዮጵያ ገበሬን የመሬት ባለቤትነት ያሳጡና ኑሮውን እያፈናቀሉ ለድንበር ዘለል ከበርቴዎች የሸጡት ናቸው።
  • በኦሮሞ፣ በኦጋዴን፣ በጋምቤላና በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች በተወርዋሪ ጦራቸው በአንድ ብሔረሰብ አባላት ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ያካሄዱና በዘር ማጥፋት ወንጀል መጠየቅ የነበረባቸው ወንጀለኛ ናቸው።

አቶ መለስ ዜናዊ እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ እጅግ በርካታ ብሔራዊ ጥፋቶች ፈጽመው አልፈዋል። መሬት ይቅለላቸው እንጂ በፌደራልና በክልል ሥልጣን ስም፣ በዲሞክራሲና በነፃ ምርጫ ስም፣ በነፃ ፕሬስና በብዙኀን ፓርቲ ስም በአጠቃላይ በማይተገበር ሕገ መንግሥት ስም ጥቂቶች ብዙኀኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር ከፋፍለው ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አፍነው የዲሞክራሲያዊ ግንባታውን ቀልብሰውታል።

አገራዊ - አገራዊ፣ ብሔራዊ - ብሔራዊ የሚሸተው የአብሮነት መዓዛ ተበርዞና ጠፍቶ ክልላዊ - ክልላዊ እንዲሸትና በአንድ ሀገር ሕዝቦች መካከል የነበረውን የአብሮነት ታሪክና ባህል በጎሣ ፖለቲካ መርዘውታል።

አቶ መለስ ዜናዊ ታላቅ ክብርና ሞገስ ያለው የኢትዮጵያዊነት ካባ አልሻም ብለው በትግሬነት ሰደርያቸው የተመፃደቁና ራሳቸውን ከብሔራዊ ክብር ወደ መንደር ያወረዱ፣ ቂም በቀል ከደም ሥራቸው ጋር የተሳሰረ፣ ጥላቻ፣ ፍርሃትና ተጠራጣሪነት ተደራርበው ዕረፍት ስላሳጧቸው ለዕልፈት በቅተዋል።

የሞተን አልቅሶ ወይም ሸኝቶ መቅበር ቀጣይ ነባራዊ ክንውን ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ከማንም በላቀ ምንም ያስከፋንና የበደለን ቢሆንም ሰው ከሞተ በኋላ ክብር እንሰጠዋለን። ይህም በጎ ባህል ነው!

የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ፋይዳም ይኸው የባህል ጉዳይ ነው። በዚህ ላይ ይፋዊ የሆነ የውጡና ቅበሩ ትዕዛዝም በነቂስ ተሰራጭቷል። ሰው ናቸው ኖረዋል፣ ሰው ናቸው ሞተዋል፣ ሰው ናቸው ሲሞቱ ተቀብረዋል፣ ሌላ ታሪክ የላቸውም። ታሪክን የሚሠራ ሕዝብ እንጂ ግለሰቦች አይደሉም። እናም የወደቀው የሀገራችንና የአንድነታችንን ታሪክ ለማቅናትና መልሶ ለመገንባት ተቃዋሚውም ሆነ ገዥው ፓርቲ በአብሮነት በጋራ ለመሥራት ግዜው የግድ ይላል።

Friday, 21 September 2012

ከመለስ በኋላስ? (ተመስገን ደሳለኝ - አዲስ አበባ)

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዕሁድ ዕለት ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል። ለሁለት ሳምንት ያህልም ለእልፍ አእላፍት አንገብጋቢ ጉዳዮቻችን ግርዶሽ ሆኖብን የነበረው ብሔራዊ  ዘንም አብሮ አብቅቷል። ለቤተሰቦቻቸው እና ለዘመዶቻቸው መፅናናትን ከልብ እመኛለሁ። ስለዚህም ከቀብር መልስ ባሉ  ገራዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገር መ መር አለብን ብዬ አስባለሁ።

(የአቶ መለስ ሞት በመንግስት በይፋ ከተነገረ በኋላ ጥቂት ባለስልጣናት እና አንድ ቱጃር ነጋዴም ህይወታቸው እንዳለፈ በማህበራዊ ድረ-ገፆች በስፋት ሲዘገብ ቢቆይም ‹‹ሟቾቹ›› በኢቲቪ እየቀረቡ በአቶ መለስ መሞት የተሰማቸውን  ዘን ገልፀው አለመሞታቸውንም በገደምዳሜ አሳይተውናል፡፡ ይህ አንድ እውነት ነው። አልፎ ተርፎም ሞቱ የተባሉት ቱጃር ነጋዴ ከጥቂት ቀናት በፊት ሰራተኞቻቸውን ሰብስበው ‹‹መለስን ከአንድ ወር ከአስራአምስት ቀን በፊት ብራስልስ ሄጄ ጠይቄዋለሁ፡፡ አልጋው ላይ ተኝቶ በላፕቶፑ ስራውን እየሰራ ነበር፡፡ ረመዳን ነው አልዋሽም፣ ሞተ በተባለበት ጊዜ የውሸት ነው አልሞተም ነበር›› ብለዋል። እንግዲህ ነጋዴው አቶ መለስን በጠየቁበት እና ሞታቸው በተነገረበት ጊዜ መካከል የ45 ቀን ክፍተት መኖሩን ልብ በሉ) አስቀድሜ እንዳልኩት የአቶ መለስ መሞት ከተነገረ በኋላ ሞቱ የተባሉትን ጨምሮ በርከት ያሉ ባለስልጣናትን በኢቲቪ ያየናቸው ለስራ ብቁ በሆነ አካላዊ ጤንነት ሳይሆን ገና በእግሩ መቆም ያል መረ ህፃንን ‹‹ወፌ ቆመች፣ አልወደቀች…›› እያልን ራሱን ችሎ እንዲቆም ስናበረታታው እየተንገዳገደ ለመቆም በሚሞክርበት አይነት አቋቋም መሆኑም ሌላ እውነት ነው፡፡ መቼስ ምን ይባላል ‹‹እግዜር ይማራችሁ›› ከማለት ውጭ።

የሆነ ሆኖ የአቶ መለስ መሞትን ተከትሎ አንዳንድ ያልጠበቅናቸው ነገሮችን ለመታዘብ ችለናል፡፡ ‹‹መለስ አልሞተም››፣ ‹‹ ግና አይሞትም›› ከሚሉት  ምሮ
‹‹አለ ገና አለገና አለገና
‹የእከሌም› አለገና››

(የሁለት ባለስልጣናትን ስም እየጠሩ) እያሉ እስከሚጨፍሩ ሰልፈኞች ድረስ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ስንሰማቸው የነበሩ ድምፆች ናቸው።

የ ገሬ ህዝብ ስነ-ልቦናን መረዳት እንኳን ለእኔ ለጉምቱ የማህበራዊ ስነ-ልቦና ተመራማሪዎችም ቢሆን የዳገት ያህል አድካሚ ነው፡፡ መቼም ከሰልፍ ጋር እንደ በሻ በፍቅር የወደቀ ህዝብ ያለ አይመስለኝም፡፡ በጃንሆይ ላይ የተቃጣው የ1953 ዓ.ም መፈንቅለ መንግሥት ሲከሽፍ መሰለፍ፤ ራሳቸው ጃንሆይ በ1966ቱ አብዮት ከቤተ መንግሥቱ ሲባረሩ ‹‹ሌባ፣ ሌባ፣ ሌባ…›› እያለ ለመስደብ መሰለፍ፡፡ …ለአብዮት በዓል በአዲስ አመት የመ መሪያው ቀን ማግስት መሰለፍ፤ መንግሥቱ ኃይለማርያም በ1969 ህዳር 13 ቀን በኢህአፓ የተደረገባቸው የመግደል ሙከራ ከከሸፈ በኋላ ቆራጡ መንጌ በኢቲቪ ቀርበው ሁለት እጃቸውን ወደላይ ቀስረው ‹‹የበረደች ጥይት ሞኋይቴን ከመምታቷ ውጭ ሙሉ ጤነኛ ነኝ›› እያሉ መንፏለላቸውን ተከትሎ በማግስቱ በአብዮት አደባባይ ለድጋፍ ሰልፍ ስንወጣ ወፍ አልቀደመንም፡፡ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ከተደረጉ ከየትኞቹም ሰልፎች እጅግ ምፀታዊ በሆነ መንገድ የሚታወሰኝ በወራት ልዩነት የተደረገው የአስራ ዘጠኝ ስልሳ ዘጠኙ ሆሆታ ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- በ1969 ሚያዚያ 23 የሰራተኞች ቀንን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በ‹‹ኢማሌድህ›› ስም መኢሶን ባስተባበረው ሰልፍ (እነመንግስቱ ኃ/ማሪያምም ባሉበት) ላይ ድፍን የአዲስ አበባ ህዝብ ‹‹መኢሶን ፓርቲያችን›› ሲል አብዮት አደባባይን በሰልፍ አጥለቀለቀ፡፡ ይህ በሆነ በ3ኛው ወር መኢሶን ከደርግ ጋር በፈጠረው ፀብ የአመራር አባሉ ተደናግጦ ዋነኛ ምሽጉ የነበረውን የህዝብ ድርጅት ጽ/ቤትን ለቆ ከ ገር ለመውጣት ሲሞክር ሱሉልታ አካባቢ ተያዘ፤ ይህን ጊዜም በአብዮት አደባባይ ‹‹መኢሶን ፓርቲያችን›› እያለ ‹‹ለውዳሴ›› የተሰለፈው ህዝብ

ተይዞ መጣ፤
ጠላ ሲጠጣ፡፡
በማለት እያላገጠ ጨፈረበት፡፡ በ1981 ዓ.ም ግንቦት 8 ቀን በመንግሥቱ ኃይለማርያም ወታደራዊ ጁንታ አገዛዝ ላይ የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት በመክሸፉም ቅዳሜ ግንቦት 12 ቀን 1981 ዓ.ም. በአብዮት አደባባይ የተጥለቀለቀ የድጋፍ ሰልፍ ያደረገው ህዝብ፣ ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም. መንግሥቱ ኃይለማርያም ከ ገር መፈርጠጡ በሬዲዮ ሲነገር ‹‹ሌባ፣ ሌባ…›› እያለ አደባባይ ከመውጣትም አልፎ ግዙፉን የሌኒን  ውልትን እስከማፍረስ ደርሷል፡፡ …ባለፉት ሃያ አንድ የአቶ መለስ እና የኢህአዴግ የጉልበተኝነት ዘመናትም እንዲሁ በርካታ ‹‹ጉራማይሌ ሰልፎች››ን ታዝበናል፡፡ በ1997 ዓ.ም እና በ2002 ዓ.ም. የተደረጉትን ሁለት ሰልፎች ብናነፃፅር በኢህአዴግ ዘመን

በተደረጉት መ ከል እጅግ ጉራማይሌ የሆነውን ሰልፍ እናገኛለን፡፡ በ97 ቅንጅትን ደግፎ የወጣው ህዝብ ከአምስት ዓመት በኋላ የኢህአዴግን ጠቅላይ አሸናፊነት ለማብሰርም የወጣው ህዝብ ነው (ከትንሽ ማስተካከያ ጋር ማለትም፡- በመ ከል ባሉት ዓመታት ለአቅመ-ፖለቲካ ወይም ምርጫ የደረሰውን የማህበረሰብ ክፍል ሳናካት ማለቴ ነው) ብለን ብንከራከር ቢያንስ የስነ-ህዝብ ፖለቲካ (Political Demography) ያጠናን ዘዬ ይደግፈናል ብዬ አስባለሁ፡፡

ስለዚህም ሰሞኑን ለ‹‹ኑሮአችን›› እና ለበርካታ ወሳኝ የፖለቲካ ጥያቄዎቻችን ግርዶሽ ሆኖ የነበረውን የ ዘን ሰልፍንም እንዲሁ ከእነዚህ እንደ አንዱ ቆጥረን ህይወትንም ፖለቲካውንም ማስቀጠል መቻል አለብን፡፡ (ሆኖም ከሰልፉ እና ከ ዘኑ ከመውጣቴ በፊት አንድ ጥያቄ ላንሳ፡፡ ይኸውም የ ገር መሪ  ዘኑን እንዴት ነው የሚገልፀው? መቼም በአደባባይ እንደጠቅላይ ሚንስትር  ይለማርያም ደሳለኝ ‹‹ኡኡኡ…›› እያለ ግን አይመስለኝም፡፡ ይህ አይነቱ ተለምዶአዊ አለቃቀስ የሚፈቀደው እናቱ ጥላው ለጠፋችበት ህፃን ብቻ ነው፡፡ አቶ መለስ ቢሆኑ ማንም ቢሞት እንዲህ አይነት ለቅሶ በቴሌቪዥን ካሜራ ፊት አያለቅሱም፡፡ ለማስረጃ ያህልም ከዚህ ቀደም የደህንነት ሚንስትሩ ክንፈ ገ/መድህን በሞቱበት ወቅት  ዘናቸውን የገለፁት ለአንድ  ገር መሪ ፕሮቶኮሉ በሚፈቅደው መልኩ ተቆጥበው ነበር፡፡ ይህ ማለት ግን መለስ በክንፈ ሞት በሚገባ አላዘኑም ማለት አይደለም፡፡ በሚገባ አዝነዋልና፡፡ በሚገባ አላለቀሱምም ማለት አይደለም፤ በሚገባ አልቅሰዋልና፡፡ ነገር ግን በአደባባይ አይደለም፡፡ የ ገር መሪ  ዘኑ ምንም ያህል የበረታ ቢሆን ወደአደባባይ አያወጣውም፡፡ ምክንያቱም የሚመራው ህዝብ ሙሉ እምነቱን በቁርጠኛ አመራሩ ላይ ከመጣሉ አኳያ በአደባባይ ለአንድ የስራ ባልደረባው እንዲህ እየጮኸ አያለቅስምና ነው)

