Sunday, 21 October 2012

አቶ ስብሐትና የተንኮል ፖለቲካ – በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም


Thursday, 18 October 2012

ከረጂም ርቀት ሯጮቻችን የምንማረው ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)


rucኢትዮጵያ በመልካም ስሟም፤በአስከፊ ገጽታዋም ትታወቃለች:: ኢትዮጵያ በመልካም እንግዳ ተቀባይነቷና አስተናጋጅነቷ፤በሕዝቦቿ መልካም ባሕሪ፤ በመልክአ ምድሯ ውበት፤እና በግሩሙ ቡናዋና በማይደፈሩት ጅጋኖች ረጂም ርቀት ሯጮቿ ትታወቃለች፡፡ ተወዳዳሪ በሌለው የሰብአዊ መብት ጥሰት፤የፕሬስ ማፈኛ ተቋሟም፤በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፖለቲካ እስረኞች የሚገኙባት ሃገርም ሆና ኢትዮጵያ ትታወቃለች፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ችጋር (ኤክስፐርቶቹ እንደሚሉት፤ “ሥር የሰደደ የማይነቀል የምግብ እጥረት”) ከውቢቷ ኢትዮጵያ ጋር ከተሳሰረ ዘመናት አልፈዋል፡፡ የሆነው ሆኖ አትዮጵያ ከጭቆና የፈላጭ ቆራጭ አስተዳደር ወደ ዴሞክራሲ ጉዞዋን ጀምረለች፤ ወይስ ኢትዮጵያዊያኖች ከአምባገነኖች አገዛዝ ወደ ነጻነት እየሮጡ ነው ብል ይሻላል?
ላለፉት ምእተ ዓመታት ኢትዮጵያ ዓለም ያደነቃቸውን  ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የማይደፈሩና አልበገር ባዮች የመካከለኛና የረጂም ርቀት ሯጮችን አፍርታለች፡፡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ አህጉር ጭምር ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ ኢትዮጵያዊ አበበ ቢቂላ ነበር፡፡ ሮም ላይ በተካሄደው የ1960ው ኦሎምፒክ የመጀመርያው አፍሪካው የወርቅ ባለድል አበበ ቢቂላ ነበር፡፡ በወቅቱ በቦታው የተገኙ ታዛቢዎች ስለ ድሉ: ሲናገሩ  ‹‹በ1935 ዓም ኢጣልያ ኢትዮጵያን ለመውረር መላውን የኢጣልያ ዲቪዚዮን ማሰለፍ አስፈልጓት ነበር:: ከ25 ዓመታት በኋላ ግን አንድ ጫማ አልባ የሆነ የኢትዮጵያ የክብር ዘበኛ አባል ያንን ጦር በሮም አደባባይ ድል አደረገ›› በማለት ተቹ፡፡ ለአቤ ያ የሃገር ክብር፤ግዳጅ ነበር፡፡ ‹‹ማንም ሊያውቀው ይገባ ዘንድ የምፈልገው፤ሃገሬ ኢትዮጵያ ምንጊዜም ቢሆን ድልን በቆራጥነትና በአርበኝነት ንብረቷ ማድረግ መቻሏን ነው›› ብሎ ነበር አበበ የተናገረው  በወቅቱ፡፡  ይህ ነበር የዚያ ኩሩ ጀግና ተተኪ የማይገኝለት አትሌት ቃል፡፡ አቤ እንደገናም ይህንኑ መሰል ድል እንደገና በ1964 ዓም በጃፓን ቶክዮ ደገመው፡፡ አቤ ድሉን የተቀዳጀባቸው ሁለት ከተሞች በአለም ጦርነት ቀስቃሾች ወዳጅነታቸው ያየለ ከተሞች እንደነበሩ ብዙዎች አልተገነዘቡትም፡፡
ሌሎችም ፈለጉን ተከተሉ፡፡ በ1968 በሜክሲኮ በተካሔደው ኦሎምፒክ ማሞ ወልዴ የማራቶን ድል አድራጊ በመሆን የወርቅ ሜዳልያ አጠለቀ፡፡በ1980 ምሩጽ ይፍጠር በሞስኮው ኦሎምፒክ በ5000 እና በ10000 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሆነ፡፡ በሲድኒም ገዛኸኝ አበራ ማራቶንን ላማሸነፈ የመጀመርያው ወጣት አትሌት ሆኖ በ2000 ዓም የወርቅ ሜዳይ አነገተ፡፡ ባለፉት በርካታ ዓመታት ኃይሌ ገብረሥላሴ ረጃጂም ሩጫዎችን የግሉ በማድረግ በተደጋጋሚ ሁለት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊና እንዲሁም፤ በ10000 ሺ ሜትር  የዓለም ሻምፒዮን ነው፡፡ ኃይሌ በርካታ የሩጫ ሬኮርዶችን በመሰባበር የሬኮርዶች ባለቤት ሲሆን የብዙ የክብር ስሞችም ለስሙ ያስገኘ ነው፡፡ በዓለም ታዋቂ የሆነው ራነርስ ወርልድ፤ የአሜሪካ ታላቁ የስፖርት ጋዜጣ፤‹‹የዓለማችን ታላቁ የረጂም ርቀት ሯጭ›› በማለት ሰይሞታል፡፡ ቀነኒሳ በቀልም በ5000 እና በ10000 ሜትሮች ሁለት የኦሎምፒክና የዓለም ሬኮረዶች በ2008 በቤይጂንግ የጥንድ ባለድል ና ባለቤት ነው፡፡ በተመሳሳይም በአቴንስ ድሉን ደግሞታል፡፡ በዓለም ሻምፒዮንነት ድሉን ለመዘርዘር በጣም በርካቶች በመሆናቸው መዘርዘሩ አዳጋች ነው፡፡