አሁን ወደዋናው ጉዳያችን እንመለስ፡፡ ደህና! የመ መሪያ አ ንዳችን የሚሆነውም ከፊት ለፊታችን ለተደቀኑብን በርካታ ጥያቄዎች አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መልስ ሊሰጡን እንደሚገባ በአንክሮ ማስታወሱ ላይ ነው፡፡ ቀጣዩ ደግሞ የኢህአዴግ አጥር የማያካልለን ኢትዮጵያውያን ግዴታዎቻችንን ለይተን ማወቅ እንደሚኖርብን መነጋገሩ ይሆናል፡፡ ይህ አይነቱ መነጋገር አስፈላጊ የሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልክ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆንን እና የ ገራችን ፖለቲካ እንደማይመለከተን ሁሉ ከዳር ቆመን ‹‹ስብሃት ነጋ እና በረከት ስምኦን ግብግብ ገጥመዋል››፣ ‹‹ህወሓት በብአዴን እየተሸነፈ ነው››፣ ‹‹ሰራዊቱ እና ደህንነቱ ከህወሓት ጎን መሰለፉ አይቀርም››፣ ‹‹ጄነራል ሳሞራ የኑስ እያንገራገረ ነው››… ጂኒ ቁልቋል በሚሉ የፖለቲካ ዜናዎች ‹‹ቢዚ›› መሆንን የመጨረሻ ግዴታችን እያደረግነው ስለሆነ ነው፡፡ ይህ ግን አትራፊ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የእነዚህ ፓርቲዎችም ሆነ የጉምቱ ባለስልጣናቱ ፉክክር በየትኛውም ውጤት ቢጠናቀቅ ከኢህአዴግ ውጭ ላለነው የሚፈይደው ነገር የለምና፡፡ ለእኛ የሚጠቅመን የፉክክሩ ቀጥተኛ ‹‹ተዋናይ›› መሆን ብቻ ነው፡፡ አንድ ፓርቲ ብቻ በ ገር ጉዳይ እና በመንግሥት ፖለቲካ ላይ የሚወስንበት ዘመን ከአቶ መለስ መጨረሻም ጋር አብሮ መቆምም ይኖርበታል፡፡ እናም ከኢህአዴግ እኩል በቀጣዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የመወሰን መብታችንን የማስከበር ትግል መ መር ያለብን ይመስለኛል፡፡

በእርግጥ ይህንን እድል እነበረከት ስምኦንም ሆኑ እነ ስብሃት ነጋ ከአውሮፓ እና አሜሪካ ጠርተው፣ ወይም ከተጣድንበት የማህበራዊ ድረ-ገፆች አውርደው አሊያም ከየመኝታችን ቀስቅሰው ይሰጡናል ብለን ካሰብን አንድም ኢህአዴግን በሚገባ አላወቅነውም፤ ሁለትም ፖለቲካ እና ተቃውሞን ነጣጥለን አልተረዳነውም ማለት ነው፡፡

ስለዚህም የፖለቲካ ተሳትፎ የምናገኝበትን ዕድል በየትኛውም መንግድ ተጠቅመን ማደላደል አለብን፡፡ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ከሄድንበት መንገድ በተለየና በአዲስ መንገድ መጓዝ ይኖርብናል፡፡ ከአዲሱ መንገዳችን ምን አልባትም አንዱ ባልተለመደ መልኩ ለኃይለማርያም ደሳለኝ እና ለኢህአዴግ ትንፋሽ መሰብሰቢያ ወይም ‹‹የማሪያም መንገድ›› መስጠቱ የመ መሪያው እርምጃችን ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን አባባል ትንሽ ፈታ ስናደርገው ‹‹ለኢህአዴግ ጊዜያዊ ድጋፍ መስጠት›› የሚል ሆኖ ልናገኘው ብንችል መደንገጥ አይኖርብንም፡፡

እንዲያውም በግልባጩ ይህንን እርምጃ እንደብስለት እንጂ ክብረ-ነክ አድርገን መውሰድ የለብንም፡፡ ለምን? የሚል ጥያቄ የሚያነሳ ካለ መልሱ ለኢህአዴግ የምንሰጠው ጊዜያዊ ድጋፍ ‹‹ከታላቁ መሪ ወረስኩት›› ለሚለው ‹‹ራዕዩ›› ሳይሆን ‹‹በ ገር ጉዳይ የመወሰን እድልን›› ከአጥሩ ውጭም አውጥቶ ማካፈሉ ለ ገሪቱ መፀኢ እድል አስፈላጊ መሆኑን ቀልቡን ሰብስቦ እስኪያምን ብቻ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ነው የሚል ይሆናል፡፡ ልክ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቀብር ስነ-ስርዓት የተሳካ ለማድረግ ህዝቡ ለኢህአዴግ እንደሰጠው አይነት ድንገቴ ዕድል ማለቴ ነው-እኛም ከፓርቲው የምንፈልገው፡፡

ሆኖም ‹‹ይህንን አይነቱን ዕድል ኢህአዴግ እስኪሰጠን ምን ያህል ጊዜ መጠበቅ ይኖርብናል?››፣ ‹‹እንዴትስ ሆኖ ነው በመንግስታዊ ስልጣን ላይ የመወሰን ዕድል የሚሰጠን?›› የሚሉ ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀሬ ናቸውና እንደመነሻ ሃሳብ ሊሆኑ የሚችሉ የራሴን ሁለት ጥቁምታዎችን ላቅርብ፡-

1ኛ.  ይለማሪያም ደሳለኝ እና አጋሮቻቸው፣ ካድሬዎቻቸውን እና ደጋፊዎቻቸውን ‹‹ብሄራዊ ዕርቅ›› ከመፍጠር አኳያ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት የመመስረቱን አስፈላጊነት ማሳመንን የመ መሪያው የቤት ስራቸው ሊያደርጉት ይገባል፡፡ እነሱንም ካሳመኑ በኋላም ሽብርተኛ ለተባሉ ድርጅቶችም ሆነ ለፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ምህረት አድርገው በጥሪው እንዲካተቱ መፍቀድ ይኖርባቸዋል፡፡

2ኛ. አንደኛውን አማራጭ አዲሱ መንግስት የመሸከም ትከሻ ከሌለው ቀሪው አማራጭ በ2005 ዓ.ም የሚደረገው የአዲስ አበባ ምርጫ ነው፡፡ እናም ይህ ምርጫ ከመደረጉ በፊት አሁን ያለውን የምርጫ ቦርድ ማፍረስና ተአማኒነት ባላቸው ገለልተኛ ባለሙያዎች መልሶ ማዋቀር፣ የመንግስት ሚዲያዎች ለተቃዋሚዎችም ለገዥው ፓርቲም እኩል የሚያገለግሉበትን መመሪያ አዘጋጅቶ መተግበር፣ የሰራዊቱን እና የደህንነት  ይሉን በተግባር ታዛዠነታቸውን ለህገ-መንግስቱ ብቻ እንዲሆን ማድረግ፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ… ከአዲስ አበባ ምርጫ በፊት ማመቻቸት የግዴታ ውዴታ ነው፡፡ (…ለአዲሱ መንግስት ጊዜና ድጋፍ እንስጠው ያልኩት እነዚህ ሁኔታዎች እንዲሟሉ ብቻ ነው፡፡ ይህንን ድጋፍ ስናደርግ ግን የመኢሶንን ስህተት ላለመድገማችን እርግጠኛ መሆን ይኖርብናል) መኢሶን የ66ቱ አብዮት የፈጠረው ትልቅ ፓርቲ ነው፡፡ ምሁራዊ ሰውነታቸው የጎላ ልሂቃኖችም የተሰባሰቡበት ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ፓርቲ ሊታረም የማይችል ከባድ ስህተት ሰርቷል፡፡ ይኽውም ለወታደራዊ ጁንታ ድጋፍ መስጠት አለብን በሚል የተሳሳተ ስሌት ከደርግ ካምፕ ውስጥ በመግባት ‹‹የህዝብ ድርጅት ጽ/ቤት››ን በመመስረት በርካታ ካድሬዎችን ከመመልመሉም በላይ የመኢሶንን ውሳኔ ‹‹የተሳሳተ›› በሚል ግጭት ፈጥሮ ቀይና ነጭ ሽብር ለመ መር ምክንያት ሆኖአል፡፡ እናም ይህ ስህተት እንዳይደገም መጠንቀቅ ያሻል፡፡ ማን ነበር ‹‹ሰው የሚማረው አንድም ከፊደል፣ አንድም ከመከራ ነው›› ያለው?

መቼም ይህ ሁሉ ህዝብ ያዘነው አቶ መለስ በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ‹‹ ገሬን አሳድገውልኛል››፣ ‹‹ህይወቴን ቀይረውልኛል››፣ ‹‹መብቴን አክብረውልኛል…›› ብሎ እንዳልሆነ የህወሓት እና የብአዴን ሰዎችም በልባቸው ያምናሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ህወሓት በሊቀመንበሩ በአቶ መለስ ቦታ ‹‹ሌላኛው መለስ›› ሊባሉ የሚችሉትን አባይ ፀሐዬን ለመምረጥ እንዳቀደ፤ ኦህዴድ ደግሞ አስቴር ማሞን ‹‹ሊቀመንበር›› በሚለው አ ንዳው ላይ እንዳሰፈረ የመረጃ ምንጮቼ ነግረውኛል፡፡ ምንአልባት ህወሓት አባይ ፀ ዬን መምረጡ እውነት ከሆነ ግን ራሱን የቻለ አንድምታ ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም አባይ መለስ ያደርጉት የነበረውን የሴራ ፖለቲካ በሙሉ ለማድረግ የሚችል አቅሙም ልምዱም እንዳላቸው የህወሓት አመራሮች ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ስለዚህም ህወሓት አባይን በማምጣት በመለስ ሞት የጎደለበትን ‹‹የበላይነት›› የመመለስ ዕቅድ ሊኖረው ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ መጭው ጊዜ አደገኛ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ አዲስ አበባ የሚገኙ የምዕራብ  ገራት ዲፕሎማቶችም ‹‹ስጋታቸው እንደሆነ ገልፀውልኛል፡፡ በእርግጥ የዲፕሎማቶቹ ስጋት በአክራሪው የህወሓት አመራር ላይ ብቻ ሳይሆን በረከት ስምኦንን እና አዲሱ ለገሰንም ይጨምራል፡፡ እነዚህ ሰዎች ‹‹ነባራ ታጋይ›› (Old Comrade) ከመሆናቸው አኳያ በኃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የበላይነታቸውን ከማሳየታቸውም በተጨማሪ፣ ‹‹መጠቀሚያ›› የማድረግ እቅድ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ከአዲሱ መንግስት ‹‹መሰረታዊ የፖለቲካ ማሻሻያዎች››ን መጠበቅ ላም አለኝ በሰማይ….አይነት እንደሚሆን ዲፕሎማቶቹም ያምናሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በዲፕሎማቶቹ አይን ሞገስ ያገኙት ወይም ተመራጭ ሆነው የወጡት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ እና ቴዎድሮስ አደህኖም ብቻ ናቸው፡፡ ሆኖም ከብርሃነ ክርስቶስ በስተቀር ሁለቱ ሰዎች በኢህአዴግ ውስጥ ተሰሚነታቸው አናሳ ስለሆነ የነባር ታጋዮቹ መጠቀሚያ የመሆን ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ (ይህ የዲፕሎማቶቹ ምልከታ ምንአልባትም አቶ መለስ ኢህአዴግን ወደቻይና መሳባቸው አሳስቧቸው፤ እነርሱ የተሻሉ ናቸው ያሏቸው እነ ኋ/ማሪያም ደግሞ በግልባጩ ስርአቱን ወደምዕራቡ ጎራ ሊመልሱት ይችላሉ ብለው ማመናቸው ይሆናል)

በአናቱም ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ኃይለማርያም ደሳለኝ ለሰራዊቱ ‹‹Commander in chief›› (ጠቅላይ ወታደራዊ አዛዥ) ለመሆን ያላቸው ብቃት እና ተቀባይነትም አሳሳቢ ሲሆን ሌላው አደገኛ እንቅፋት የሚሆንባቸው በብሔርና በጥቅመኝነት የተወሳሰበውን የገዢው ልሂቅ ስብስብን ‹‹የፖለቲካ ማሻሻያ መደረግ አለበት›› ብሎ ማሳመኑ ላይ ነው፡፡ ኦህዴድ ውስጥም አባዱላ ገመዳ ወርደው አለማየሁ አቱምሳ በተተኩበት ወቅት በአባዱላ ጊዜ የነበሩትን በርካታ ካድሬዎች ‹‹ሙስና›› በሚባል የመገምገሚያ አ ንዳ ብዙዎችን ከፓርቲው ውጭ ሲያደርጉ፣ ጥቂት የማይባሉትን ደግሞ ለእስር ዳርገው እንደነበረ ይታወሳል፡፡እናም አሁን ከአዜብ መስፍን ጋር የጠበቀ ጓደኝነት ያላቸውን አስቴር ማሞን ሊቀመንበር ለማድረግ የታሰበው በአባዱላ መነሳት ያኮረፉትን ካድሬዎች ለማለዘብ ሊሆን ይችላል የሚል መላምት አለ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የተባረሩና የታሰሩ ካድሬዎች ወደቦታቸው የመመለስ እድል ማግኘታቸውን አይቀሬ ስለሚያደርገው አደገኛ ‹‹አቧራ›› ማስነሳቱ አይቀርም፡፡

በመጨረሻም- አጭር መልዕክት-ለኢህአዴግ

የ ገሪቱን ስልጣን በተለይ ህወሓት እና ብአዴን እንደአያት ቅድመ አያት ርስት ‹‹ወራሽ ነኝ›› በሚል በቤተመንግስት እና በኢህአዴግ ጽ/ቤት እያደረጋችሁት ያለውን ትግል ብትረሱት የተሻለ ነው፡፡ እናውቃለን ታግላችኋል፤ ነገር ግን በስልጣን የቆያችሁባቸው ሃያ አንድ ዓመታት ከበቂ በላይ ክሷችኋል፡፡ እናውቃለን አምባገነኖች ናችሁ፣ ነገር ግን ትውልዱ አምባገነንነትን ሊሸከም እንደማይችል ሊገባችሁ ይገባል፡፡ …በጣም የሚገርመው ደግሞ በዚህ ሳምንት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴያችሁ ከመለስ ሞት በኋላ የመ መሪያውን ስብሰባ አድርጎ ያወጣው መግለጫ ይዘት ነው፡፡ አዎን! ይህ ስብስብ ከተጠናቀቀ በኋላ ፓርቲው በመግለጫው ላይ ‹‹የሕዝብን ቁጭትና አደራ በህዝቡ በራሱ በተደራ ና ቀጣይነት ባለው ተሳትፎ ወደውጤት በመቀየር….›› የሚል  ረግ ሰንቅሮበታል፡፡ ምንአልባት አባባሉን ልብ ካላልነው ብዙም አሳሳቢ ላይመስለን ይችላል፡፡ ሆኖም ይህን  ረግ ፈታ አድርገን ካየነው መጭው ጊዜ ብሩህ እንደማይሆ በእርግጠኝነት እንደሚጠቁመን እንረዳለን፡፡ ምክንያቱም ይህ አይነቱ ሁኔታ የሚያመላክተው አንድም ፓርቲው ‹‹የመለስን አደራ ለማስፈፀም›› በሚል ያለአንዳች ማሻሻያ ለመቀጠል የወሰነ መሆኑን ሲሆን፤ ሁለተኛው አደገኛ ነገር ደግሞ ስርዓቱ ወደ “Stationary bandits” (መንግስታዊ ሽፍትነት) የመቀየር አዝማሚያ እንዳለው አመላካች ነው፡፡ ይኸውም ‹‹የህዝብን ቁጭትና አደራ በህዝቡ በራሱ…›› ለመወጣት በሚል