በሴቶችም በኩል ቢሆን የማይተናነስ ድል ያስተናገዱ ጀግኖች አሉን፡፡በ2011 ጢቂ ገላና በ2012 በተካሄደው የሎንዶን ኦሎምፒክ ላይ 2፡23፡07 በሆነ ሰአት አዲስ የኦሎምፒክ ሬኮርድ በማስመዝገብ አሸናፊ ነበረች፡፡ ፋቱማ ሮባም በተመሳሳይ ሰአት በአትላንታ በ1966 በተደረገው የኦሎምፒክ ውድድር የወርቅ ባለድል ነበረች፡፡ ደራርቱም በ10000 ባርሴሎና ላይ በ1992 አሸንፋ ወርቅ አንግታለች፡፡ ጥሩነሽ ዲባባም በቤይጂንግ በ2008 የ5000ና የ10000 የድል ባለቤት ነበረች:: ይህንንም በመድገም በ2012 በሎንዶን ኦሎምፒክ በ10000 የድል ባለቤት ሆናለች፡፡ ባለፈው ሳመንት በችካጎ ከተማ ጸጋዬ ከበደ በ02፡04፡38 ሰአት በሌሊሳ ፈይሳ ተከታይነት በ02፡04፡52፤ረጋሳ ጥላሁንም በሶስተኛነት 02፡05፡27 ሰአት ሲጨርሱ በሴቶችም አጸደ ባይሳ በ02፡22፡03 ቀዳሚ ሆና ወርቅ አጥልቃለች፡፡  የወርቅ የብር የነሐስ ባለድል የሆኑትን፤የማራቶን ጀግኖች የተባሉበትን፤እና በሌላም ተመሳሳይ ውድድር  የዓለም ባለክብረ ወሰን የሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ለመዘርዘር ማለቂያ የለውም፡፡ ብዙዎች የነዚህን ጀግኖች ሚስጥር ማወቅ ይጓጓል፡፡ ሁሉም ተመራማሪዎች ጉዳዩን በሚገባ ካጠኑና ከመረመሩ በኋላ የደረሱበት መቋጫ፤ ‹‹ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ለድል የሚያበቃቸው ሚስጥር ለድል አድራጊንት የሚያድርባቸው ረሃብ ነው›› በማለት ደምድመዋል፡፡
የረጂም  ርቀት ሩጫ ለኢትዮጵያ  ፖለቲካ  እንደ  ተምሳሌትነት
ባለፈው ኖቬምበር 2009 (‹‹የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ወደ ነጻነት በሚል ጦማር ላይ እንደጣፍኩት››) ሁልቆ መሳፍርት የሌላቸው ተሳታፊዎች ለነጻነት ብቻ አይደለም ሩጫቸው፤ከጭቆናና ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ማነቆ ለመውጣትም ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን እነዚህ ሯጮች ሩጫቸው የሚዞርበት ቀለበት ኢትዮጵያ በገባችበት የወህኒ ማነቆ ውስጥ መሆኑ ነው፡፡ የረጂም ሩጫው ለኢትዮጵያ ፖለቲካና ይህችንም ሃገር ከጭቆና አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ ለማሸጋገር ተምሳሌት ሊሆን ይችላል፡፡ ረጂም ርቀት ሩጫ የጉልበት ብርታት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የጠነከረና የቆረጠ የህሊና ጥንካሬም ነው፡፡ረጂም ሩጫ ለመሮጥ ታላቅ የሰውነት ጥንካሬን ከዚያም ሌላ እጅግ የጎለበተ ሃይልና ትእግስትን ይጠይቃል፡፡ ረጂም ርቀት ሩጫ አድካሚ፤አሰልቺ፤ፈታኝ ነው፡፡ ረጂም ሯጮችም የራሳቸውን ሂደት በመጠበቅ፤ልኩን በማስተካከል፤ያንን አቧራማና ውጣ ውረድ ያለበትን ሂደት በውሃ ጥምና በላብ በመደፈቅ፤ከፊት የሚገፋቸውን ንፋስ እየሞገቱ፤ ንዳዱ እያቃጠላቸው፤ከየጡንቻዎቻቸው ያለውን ሃይል እያዳከመ ሲፈትናቸውም ድል እያደረጉ ግባቸውን ይመታሉ፡፡ የርቀት ሯጭ ሁል ጊዜ ዓይኑ አሻግሮ የሚመለከተው፤ድካሙን ሳይሆን በድል የሚጠለቅለትን የአሸናፊነት ሃብል ነው፡፡ ይህን ሁሉ የሚያመጣው ታዲያ እድሜ ሳይሆን፤አመጋገብ ሳይሆን፤ ለስኬት ያለው ጥንካሬና እልህ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ረጂም ርቀት ሯጮች የድል ሚስጢር‹‹ ለማሸነፍ ያላቸው ቁርጠኝነት ነው፡፡›› ይህም ደረጃቸውን ከፍ አድርጎ ለማስቀመጥ የሚያስችላቸውን መመዘኛ ሰርተዋል፡፡እኛም ለዴሞክራሲ በምናደርገው ሩጫ ፈቃደኝነትና የድል ረሃብ ያስፈልገናል፡፡ ለዴሞክራሲ የወርቅ ሜዳልያ የሚገኘው 100 ሜትርን በግል በመሮጥ፤ ወይም 400 ሜትርን በቅብብሎሽ በመጨረስ አይደለም፡፡ የነጻነት የድል ወርቅ ሜዳልያም በ400 የዝላይ ሩጫ ሳይሆን፤በ1500 ሜትርም አስቸጋሪ ሩጫ አይሆንም፡፡ የሁሉም ነጻነቶችና መብቶች የወርቅ ሜዳልያዎች የሚገኙት፤ ከረጂም አድካሚና ፈታኝ፤ በተራራ ውጣ ውረድ፤ አስቸጋሪና ድንቅፍቅፉ የበዛበት ፈላጭ ቆራጭና ጨቋኝ አገዛዝ ከሚገኝበት ከጭቆና ሸለቆዎች፤ ቁጥቋጦ አልባ በሆነው ሕግ በሌለበት ሜዳ፤ ውሃ በደረቀበት በረሃ መቻቻል በማይኖርበት፤ጭካኔና መሃይምነት ከበዛበት ደርሶ በማሸነፍ በሚደረግ የማራቶን ድል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ፤ ለሰብአዊ መብት መከበር በሚደረግ የማራቶን ሩጫ፤ ልክና ደረጃ ማስቀመጥ ይገባናል፡፡ እነዚህ ውጤቶችና ደረጃቸው ምንድን ነው? በመጀመርያ ከሰው አቅም በላይ የሆኑ አይደሉም፡፡ሁላችንም አልፎ አልፎ የምንተገብራቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ሁለተኛ የሰውነት ሁኔታ ውጤቶችም አይደሉም፡፡ግን ስነ አእምሮአዊ፤ የእውቀት፤የእምነት  እንጂ፡፡