ፕሮፓጋንዳ በከፍተኛ ደረጃ ግብር መጣልን፣ ለአባይ ግድብ ሁለተኛ ዙር ቦንድ ግዙ ተብሎ እንደተደረገው አይነት ማስገደደድና የመሳሰሉት እርምጃዎችን ሊወስድ መቻሉ አይቀሬ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በኑሮ ውድነቱ ላይ ተጨማሪ ጫና መፈጠሩ አያጠያይቅም፡፡ እናም ከዚህ ይልቅ ህዝቡ ለአቶ መለስ ያወረደውን እንባ ‹‹ኢቲቪን ገለል›› አድርጋችሁ እውነተኛ ምክንያቱን ለማወቅ ብትጥሩ ‹‹አዋጭ›› ንግድ ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ ልክ እንደ ዝነኛው ኤፈርት፡፡ ስለዚህም ያ እንባ ለውጥ ፈላጊ መሆኑን ልትረዱት ይገባል፡፡

አጭር መልዕክት-ከኢህአዴግ ውጭ አማራጭ ለምትሹ

እነሆም ከዚሁ ጎን ለጎን /የኢህአዴግ ውሳኔ ምንም ሆነ ምን/ በ ገራችን ጉዳይ የመወሰን መብታችንን ለማስከበር ለ ዘን የወጣነውን ያህል ‹‹ነቅለን መውጣት›› ብቸኛ አማራጫችን ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን የዲያስፖራና ልሂቃን በዚህ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ አዎንታዊ ድጋፋቸው ያስፈልጋል፡፡ ከጥላቻ የራቀ የፖለቲካ ስልት በመከተል በዕውቀትም ሆነ በገንዘብ ለውጥ ፈላጊውን ኢትዮጵያዊ ማገዝ ለነገ የሚተው ስራ አይደለም፡፡ እንዲሁም ከጥቂት ወራት በኋላ በሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ምርጫ ላይ ድጋፍ የመስጠትንና የመንሳትን ችሎታ በኢትዮጵያ ላይ በሚኖራቸው የውጭ ፖሊሲ ቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የቅስቀሳ ስራ መስራቱም አንድ ስልት ይመስለኛል፡፡

ከዚህ ባሻገር ግን በታቃዋሞ ጎራ (በ ገር ውስጥም በውጭም) የተሰባሰበው  ይል ልዩነቱን አጥብቦ ወደአንድ መሳበሰብ ይኖርበታል፡፡ በአናቱም ምናአልባት ምንአልባት ነገሩ ሁሉ ካሰብነው በተቃራኒ ሄዶ ‹‹አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ›› የመሆን አዝማሚያ ቢኖረው እንኳ ‹‹ለሰላማዊ እምቢታ›› ራስን ማዘጋ ቱ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ወሳኝ ነው፡፡ በእርግጥ ዝግጅቱ ይህን ‹‹እምቢታ›› ተከትሎ የሚመጣውን ማንኛውንም መስዋዕትነት የመክፈል ቁርጠኝነትን ማጠቃለል ይኖርበታል፡፡ ያኔ ነው መለስን የመተካት ጉዳይ የኢህአዴግ የግል ጉዳይ የማይሆነው፡፡ ያኔ ነው በኢትዮጵያ ጉዳይ ጥቂት ግለሰቦች የሚወስኑበት ጊዜ የሚያከትመው፡፡ ያኔ ነው በ ገራችን ጉዳይ ጉልበተኞች ብቻ ያሻቸውን የሚያደርጉበት  ንበር የምትጠልቀው፡፡ ያኔ ነው አንተም እኔም ኢትዮጵያዊነታችን በተግባር የሚረጋገጠው፡፡ ያኔ ነው…

Monday, 17 September 2012

በቁማቸው ከገደሉት በሞታቸው የገደሉት በፍቃዱ ዘ ኃይሉ | September 1st, 2012 at 3:10 am | |

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞት በብዙዎች ጉንጭ ለሁለት ወር ሲጉላላ ቆይቶ በኢትዮጵያ መንግስት ከተረጋገጠ ይኸው ሁለት ሳምንት ሊሆነው ጥቂት ቀናት ቀሩት፡፡ መንግስት ብሔራዊ የሐዘን ቀናት እስከዕለተ ቀብራቸው በማወጁ ባንዲራም ዝቅ ብሎ እየተውለበለበ ነው፣ መገናኛ ብዙሐንም ሙሉ ትኩረታቸውን በዚያው በሐዘኑ ጉዳይ ላይ እንዳደረጉ ናቸው፡፡ (በነገራችን ላይ የጡረተኛ ሚኒስትሮችን ጥቅማጥቅም የሚዘረዝረው የ2001 አዋጅ ላይ [አንቀጽ 11/1/ለ] ብሔራዊ የሐዘን ቀን አንድ ቀን እንደሆነ ይደነገጋል፡፡)

ኢትዮጵያውያን ወትሮም ቢሆን ሐዘን የማክረር ባሕላችን የተጋነነ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሠልስት ሳይቀር እየተሰረዘ የሦስቱ ቀን ሐዘን ወደሁለት ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡ በነገራችን ላይ የሐዘን ቀናት ወደሦስት ቀናት ዝቅ እንዲሉ የተደረገው በአፄ ምኒልክ አዋጅ የዛሬ መቶ ዓመት ገደማ ነበር፡፡ እንግዲህ በሰሞኑ፣ ሁለት ሳምንታት የዘለቀ የሐዘን ግዜ መቶ ዓመት ያህል ወደኋላ ተመልሰናል ማለት ይቻላል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር የሞተበት አገር ሕዝብ ማዘኑ አስገራሚ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን በውዴታም ይሁን በግዴታ ይህንን ያህል ቀናት ማዘኑ ወይም እንዲያዝን ማድረጉ ብዙ ጥያቄዎችን ያጭራል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የምናውራውም ከዚህ ፈር ከለቀቀ የሐዘን ግዜ በስተጀርባ ስላሉ ጉዳዮች ነው፡፡

አንድ፤ ችግር ይኖር ይሆን?

አገሪቱ አሁን እየተመራች ያለችው በተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ነው ቢባልም፣ ያንን የሚያስመሰክር ነገር አላየንም፡፡ የመንግስት ልሳን የሆኑት እነ አዲስ ዘመን ሳይቀሩ ‹‹ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር›› እያሉ ነው የሚጠሯቸው፡፡ ከዚያም በላይ አሳሳቢው ግን በቶሎ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ማዕረግ በፓርላማ ምርጫ እንዲቀበሉ አለመደረጉ አጠያያቂ ነው፡፡ ምንም እንኳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በታወቀ በሦስተኛው ቀን ተመርጠው፣ ቃለመሓላ እንደሚፈጽሙ ቃል ተገብቶልን የነበረ ቢሆንም፣ መጀመሪያ ‹‹በአቡነ ጳውሎስ ቀብር›› በኋላም ደግሞ ‹‹የፓርላማ አባላት ሐዘናቸውን ይወጡ›› በሚሉ የማያሳምኑ ምክንያቶች ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፡፡ ይሄ ቁርጥ ያለ ቀን ለማስቀመጥ ያለመወሰን ጉዳይ አሁንም በአቶ ኃይለማርያም ተተኪነት ላይ በግንባሩ ውስጥ (ከምስጢር ወዳድነቱ አንፃር) ስምምነቶች አለመኖራቸውን የሚያጠራጥር ነው፡፡

እንደሚታወሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩን መታመም በስንት ውትወታ ያመነው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ ሕመሙን አቃልሎ ነበር የተናገረው፡፡ በሌላ በኩል በተለይ በማሕበራዊ አውታሮች ውስጥ የተናፈሱት ወሬዎች ደግሞ ‹‹የሚተኩት ሰው ላይ እስኪስማሙ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞተዋል›› የሚል አንድምታ ነበራቸው፡፡ የዚያን ግዜውን ወሬ ውሸትነት የሚያረጋግጥ ነገር እስካልተገኘ የአሁኑንም በሐዘን የተሸፈነ የጊዜ ክፍተት በጥርጣሬ መመልከቱ ምንም ሊያስገርም አይገባም፡፡ ስለዚህ የመንግስት አካላት ጉዳዩ የሕዝብ መሆኑን በማወቅ ግልጽነት እና ኃላፊነት የተሞላበት አሠራር እንዲከተሉ እመክራለሁ፡፡

ሁለት፤ መተኪያ የላቸውም?