የርቀት ሯጮች ትኩረታቸው አንድ አቅጣጫ ነው፡፡ ምልከታቸውን በአንድ አቅጣጫ ግባቸው ላይ አስተካክለው በህሊናቸው እየተመሩ ግባቻውን ማሳካት ነው፡፡ በቀላሉ ከኢላማቸው አይዘናጉም፡፡ የመጨረሻው መግቢያ በር እስኪደርሱ ድረስ ይሮጣሉ ይሮጣሉ እንደገናም ለድል ይሮጣሉ፡፡  ውሃ ጥም ቢጠብሳቸውም፤ድካም ቢሰማቸውም ተስፋ መቁረጥን ሳያስጠጉ ድላቸውን ብቻ በማሰብ በጠንካራ የአእምሮ እሳቤ፤ውጤታማነታቸውን እያማጡ ዓላማቸውን ለግብ አስተካክለው በሩ ጋ ደርሰው ድልን ይወልዳሉ፡፡ ውድድራቸው ከኋላ ከቀረው ወይም ከፊት ከቀደመው ጋር ሳይሆን ረጂም ርቀት አለህ፤ ደክሞሃልና ተወው ከሚላቸው አሳናፊና ተስፋ አስቆራጭ አስተሳሰባቸው ጋር ነው፡፡ እነዚህ የረጂም ሩጫ ርቀት ሙያና የድል ባለቤትነት ሱሰኞች የሆኑት ሯጮች ግን ውጣ ውረዱን ድካሙን ተስፋ አስቆራጩን ሳንካ አስተሳሰብ ያለ የሌለ ጥናካሬና ጉልበት፤ ድልን ለመቀዳጀት ለራሳቸው የገቡትን ቃል በማክበር፤ የድል ርሃባቸውን ለመወጣትና ያንን የወርቅ ሜዳይ ለማጥለቅ ሂደቱን ቀጥለው ድልን ይመገባሉ፡፡ ረጂም ርቀት ሯጮች ዘወትር ከብረት የጠነከረ ቆራጥነት ስላላቸው ሁልጊዜም ለማሸነፍ ዝግጁ ናቸው፡፡ ለድል የሚያበቃቸውን ፕላን ነድፈው ይዘጋጁና በሂደት ያስተካክሉታል፤ እንዲያውም የቸገረ ነገር ከገጠማቸው ጨርሰው እቅዳቸውን ሊለውጡት ይችላሉ:: ለዚህም ፈቃደኛ ናቸው ዝግጁም ሆነው ይጠብቁታል፡፡በዝግጅታቸው ሂደት ሁሉ ስሜታቸውን ከማሸነፍ ጋር እንዳጋቡት ነው፡፡ኃይሌ አንድ ጊዜ ሲናገር ‹‹በቅድሚያ አስፈላጊውን ልምምድ ጠንቅቆ ማድረግ፤ከዚያም በራስ በመተማመን ላደርገው እችላለሁ ብሎ መነሳት፡፡ ነገ የኔ ቀን ነው ብሎ ማመን፡፡ ከዚያም፤ ‹‹ከፊቴ ያለው ሰው፤አሱም እንደማንም ሰበአዊ ፍጡር ነው፤ሁለት እግር አለው፤እኔም ሁለት እግር አለኝ ይሄው ነው በቃ፡፡ በእንዲህ ነው ራስህን የምታዘጋጀው››::  ሲያሸንፉም ድሉ የግላቸው ሳይሆን የሃገራቸውና የሕዝብ ድል ነው ብለው ነው የሚያምኑት፡፡ አቤም ‹‹ዓለም እንዲያውቅልኝ የምፈልገው፤ሃገሬ ኢትዮጵያ ዘወትር በቆራጥነትና በጀግንነት ስሜት ለድል መብቃቷን ነው›› ያለውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡
የረጂም ርቀት ሯጮች ሌሎች የማያዩትን የሚመለከቱበት ራዕይ አላቸው፡፡‹‹ ምንም እንኳን የመጨረሻው የድል ጣቢያ በተራሮችና በወጣ ገባው መሬት ቢጋረድም፤ ግባቸውን በማገናዘብ አሻገረው ከለላውን ጥሰው ያዩታል››::  የመጨረሻዎቹን ቀሪ ርቀቶች በሕሊና አይኖቻቸው በመመልከት ለዚያ ወሳኝ ሰአት በመዘጋጀት በድል ሲገቡና አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ሲያዝመዘግቡ በማየት ለድል ይበቃሉ፡፡ እነዚህ ሯጮች የአእምሮና የመንፈስ ጽናት አላቸውና፤አቅማቸው የሚችለው ብለው ካሰቡት በላይ አቅም እንዲኖራቸው ስለሚያግዛቸው የሰውነታቸውን ድካም የመንፈሳቸውን ስንፈት በመቋቋም፤ለድል ይበቃሉ፡፡ ረጂም ርቀት ሯጮች፤ እጀጉን የጠነከረ በራስ መተማመን ስላላቸውና የጀመሩትን ሥራ በድል የመወጣት ጽናት ስለሚታጠቁ ለድል ይበቃሉ፡፡ለማሸነፍ የሰነቁትን ዓላማና ግብ አይጠራጠሩትም፡፡ ሲሮጡ ወደ ኋላ ከመመልከት ይልቅ በጥንካሬ ወደፊት እየገፉ እያንዳንዷ ማይል ወደ ድል በር የምታቃርብና አሸናፊ እንደምታደርጋቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ረጂም ርቀት ሯጮች ለስርአት የተገዙ፤ እራሳቸውን ለመልካም ስነምግባር ያሳደሩ ናቸው፡፡ምናልባት ሽንፈት ቢያጋጥማቸውና ማድረግ የሚገባቸውን እንዳላደረጉ ቢገነዘቡም፤ በዚያ ስህተት በመቆጨት ቁጭ ብለው በሃዘን ፊታቸውን አይነጩም፡፡ ያን ሁኔታ የፈጠረባቸውን ሰበብ በማወቅ ጉድለቱን አስተካክለው የጎደለውን ሞልተው፤ የሰነፈውን አጠንክረው፤ የደከመውን አጎልብተው  ለሚቀጥለው ድል እራሳቸውን በአግባቡ ያዘጋጃሉ፡፡ ቂም የለም ተስፋ መቁረጥ ጨርሶ ቦታ የለውም፤ ሰበብ አስባብ ፈልገው ሌላውን መውቀስ የነሱ ባህሪ አይደለም፡፡ የዴሞክራሲ ዋጋ፤ ነጻነትና የሰብአዊ መብት መከበር በአጭር ርቀት ሩጫ፤ በቅብብሎሽና በመሳሰሉት የሚገኝ ድል አይደለም፡፡ እጅጉን አድካሚና ፈታኝ የሆኑ ሂደቶችን በመወጣት ብቻ የሚገኝ ነው፡፡ የዴሞክራሲ ሩጫ ለነጻነትና ከጭቆና ለማምለጥ በሚሮጡና፤እነዚህን የነጻነትና የዴሞክራሲ ሯጮች  በሚያሳድዱ ጨቋኞች፤ መሃል የሚካሄድ የማራቶን ሩጫ ነው፡፡ አሳዳጆቹ በሯጮቹ ላይ የበላይነት ያላቸው ስለሚመስላቸው ርቀው ሳይሄዱ ጠልፈው አደናቅፈው ለመጣልና ለማሰናከል የማያደርጉት አንዳችም ተንኮል አይቀራቸዉም፡፡ የሆነው ቢሆንም ግን ሯጮቹ የዴሞክራሲና የነጻነት ፈላጊዎች ቆርጠውና ለዓላማቸው ጸንተው፤ በጥንካሬና በአትንኩኝ ባይ ስሜታቸው ለድል መብቃት ይገባቸዋል፡፡ ለዚህም ነው የዴሞክራሲና የነጻነት ሩጫ አጫጫር ርቅት ሩጫ ሳይሆን የረጂም ርቀት ማራቶን የሚሆነው፡፡
ለነጻነት፤ ለዴሞክራሲ፤ ለሰብአዊ መብት በሚደረገው የረጂም ርቀት ሩጫእያንዳንዳችን  ሯጮች መሆን ይኖርብናል
በአባጣ ጎርባጣው፤ በሸንተረሩ፤ በዳገት ቁልቁለቱ፤ በሚካሄድ የኢትዮጵያ ነጻነት፤ የዴሞክራሲ፤ የሰብአዊ መብት መከበርን ለማረጋገጥ ከዘረኝነት፤ ለመውጣት ረጂም ርቀት ሩጫ ላይ የሚደረገው ውድድር በተለያየ ወቅት ድል አድራጊ አንድ አንድ ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ማለት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕሊናውን አዘጋጅቶ እራሱን በዲሲፕሊን አስገዝቶ፤ልቡን ለድል አስተካክሎና ሞልቶ፤ የድል ማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ጋንዲ እንዳለው ‹‹በዓለም ላይ ማየት የምትሻውን ለውጥ መሆን መቻል አለብህ››፡፡ በቅድሚያ የራሳችንን ጠባብ አመለካከት፤ ጥላቻ፤አለመግባባት፤ጋጠ ወጥነት በማስወገድ፤ ለዴሞክራሲ፤ ለነጻነት፤ ለሰብአዊ መብት መከበር የሚከናወን ‹‹የኦሎምፒክ ማራቶንን››  ማሸነፍ አለብን፡፡ የየግል ድላችንን በ80 ወይም በ90 ሚሊዮን ስናባዛው፤ሃገራችን ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት ሰንቆ ከያዛት ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ፤ከጭቆና ማነቆ ስርአት ወደ 13 የጸሃይ ወራትነት ልንለውጣት እንችላለን፡፡
ከረጂሙ አድካሚና ፈታኝ ፤ ውጣ ውረድ የተሞላበት ሩጫ በኋላ ስላለው የድል ሽልማት ማንም ቢሆን ሊጠራጠር አይገባም፡፡ ይህን አሽቅድድሞሽ ስናሸንፍ፤ለሕብረተሰቡ የሕግ የበላይነት የነገሰባት፤የሰብአዊ መብት የተከበረባት፤ አለአግባብ በስልጣን መጠቀም ተጠያቂነትን የሚያስከትልባት፤መንግሥት በሕዝብ ፈቃደኝነት ላይ ብቻ የሚያስተዳድርባት፤ሕዝቡ ሳይሆን መንግሥት ሕዝብን የሚፈራባት፤ሕዝቡ ያለአንዳች  ፍርሃት በነጻነት፤ የመንግስት ወከባ ሳይኖርበት፤የሚኖርባትን ሃገር ለድል ማብቃታችንን መዘንጋት የለብንም፡፡ ምናልባትም የድል ወርቅ ሜዳይ የምናጠልቅበት ጊዜ ይረዝም ይሆናል:: ስለዚህም የዚህን ማራቶን በቅብብሎሽ መሮጥ ይኖርብናል፤ በዚህም አንዱ ትውልድ ለሌላው በማስተላለፍ ይህን ታላቅ ድል ማግኘታችን የግድ ነው፡፡ የማያጠራጥር ወኔ ከወጣቱ ትውልድ ቆራጥ የወኔ ድል ለቀጣዩ ትውልድ፡፡ ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ፤ የሰብአዊ መብት፤ ርቀት ሯጮች፤እንደ ዓለም ኦሎምፒክ ሯጮች ድካም ሊሰማቸው ተስፋ አስቆራጭ ሃሳብ ሊሞግታቸው የድሉ በር ሩቅና የማይደረስበት መስሎ ሊታያቸውና ድልም የማይታሰብ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ እንዲያውም ወደ ድሉ በር መድረሱ አዳጋች መስሏቸው ለማቋረጥም ይዳዳቸው ይሆናል፤ እራሳቸው ሊከብዳቸው፤ ጡንቻዎቻቸው ሊዝሉ፤ ከማብቂያው በር ለመድረስ ርቀቱ ተስፋ አስቆራጭ ሊሆንባቸው ይሞክራል:: መንገዱ ወጣገባ፤ ቢሆንም የዴሞክራሲ፤ የነጻነት፤ የሰብአዊ መብት ሯጭ ግን እኔም የረጂም ርቀት ሯጮቻችን ደጋግመው እንዳደረጉት ሁሉ ማድረግ ይኖርብኛል፤ ብሎ ቆርጦ መነሳት አለበት፡፡ ሕሊናችንን ‹‹ላደርገው እችላለሁ፤ልናደርገው እንችላለን፤ርቀቱን ጨርሶ አለማሸነፍ ግን ፍላጎታችን አይደለም፡፡ ማንንም ሮጠን ለድል መብቃት ማሸነፍ መብቃት አለብን፡፡ ከዚህ የድል በር ሊያናጥቡንና ሊያጨናግፉን የሚጥሩትን ሁሉ አልፈንና ቀድመን ድል ማድረግ ዓላማችን ነውና ማሸነፍን ለምንም ሳናካክስ ድልን መጨበጥ ይኖርብናል፡፡ ለድል የሚያስፈልገን ይህ ቁርጠኝነት ብቻ ነው፡፡የ‹‹ኦሎምፒክ ማራቶን››
ለዴሞክራሲ፤ ነጻነትና የሰብአዊ መብት መከበር በኢትዮጵያ!