የመለስን ሞት ተከትሎ አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ አብዛኛው የቴሌቪዥን አስተያየት ሰጪ ‹‹እርሳቸውን መተካት አይቻልም›› ለማለት መድፈራቸው ለአገራችን ትልቅ ቅሌት ነው፡፡ ለዚያ ነው የ80 ሚሊዮኖች አገር ‹ከአንድ ሰው ሌላ ብቃት ያለው ዜጋ የላትም› የሚለውን መርዶ ስላሰማን የመለስ ሞት እርሳቸው በሕይወት እያሉ ካደረሱብን የሰብአዊ መብት ጥሰት ሁለ በላይ ገደለን ለማለት የደፈርኩት፡፡ ይሄ አባባል፣ ኢትዮጵያ ከመለስ እጅግ የተሻሉ እልፍ ሰዎች አላት ብለን የምናምነውን ዜጎች ብቻ ሳይሆን እራሳቸውን የኢሕአዴግ አባላት እና ደጋፊዎችንም ጭምር የሚሳደብ ነው፡፡

የኢሕአዴግ አባላት ‹አንድ መለስን መተኪያ የለንም› ብለው የሚሉ ከሆነ ስልጣኑን ለተቀናቃኝ ፓርቲዎች ማስረከብ ወይም በጥምረት ለመሥራት መወሰን አለባቸው፡፡ ምክንያቱም እራሳቸው እንደነገሩን እና ‹‹መለስ የጀመሩትን ልማት እናስቀጥላለን›› መፈክር ውስጥ ውስጡን እንደምንረዳው ሁሉ ነገር እርሳቸው ነበሩና ሌሎቹ በሙሉ በእርሳቸው ሽፋን የነበሩ ናቸው ማለት ነው፡፡

በሌላ በኩል ከሕዝቡ መካከል የወጡ እና በእኔ አመለካከት ኢሕአዴግን እና ፕሮፓጋንዳውን በቅጡ ያልተረዱ ሰዎችም ይህንኑ ‹መለስ መተኪያ የላቸውም› የተሰኘ ነጠላ ዜማ እያስተጋቡ የመንግስት መገናኛ ብዙሐን ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆነዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች በመለስ 21 ዓመት የዘለቀ የስልጣን ዘመን ምን ዓይነት ስርዓት እንደተፈጠረ ሕያው ምስክሮች ናቸው፡፡ በየትኛውም ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ የቱንም ያህል የሚከበር ታላቅ ሰው ቢሞት ይታዘንለት እንደሆን እንጂ፣ መተኪያ የለውም ምን ይውጠናል የሚል ስጋት አይፈጠርም፡፡

የመለስን ሞት ተከትሎ የተስተዋለው ነገር የአምባገነን ስርዓት ፍሬዎችን ያሳያል፡፡ በአምባገነን ስርዓቶች ውስጥ የማኅበረሰቡ አባላት ከአምባገነኑ መሪ በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው እንዲሰማቸው ተደርገው ይቀረፃሉ፡፡ እንግዲህ ሁላችንም እንደምናውቀው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከስልጣን ይውረዱ ሲባል በፓርቲ ውስጥ ስብሰባ እዬዬ ሲባል የተከረመው ለዚያ ነው፡፡

አቶ መለስ በየትኛውም የምርጫ ክርክሮች ወቅት ከተቃዋሚዎች ጋር ፊትለፊት እንዲገጥሙ ተደርጎ አያውቅም፣ ከየትኛውም ኢትዮጵያዊ የግል ጋዜጠኛ ጋር በፖለቲካ ጉዳይ የብቻ ለብቻ የቃለ ምልልስ እንዲሰጡ ተደርጎ አያውቅም፤ ገፅታ ለመገንባት በሚያስችሉ መድረኮች ላይ ብቻ እንዲገኙ እና በጥንቃቄ የተመረጡ ንግግሮችን ብቻ እንዲያደርጉ ሲመቻችላቸው ከመክረሙ አንፃር የማኅበረሰቡ አካላት ላይ ‹ከሳቸው ሌላ የለን ይሆን?› የሚል ውዥንብር መፍጠሩ አያስገርምም፤ የሚያስገርመው ሊተኳቸው ዕጩ ሆነው የቀረቡት ግለሰብም ይህንኑ ማስተጋባታቸው ነው፡፡

ሦስት፤ ሐዘን ወይስ …?

የመለስን አስተዳደር ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ ባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በየሳምንቱ በሚታተሙ ጥቂት ጋዜጦች እና በየአምስት ዓመቱ (ለይስሙላ) በሚካሄደው ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ነበር እያሉ የሚከራከሩ አሉ፡፡ በመሰረቱ እነዚህ ሰዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸውን እንጂ በጠበበ ምህዳር እንዳይፈናፈኑ መታሰራቸውን፣ ጋዜጠኞች በጻፉት ነገር መከሰስና መታሰራቸውን፣ ምርጫዎች ከጊዜ ወደጊዜ በአንድ ፓርቲ የበላይነት ብቻ የሚጠናቀቁ መሆናቸውን ሳይጠቅሱ ያልፋሉ፡፡ እነዚህ ቁምነገሮች ደግሞ የስርዓቱን ዋነኛ ባሕርያት ገላጭ ናቸው፡፡

የመለስ አስተዳደር ‹‹ሕገመንግስታዊ አምባገነን (constitutional dictatorship)›› የሚባለው ዓይነት ነው፡፡ ይህ የአምባገነን ዓይነት መሪዎች ለአደጋ ጊዜ እንዲጠቀሙበት በሕገመንግስቱ ላይ የሚሰጣቸው ስልጣንን ተጠቅመው ለጭቆና ሲያውሉት የሚፈጠር ነው፡፡ የአሜሪካው የቀድሞ ፕሬዚደንት ፍራንክሊን ሩዝቬልት ‹‹ታላቁ ድብታ (Great Depression)›› በመባል በሚታወቀው የኢኮኖሚ ውድቀት እና የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት አገራቸውን ከውድቀት ለማዳን ይህንን ስልጣናቸውን በመጠቀም ኮንግረሱን ሳያማክሩ እርምጃዎች ወስደዋል፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ ግን ምንም ዓይነት ተጨባጭ ችግሮች ባልተመዘገቡበት ጊዜ ፓርላማውን ሳያማክሩ ሶማልያ ገብተዋል፣ ምርጫ 97 የተካሄደ ዕለት የሰራዊቱን ተጠሪነት ወደራሳቸው አዙረዋል፣ የፌዴራል ከተማዋ አዲስ አበባን እና የደቡብ ክልልን ምክርቤቶች በትነዋል፡፡ ከዚያም በላይ ጨቋኝና ከሕገመንግስቱጋ የሚጋጩ አዋጆችን አውጥተው የተፎካካሪዎቻቸውን አቅም አዳክመዋል፣ የተፎካካሪዎቻቸውን ደጋፊዎች ወኔና ተስፋ ቀምተዋል፡፡