የኛ ድል አድራጊ ሻምፒዮናዎች ከፊት ለፊታቸው የቆመ ዳገት ሲያጋጥማቸው፤ወይም ሃይለኛው ንፋስ ሲሞግታቸው በቀላሉ እጃቸውን አይሰጡም፡፡ ዝናብ ይሁንም ውርጭ፤ በረዶ ይሁን ንዳድ ቃጠሎ፤ከዓላማቸው ጨርሰው አይዘናጉም፡፡ ውድድሩ የተሻለ ገንዘብ ስለማይገኝበት አለያም ሁኔታው ምቹ ስለማይሆን ብለው ተስፋ አይቆርጡም፡፡ ምንም ይሁን ምን ጨርሶ አይተዉትም፡፡ ተስፋም አይቆርጡም፡፡ ለድልና ለክብር፤ ለማንነት ማረጋገጫ ድል፤ ቀድሞ ለመገኘት ብቻ ይተገላሉ ይሮጣሉ ይሽቀዳደማሉ::  ወደኋላ ሳይሆን ወደፊት በመሮጥ እንቅፋታቸውን ሁሉ እያለፉ በድል በር ቀዳሚ ሆነው ብቻ መገኘት ነው ያላቸው አማራጭ፡፡ የማንም ሃይል በጠላትነት ቢሰለፍ ለድል ቆርጠው ተነስተዋልና ዐላማቸውም ያው ድል ብቻ በመሆኑ ለድል ከመብቃት የሚያግዳቸው አንዳችም ነገር አይኖርም፡፡
‹‹ማንም ሊያውቀው ይገባ ዘንድ የምፈልገው፤ሃገሬ ኢትዮጵያ ምንጊዜም ቢሆን ድልን በቆራጥነትና በአርበኝነት ንብረቷ ማድረግ መቻሏን ነው::››  አበበ ቢቂላ

Thursday, 11 October 2012

“የተሰጠኝ ቤት ለደኅንነቴ አያመችም፣ ለፕሮቶኮሌን አይመጥንም”አዜብ መስፍን Source: ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®


አዜብ መስፍን ፈርተዋል!!

“የተሰጠኝ ቤት ለደኅንነቴ አያመችም፣ ለፕሮቶኮሌን አይመጥንም”

መለስ የሚያቆላምጧቸው ወ/ሮ አዜብ ለመቀማጠልና ለደኅንነታቸው በመስጋት ቤተመንግሥቱን “አልለቅም” ማለታቸውን የጎልጉል ምንጮች አረጋገጡ። የአዲስ አበባ መረጃ አቀባዮቻችን እንደሚሉት ከሆነ የቀድሞዋ “ቀዳማዊት እመቤት” ሶስት ቪላዎች እንዲያማርጡ ቢለመኑም አሻፈረኝ በማለት ባነሱት የደኅንነት ጥያቄ ገፍተውበታል።
ከህወሓት መከፈል በኋላ አቶ መለስ ህወሓትን በመዳፋቸው ውስጥ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ገንነው የወጡት ወ/ሮ አዜብ የተባረሩት፣ የተባረሩት ደጋፊዎችና የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ኢህአዴግ ውስጥ ጥርስ የነከሱባቸው ይበረክታሉ። የሥልጣን እርከን በመጣስ ከሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት በተጨማሪ ለሚያካሂዱት የንግድ ስራ ሲሉ መመሪያ በመስጠት፣ የማይፈልጉትንና አልታዘዝ የሚሉዋቸውን ባለሥልጣናት በማስገደድ፣ በተለይም ተወላጅ ሳይሆኑ በህወሓት አመራሮች ላይ ሲያሳዩ የነበረው የበላይነት ዛሬ አደጋ እንዳመጣባቸው የዜናው ምንጮች ይናገራሉ።
የመለስን በጠና መታመምና ይፋ ያልተገለጸ ሞት ተከትሎ፣ ከዚያም “የውድ ባለቤታቸው” ህልፈት ይፋ በሆነ ማግስት፣ ብዙ የተወራባቸው ወ/ሮ አዜብ፣ ባለቤታቸውን “ሲሰናበቱ” የባለቤታቸውን የፖለቲካ አቅጣጫ “ውርስ” የማይበረዝ ከሆነ እንደሚገፉበት የተጠቆሙበትን ቃል አቶ ሃይለማርያም በቀጥታ ቃል በቃል መድገማቸው ወ/ሮ አዜብን “አሁንም የሚደፍር የለም” የሚል አስተያየት እንዲሰነዘር አድርጎ ነበር።
በወቅቱ አንደ አንድ ጉሊት ቸርቻሪ፣ ችግር እንደ ገረፋት ቅጠል ሻጭ እናት “ልጆቼን በማሳደግ እፈተናለሁ” በማለት ሲናገሩ መሳለቂያ የሆኑት ወ/ሮ አዜብ ኢህአዴግ ውስጥ እየጋመ ያለው የውስጥ ለውስጥ ኃይል የማሰባሰብ ሩጫ “ደመራው” ወደ የትኛው ወገን እንዳዘነበለ ባልታወቀበት ሁኔታ ተወጥረው ተይዘዋል።
ለጠ/ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቅርበት ያላቸው ክፍሎች እንደሚሉት ወ/ሮ አዜብ የኃይል ሚዛኑን በበላይነት ከያዙት ክፍሎች ጋር ቢመደቡም በእርሳቸው ጎትጓችነት፣ በባለሃብቶች ጠቋሚነት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር ከኦህዴድ ግምገማ ተርፈው ለወዳጃቸው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መላካቸው ታውቋል።