እናም ይህንን ሁሉ በውጤታማነት ካከናወኑ በኋላ የሞታቸው ዜና ሲሰማ (በእርግጥ ከብዙሐኑ አንፃር ሲታዩ ብዙ ናቸው ለማለት ቢቸግርም) ለቁጥር የሚያታክቱ ሰዎች አስከሬናቸውን ለመቀበል መውጣታቸው፣ ቤተመንግስት ድረስ ለቅሶ ለመድረስ መሰለፋቸው እና አሁንም በመጪው የቀብራቸው ስርዓት ላይ መገኘታቸው የሚሰጠው ትርጉም አለ፡፡ አንደኛ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ቢጨቁኑት ምህረት የማይቸግረው መሆኑ፣ ሁለተኛ፤ በአስተዳደራቸው የተፈጠረው የፍራቻ ድባብ አሁንም ለእርሳቸው አላዘንክም በሚል ቅጣት ያስከትልብኛል ብሎ በመፍራቱ፣ ሦስተኛ አጋጣሚውን በመጠቀም ቤተመንግስቱን ለመጎብኘት ወይም የገቢ ምንጭ ለመፍጠር (ፎቶ፣ ፖስተር እና ቲሸርት ሽያጮችን ልብ ይሏል) ነው፡፡

አራት፤ ኪሳራው በማን ነው?

መለስ መሞታቸው በመንግስት መገናኛ ብዙሐን ከታወጀ በኋላ የአገሪቱ ኢኮኖሚም በሐዘን እንዲቆዝም የተፈረደበት ይመስላል፡፡ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች በሥራ ሰዓት ሐዘን ነው በሚል እንዲሰበሰቡ ይታዘዛሉ፣ በክልሎች የለቅሶ ስነስርዓቶች ይዘጋጁ እና ሰዎች እንዲገኙ ሲባል መሥሪያ ቤቶችም እየተዘጉ ነው፡፡ ከዚህም በላይ በቁመታቸው ከዚህ በፊት አይተናቸው የማናውቃቸው ‹ቢልቦርዶች› እየታተሙ ይለጠፋሉ (በአራዳ ሕንፃ ቁመት የተዘረጋውን ልብ ይሏል)፡፡ ሌላው ቀርቶ መስቀል አደባባይ የተተከለውን ድንኳን ለመገንባት የተንቀሳቀሰው ክሬን እና የወጣበት ወጪ አመታዊ በጀቷን በብድር ከምትሞላ አገር የሚጠበቅ አይደለም፡፡

የአሁኖቹ መሪዎች ሕዝቡ ያሳየውን ሰብአዊ ርህራሔ እና ሐዘን እንዳያቆም ይፈልጉ እንጂ ሕዝቦች ሐዘኑ ይቀጥል እስካላሉ ድረስ ለብክነቱ ተጠያቂ መሆን አይችሉም፡፡ በዚህ የኑሮ ውድነት ዜጎች ከአፋቸው እየነጠሉ የሚከፍሉት ታክስ ለፖስተር ማሳተሚያ፣ ለመፈክር እና ለፕሮፓጋንዳ ብሎም የፓርቲ አባሎችና የደጋፊዎች ሊግ አባላት እና ሌሎችንም ማመላለሻ ትራንስፖርት ፍጆታ መዋሉ የመንግስትን ማን አለብኝነት (ተጠያቂነት ማጣት) ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

መንግስት በዚህ ግዜ የሚያስፈልገው፣ ይህችን አጋጣሚ ተጠቅሞ እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት እና መፍጨርጨር የነበረ ቢሆንም፣ ‹እንኳን ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ› የሆነውን ኢኮኖሚያችንን በአልባሌ ብክነት ማባከኑ ጉዟችንን እያደር እንቦጭ ያሰኘዋልና ሊታሰብበት ይገባል፡፡

በመጨረሻም
በዓለማችን ለአንድ ሰው ቀብር ብዙ ሰው አደባባይ በማስወጣት ግብጾችን የሚፎካከራቸው የለም፡፡ 5 ሚሊየን የሚገመቱ ግብጻውያን እ.ኤ.አ በጥቅምት ወር 1970 ለፕሬዘንዳንታቸው ጋሜል አብደል ናስር ቀብር አደባባይ ወጥተዋል፡፡ የኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮችም እሁድ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ለአቶ መለስ ቀብር እንዲወጡ ይፈልጋሉ፡፡ እርግጥ ለቀብሩ ሊወጡ የሚችሉት የግብጻውያኑን ያክል ባይሆኑም ብዙ እንደሚሆኑ መገመት ከባድ አይደለም፡፡

ነገር ግን ይህ የጎሳ ልዩነት ተደረገብኝ፣ የኢኮኖሚ በደል ደረሰብኝ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት ደረሰብኝ፣ ዴሞክራሲያዊ መብቴን ተነፈግኩ ሳይል ሐዘኔታውን በክብር እየገለፀ ያለ ሕዝብ ብዙ የሚገባው መሆኑን መዘንጋት ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡ ይህ ሕዝብ በሐዘን ሰበብ ከድንኳኑ ጀርባ ሌላ ደባ የሚሰራበት ዓይነት ሕዝብ አይደለም፡፡ ይህ ሕዝብ የስርዓት ለውጥ እንጂ የንጉሥ ለውጥ ምንም አይፈይድለትም፡፡

---
ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ቢሆንም፣ ጋዜጣው እንዳይታተም በብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት በመታገዱ እዚህ አስፍሬዋለሁ፡፡

መለስ አሁን አይሙትብን July 16, 2012በ Naod ቤተሥላሴ

መለስ ዜናዊ እንዲሞት የሚጸልይ ጓደኛ አለኝ፡፡ እኔ ግን፤ መለስ ተራ ሰው ይመስል፤ ድንገት ዝም ብሎ እንዲሞት፤ አልፈልግም ባይ ነኝ፡፡ ስለ ሁለት ነገር  1ኛ፤ ከታሪካችን በመማር  2ኛ፤ መለስ ከመሞቱ በፊት ማየት ያለበት ነገር አለ ብዬ ስለማምን፡፡
በታሪካችን መሪዎቻችንን ሥልጣን የለቀቁት፡- ተፈንቅለው/ተባረው እንደ ኃይለሥላሴ፤ መንግሥቱ ኃይለማርያም፤ ነጋሶ ጊዳዳ፡፡ ሞተው እንደ  ቴዎድሮስ፤  ምኒሊክ ፡፡ተገድለው እንደ  ዬሐንስ፤ በምርጫ ተሸንፈው…. እ…እስካሁን የለንም፡፡
አሁን ታሪክ ያቀረበልን ምርጫ ‹‹መለስ የትኞቹን መሪዎች ይቀላቀላል?›› የሚል ብቻ ሳይሆን ‹‹እንዴት ይቀላቀል?›› የሚልም ነው፡፡ 

በእርግጥ መለስ ለየት ያለ፤ የራሱ ሥልጣን መልቀቂያ መላ እንዳሰበ ተናግሯል፡፡ ሽግሽግ የሚባል መላ፡፡ እርሱ ቀስ እያለ ስልጣኑን እየተወ፤ ከታች ያሉት ብጤዎቹ ቀስ እያሉ፤ እየተሸጋሸጉ ሥልጣን እንዲይዙ፡፡ ከዚያ በአካል ሥልጣን ለቆ በመንፈስ እየመራ ሊኖር አልሟል፡፡ ሞት በእቅዱ ውስጥ ያለ አይመስለኝም፡፡ በታሪካችንም፤  አቅዶ የገደለ እንጂ፤ ተዘጋጅቶ የሞተ መሪ ኖሮን ስለማያውቅ፤ መለስ ልዩ እንዲሆን አልጠብቅም፡፡ ድንገት ይሞታል፡፡ የእኔ ግን ጸሎቴ፤ አሁን እንዳይሞት ነው፡፡ ለምን በሉ?