በአቶ ሙክታር ፊርማ ቤተ መንግስት ለቀው እንዲወጡ አንድ ሳምንት የተሰጣቸው ወ/ሮ አዜብ፤ አቶ መለስ በህይወት እያሉ ለተሰናባች ጠ/ሚኒስትር ባስገነቡት የሚኒሊክ ቤተ መንግስት ውስጥ በሚገኝ ቪላ ለመኖር ያቀረቡት ጥያቄ ወደ ጎን ተብሏል። የጎልጉል ዘጋቢ ባገኘው መረጃ መሰረት ወ/ሮ አዜብ ለጊዜው አድራሻው በግልጽ ያልታወቀ ትልቅ ግቢ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ሌላ ምንጭ ደግሞ ወ/ሮ አዜብ የሚከራከሩት በታችኛው ቤተ መንግስት (ኢዮቤልዩ) ከፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጎን ተጎራብተው ለመኖር እንደሆነ ጠቁመዋል። ሁሉም መረጃዎች እንደሚያስረዱት ወ/ሮ አዜብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አለማግኘቱን ነው።
የቀረቡላቸውን ሶስት ቪላዎች “ለደህንነቴ አይመቹም፤ ለፕሮቶኮሌ አይመጥኑም፤ ሰው ይበዛባቸዋል” በሚል ምክንያት ባለመቀበል ወ/ሮ አዜብ ቤተ መንግስቱን የሙጥኝ በማለታቸው ምክንያት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማለዳ ብስራተ ገብርኤል ከሚገኘው ቤታቸው ሲወጡ፣ ምሽት ላይ ደግሞ ተመልሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ በተፈጠረው የትራፊክ መጨናነቅ ነዋሪዎች መጨናነቃቸውን ሰንደቅ ጽፏል። እርሳቸው ባይፈልጉትም ለደህንነታቸው ሲባል በሚደረገው ጥብቅ ጥበቃ የአካባቢው ሰዎች እንደ ልብ መውጣት መግባት ተስኗቸዋል። ጋዜጣው ወ/ሮ አዜብ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ማስነበቡ በአቶ በረከትና በወ/ሮዋ መካከል የተፈጠረ ችግር ሊኖር እንደሚችል አመላካች እንደሚሆን፣ አሊያም አቶ በረከት ተቀናቃኞቻቸውን ለማግባባት ወ/ሮ አዜብን የመክዳት እርምጃቸውን ለማሳየት የተጠቀሙበት ሊሆን እንደሚችል አስተያየት ተሰንዝሯል።
ወ/ሮ አዜብ በሚኒስትሮች ደረጃ የሚሰጥ ቤት ቀርቦላቸው እንዲያማርጡ መጠየቃቸውን የጠቆሙት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች አቶ ሃይለማርያምን “ልፍስፍስ” ይሏቸዋል። አያይዘውም ክብራቸውን ማስጠበቅና ስልጣናቸውን ባግባቡ መገልገል አለመቻላቸው ወደፊት ሊጎዳቸው እንደሚችል በመጠቆም በተለይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጠንካራ የተሐድሶ ዕርምጃ እንዲወስዱ የሚቀርቡላቸውን መጠነሰፊ ጥያቄዎች የማስፈጸማቸውን ጉዳይ አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡
ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር “ካንደበቷ ትንታግ ይወጣል” በሚል አድናቆትን የሚቸሯቸው ወ/ሮ አዜብ ከደኅንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄ የተለያየ አስተያየት ቢያስከትልም እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ማረፊያቸው እንደሚታወቅ የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል። አያይዘውም ከሜጋ ማተሚያ ድርጅት ስልጣናቸው ሲነሱ አኩርፈው አረብ አገር ሄደው በአንድ ታዋቂ ባለሃብት ሽምግልና ተመልሰው ሃላፊነታቸውን ተረክበው የነበሩት ወ/ሮ አዜብ ጉሸማው ከበዛባቸው በዚሁ በቀድሞው ሽማግሌያቸው አማካይነት ሃብት ተቆርሶላቸው ህወሓትን “ደህና ሰንብት” ሊሉት እንደሚችሉም ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ወ/ሮ አዜብ በትውልድ ቀዬያቸው ነዋሪዎችና አባቶች ክፉኛ የሚወነጀሉና የተወለዱበትን የአማራ ክልል የከዱ እንደሆኑ በመግለጽ የሚቃወሟቸው ጥቂት አይደሉም። የተወለዱበትና እትብታቸው የተቀበረበት ምድር ተቆርሶ ሲወሰድ ዝምታን 
የመረጡ የዘመኑ “ዮዲት ጉዲት” የሚሉዋቸውም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በሁሉም ጎን የተወጠሩትና “ስኳር” ይወዳሉ የሚባሉት ወ/ሮ አዜብ ያላቸው አማራጭ አቶ መለስ ከተወዳጇቸው የእስያ አገሮች ወይም ቀደም ሲል ወዳኮረፉበት አረብ አገር የመዛወራቸው ጉዳይ ሚዛን የደፋ ሆኗል። ወዳጆቻቸው ለ“ለባለ ራዕዩ መሪ” ሲሉ አምባሳደር አድርገው ከሾሙዋቸው የሁሉም ትንቢት ፉርሽ ይሆናል። ሁሉም እንደሚስማሙበት ግን ወ/ሮ አዜብ አገር ቤት አይመቻቸውም። እርሳቸውም አውቀውታል – ከቤተ መንግስት ውጪ!!Source:ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®®

Monday, 1 October 2012

አዲስ አማራጭ ማቅረብ የፖለቲካ እድገት ያሳያል አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)


መግቢያ፤
የኢትዮጵያ ሕዝብ ተከታታይ ችግር፤ የስልጣኑ ባለቤት አለመሆኑ ነው። ይህ ሕዝብ፤ ለመብቱ ስኬታማነት፤ ለሃገሩ ክብርና ግዛታዊ አንድነት ያደረገው ትግል፤ የከፈለው ዋጋ፤ ሁላችንም የሚያኮራ ነው። ለስኬታማነቱ ማነቆ የሆነው ሕዝቡ ሳይሆን፤ ለሕዝቡ ቁመናል የምንለው ድሃው ህብረተሰብ ያስተማረን እኛው ነን። ድክመታችንና ጥንካሪያችን ረጋ ብለን መመርመርም ያለብን እኛው ነን። ኋላ ቀር የሆነ ያፖለቲካ ባህል ይዘን ዲሞክራሳዊ ስርአት ለመገንባት አንችልም። ለውጥ የሚያስፈልገን መሆኑን፤ በሃቅ፤ በጥበብ መመርመርና ብሩህ አማራጭና አቅጣጫ ማቀርብ ያለብን እኛው ነን። በእኛ እድሜ፤ ሶስት የመንግስት ለውጦች አይተናል፤ የአጼ ሃይለስላሴ ንጉሳዊ፤ ፌውዳላዊ፤ የመንስቱ ሃይለማሪም ወታደራዊ አምባገነን ሶሻሊዝም፤ መለስ ዜናዊ ይመሩት የነበረውን፤ የጠባብ ብሄርተኛ የአንድ ፓርቲ የበላይነት። አንጻራቸው ይለያይ እንጅ፤ እነዚህ መንግስታት፤ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ የማህበረሰብ፤ የስራ እድል፤ የትምህርት፤ የሃይማኖት አድሎና የጥቅም የበላይነት አሳይተዋል። የሃይሉ ሚዛን፤ የጥቅሙ ክብደት ተመሳሳይ ባይሆንም፤ ተከታታይ መንግስታት፤ በሃገራችንና በተራው ህዝብ ላይ ያስከተሉት በደል ክብደት ያለው ነው ለማለት ይቻላል። የተራውን ህብረተሰብ ችግር ሊፈቱት አልቻሉም። የመንግስታቱ የበላዮች፤ የገዥውን ክፍል ያገለግሉ ስለነበር፤ የልዩ፤ ልዩ፤ ህብረተሰብ ክፍሎችን ችግር በጥበብና በዘላቂነት ሊያስወግዱት አልቻሉም። ከህዝብ ድምጽና ስልጣን አንጻር ሲታይ፤ ተከታታይ መንግስታት ጥለውልን ያለፉት ችግር እንጅ መፍትሄ አይደለም።
አሁን፤ ይህ አዙሪኝ የሆነ (Vicious Cycle) ጊዜ ያለፈበት የፖለቲካ ባህል እንዲለወጥ ትንሽ ቀዳዳ ተከፍቷል። ዋናው ጥያቄ፤ ይህን እድል ለመጠቀም ምን ያህል ተለውጠናል፤ ተዘጋጅተናል፤ ምን ያህል ፈቃደኛ ነን፤ ምን ያህል ጥበበኛ ነን? ምን ያህል የሃገርና የሕዝብን ጥቅም ከድርጅትና ከግለሰብ ጥቅም በላይ አስቀድመናል? የሚለው ነው። በእኔ እምነት፤ የአሁኑ እድል ካመለጠን፤ ማንንም ለመውቀስ አንችልም፤ መውቀስ ያለብን እኛኑ ነው።
አንድ የምንጋራው አበይት ጉዳይ ቢኖር፤ የህወሓትን/ኢህአዴግን መንግስት ከሁለቱ የሚለየው ዋና ራእይ፤ “በማይታረቅ፤ የብሄር ልዩነት” የታነጸ መሆኑ ነው። በህገ መንግስቱ አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ የመገንጠል መብትን የተቀበለ የገዥ ፓርቲ የሚለው፤ ከተመቸን አብረን እንኖራለን፤ ካልተመቸን እንገነጥላለን ማለት የኢትዮጵያ ህልውና የተረጋገጠ ሳይሆን፤ የገዥው ፓርቲ እንደፈለገ የሚወስነው ሆኗል ማለት ነው። ማን መብት ሰጠው? የገዥው ፓርቲ፤ ይህን በብሄር ላይ የተመሰረተ ቅርጽ፤ በጦር ሃይል በተረዳ መንገድ ተጠቅሞበታል። አሁንም እንዳለ ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ፤ አምባገነንነትን እንደ ተፍጥሮ ህግ፤ እንደ ሕዝባዊ አገልግሎት አድርገው አለምን ያሳመኑበትን ምክንያት እዚህ አልተችም። አልፏል። መጥቀስ የምፈልገው፤ የማይታረቅ የብሄር ልዩነት፤ የአምባገነን ስርአት ልጅ ነው፤ አደጋው ከፍ ያለ የሚሆነውም ለዚህ ነው። የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት የታላላቅ፤ በተለይ፤ የምእራባዊያንን፤ በቅርቡ ደግሞ፤ የቻይናን አመኔታና ድጋፍ በማግኘቱ፤ አገራችን ያልታየ እድገት (Growth) አስመዝግባለች እየተባለ ይነገራል። በሃይል ማመንጫ ግድብ፤ በመንገድ ስራ፣ በትምህርት ስርጭት፤ በጤና ጣቢያወች ስፋት፤ በህንጻ፤ በከተሞች ስፋት፤ ወዘተ ያሳየው ለውጥ ሊናቅ አይችልም፤ የሚታይ ነው።