መለስ ይሙት ብዬ እንዳልጸልይ፤ ከአሁን በፊት እንዲሞቱ ብዬ የጸለይኩባቸው ሁለት መሪዎች፤ ጭራሽ ወደ ሕያውነት ተለውጠው መታመም ሁሉ አቆሙ፡፡አሁንም አሉ፡፡ ስለዚህ መለስን እንዲሞት አልጸልይም፡፡ እኔ ከለመንኩ፤ የምለምነው ‹‹ከእርሱ ቀድመው፤ የወለዳቸው ፖለቲኮች ሁሉ፤  እንዲሞቱ ነው››፡፡
ዓይኑ እያየ ልጆቹ… ዘረኝነት፤ ተገንጣይነት፤ በቀለኝነት፤ ከፋፋይነት፤ የአንድ ፓርቲ ገዢነት፤ ሚዲያ አፋኝነት፤ አምልኩኝ ባይነት፤  ወዘተ ዓይኑ እያየ፤ ከእርሱ ቀድመው እንዲሞቱ እመኛለሁ፡፡
ዓይኑ እያየ ጠላቶቹ…ኢትዬጵያዊነት፤ ባንዲራ፤ አንድነት፤ ታሪክ፤ ነጻነት፤ እኩልነት፤ ወዘተ ከታመሙበት አልጋ ተነስተው፤ ወደ ቀደመ ቦታቸው ሲመለሱ ቢያይ እመኛለሁ፡፡
ከመሞቱ በፊት…ሁሌ በጭብጨባ የሚቀልጠው ፓርላማ፤ በሙግት እና በክርክር ቅልጥ ሲል አይቶ፤ ፊቱን አይተው የሚፈርዱት ዳኞች መጽሐፋቸውን አይተው መፍረድ መጀመራቸውን ሰምቶ፤ የፓርቲ መለዮ እንዲያጠልቅ የተደረገው መከላከያ ሰራዊት ኢትዬጵያዊ መለዬ አበጅቶ ‹‹ኢትዬጵያውያን ላይ አልዘምትም›› ሲል እንዲያይ እመኛለሁ፡፡  
ከመሞቱ በፊት…አሁን በፍራቻ የተጻፈለትን ታሪክ ሳይሆን፤ ወደ ፊት በነጻ ታሪክ ጸሐፊዎች የሚጻፍለትን ‹‹መለስ ዜናዊ…የሀገሩን ባንዲራ ‹‹ጨርቅ›› ብሎ የሰደበ ብቸኛው መሪ››፤ ‹‹የሚጠላትን ሀገር የመራ ብቸኛው መሠሪ መሪ››፤ ‹‹የሚመራት ሀገር ተገነጣጥላ አልሞት ስላለችው የታመመ ሳዲስቲክ መሪ››፤ ‹‹የአፍሪካ መሪ ለመሆን ተመኝቶ፤ የአንድ ብሔር መሪ ሆኖ የቀረ ዴሉዥናል መሪ››፤ ‹‹ነጻ ያወጣውን ህዝብ ባሪያ ያደረገ፤  ኢጎቲስቲክ ታጋይ››፤ ‹‹ቃሉን በየትግል ምዕራፉ የሚለዋውጥ ፓቶሎጂካል ቀዣባሪ›› የሚል ታሪኩን እንዲያነብ እመኛለሁ፡፡
ከመሞቱ በፊት… ‹‹የእከሱም ሐውልት ለወላይታ ምኑ ነው? ብሎ ለተናገረው ድንቁርና፤ የትግራይ ጨዋ እና ኢትዬጵያውያን መሪዎች፤ ይቅርታ ጠየቁ›› የሚል ዜና በአዲስ ዘመን ላይ ተጽፎ ቢያነብ እመኛለሁ፡፡
ከላይ እንደጠቀስኩት፡፡  ራሱንም፤ የሰራውንም፤ ሳያውቅ ቢሞት ትክክል አይደለም፡፡ የገደላቸው ሁሉ እንዳልሞቱ ሳይሰማ ቢሞት ትክክል አይመስለኝም፡፡ከእርሱ የተሻለ መሪዎች እንዳሉ ሳያይ ቢሞት ጥሩ አይደለም፡፡ ዛሬ ያመሰገኑት ጋዜጠኞች፤ መልሰው ‹‹አምባገነኑ›› ሲሉት ሳይሰማ ቢሞት ፌር አይደለም፡፡ ስለዚህ መለስ አሁን አይሙትብን፡፡
የዲሞክራሲ አንድ ጥቅሙ፤ መሪዎች በሰላም ከሥልጣን እንዲወርዱ ማድረግ ብቻ አይመስለኘም፡፡ መሪዎች፤ የሠሩት ሥራ በታሪክ እና ሕዝብ ፊት ሲዳኝ ቁጭ ብለው እንዲያዩ ማስገደዱም ጭምር እንጂ፡፡

በታሪክ የምናውቃቸው መሪዎች (ከመንግሥቱ ኃይለማርያም በቀር)፤ በሕይወት ቆይተው፤ ፍርዳቸውን ለመስማት፤ ታሪካቸው ምን ተብሎ እንደሚጻፍ ለማየት አልታደሉም፡፡ እስከ መጨረሻ ህቅታቸው ድረስ፤ ራሳቸው የጻፉት ታሪክ እየተነበበላቸው፤ መስማት የሚፈልጉት እየተነገራቸው፤ አንዴ ለጥፍራቸው፤ አንዴ ለቅንድባቸው እየተዘፈነላቸው ነው የኖሩት፤ የሞቱትም፡፡ ለመለስ ይሄን ዓይነት መጨረሻ አልመኝለትም፡፡ የምመኝለት፤ ከእርሱ ቀድሞ፤ ሕልሙ እንዲሞት ነው፡፡ ከሞትማ ማን ይቀራል፡፡
-------

ይሄንን ሌሊት የጻፍኩትን ጽሑፍ፤ አሁን ጠዋት ሳነበው ጊዜ ደነገጥኩ፡፡ ፓለቲከኛ ያላረገኝንም አምላክም አመሰገንኩት፡፡ በዚህ አያያዜ፤ እኔም ራሴ ምህረት የለሽ ፖለከኛ እሆን ነበርና፡፡
------

Saturday, 15 September 2012

የኢትዮጵያዊ ጦማር መለጠፊያ፡የጀግናዉ በላይ ዘለቀ ማስታወሻ

ይህ የጦማር መለጠፊያ ለእናንተ ለኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን በጀግናዉ በላይ ዘለቀ ስም የተዘጋጀ ነዉ። ማንኛዉንም በመረጃ የተደገፈ  ትክክለኛ(fact) እና ሚዛናዊ መረጃ ለመለጠፍ ዝግጁ ነን እናም በሚከተለዉ የኢሜይል አድራሻ ይላኩልን። የኢሜይል አድራሻችን patriotbelay@gmail.com ነዉ።