ሆኖም፤ እድገቱ አያስደንቅም።የማያስደንቅበት ዋና ምክንያት፤ ከአጼ ሃይለስላሴና ከደርግ መንግስታት ጋር ሲንጻጸር፤ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ከልዩ ልዩ ለጋስ መንግስታት፤ ድርጅቶችና የግል ተቋሞች ቢያንስ US$40 billion አግኝቷል። በስደት ላይ የሚገኘው አሁን ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚገመተው ስደተኛ፤ የእድገቱ ተካፋይ ሁኗል። ቢያንስ፤ በአመት ሶስት ቢሊየን፤ ሰቫት መቶ ሚሊዮን ዶላር ይልካል። ተሳትፎው ጎልቶ የሚታየው በተለይ በፍጆት ስራ፤ በቤት ባለቤትነት፤ በግል ህንጻ፤ በምግብ ተቋሞች፤ በሆቴሎች፤ ወዘተ፤ በቤተሰብ፤ ዘመድና ጓደኛ በመደጎም መስክ ላይ ነው። ይህ በፍጆት ላይ የተመሰረተ እድገት፤ መዋቅራዊ ለውጥ አላመጣም፤ ኢትዮጵያ የባሰውን ጥገኛ ሁናለች። ሕዝቡ፤ በተፈጥሮ ሃብቱ ለማዘዝ ከማይችልበት ደረጀ ላይ ደርሷል። የውጭ አገር እንቬስተሮች፤ ሸክ አላሙዲ፤ ወዘተ፤ በሃገራችን አዛዦች ሁነዋል። ተራው ኢትዮጵያዊ በሃገሩ ድምጽ፤ መብት የለውም።
አለም ባንክ እንደሚገምተው፤ ቢያንስ አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የሚደገፉት ስደተኛው በሚልከው ገንዘብ ነው። ሌሎች በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም፤ የእለት ምግብ የሚያገኙት ለጋስ የሆኑ መንግስታትና ድርጅቶች በሚሰጡት ገንዘብ/ርዳታ ነው። ከሁለቱ መንግስታት ጋር ሲወዳደር፤ የሃይለ ስላሴ መንግስት የእርዳታ ማስረጃ መሰብሰብ (Aid flow data) ከጀመረበት አንስቶ ያገኘው US$150 million፤ ይገመታል። ሳይሰረቅ ከስራ ላይ ዉሏል። የወታደራዊ መንግስት፤ በተለይ ከሶቬት ህብረት ለመሳሪያ መግዣ ያገኘውን ጨምሮ፤ 1974-1991 ከUS$3.4 billion ይገመታል። የህወሓት/ኢህአዴ አንድ አስረኛ መሆኑ ነው። አብዛኛው ለመሳሪያ፤ አገር ለመከላከል የዋለ። ደርግ፤ ከአሜርካ፤ ከእንግሊዝ፤ ከአለም ባንክ ለእድገት የሚሆን ርዳታ አያገኝም ነበር። ከህወሓት/ኢህአዴግ በፊት የነበሩት፤ ሁለቱ የኢትዮጵያ መንግስታት ከእርዳታ የተገኘ ገንዘብ በማሸሺ (Massive Illicit Transfer) አልተከሰሱም። ለመስረቅ፤ ብዙም መፈናፈኛ አልነበራቸውም።
በአንጻሩ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በሙስና፤ በአድሎና ፤ከህግ ውጭ ገንዘብ በማሸሺ በሃገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያውን ቦታ ይዟል። በአመት፣ ቢያንስ፤ US$ 3 billion ከህግ ውጭ ከሃገር ይወጣል፤ ይሰረቃል። ሙስናና ከህግ ውጭ የገንዘብ ሽሽት ባይኖር፤ ስርአቱ ተሳትፏዊና ፍትሃዊ ቢሆን፤ የኢትዮጵያ የእድገት ደረጃ ከፍ ባለ ነበር። ቢያንስ፤ ሕዝቡ፤ አስተማማኝ የምግብ ዋስትና ያገኝ ነበር። የስራ እድል በብዛት ይከፈት ነበር። የዋጋ ግሽፈት ሊገታ ይችል ነበር፤ ወዘተ። የተገኘው እድገት ዘላቂነትና ፍትሃዊ ሊሆን አልቻለም የምለው ለዚህ ነው። የእድገት ዋና መለኪያው የጥቂት ግለሰቦች ገቢና ኑሮ ተአምራዊ በሆነ ገጽታ ማደግ ሳይሆን፤ የአብዛኛው ህዝብ ኑሮ መሻሻል ሲያሳይ ነው። “የእድገታዊ መንግስት” አመራርና ፖሊሲ ለፍትህ የታሰበ አይደለም። የነፍስ ወከፍ ገቢ ፍጹም ድሃ ከተባሉት እንደ ናይጀር፤ እንደ ዝምባብዌ ካሉት ሊለይ ያልቻለው ለዚህ ነው። ዋናው መለኪያ፤ የአፍሪካ አማካኝ የነፍስ ወከፍ ገቢ US$1,070 ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አሁንም US$365 (በአመት) መሆኑ ነው።
“አስደናቂ እድገት ተጎናጽፋለች” በምትባለው ኢትዮጵያ የገቢ ልዩነት እየሰፋ መሄዱ፤ በድሃና በሃብታም መካከል ያለው የኑሮ ልዩነት አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱ፤ ሊገታ የማይችል የዋጋ ግሸፈት የሰውን ኑሮ መጉዳቱ፤ የወጣቱ እድል ተምሮ መሰደድ ተደጋጋሚ መሆኑ፤ ወዘተ፤ ፖሊሲውና መዋቅሩ የፈጠራቸው፤ ያለለውጥ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ ብቻውን ሊፈታቸው የማይችል መሆኑን የሚያሳዩ መለኪያወች ናቸው። “እድገታዊ መንግስት” የተባለው የገዥውን ፓርቲ ባለስልጣኖችና የጥቂት ቤተሰቦችን የኢኮኖሚ የበላይነቱን አስተጋባ እንጅ ዘላቂነትና ፍትሃዊ የሆነ፤ ህይወት ለዋጭ የሆነ እድገትን አልገነባም። ለዚህ የተዛባ የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት አስተዋጾ የሚያደርገው ግልጽነት፤ በህግ የሚተዳደር ውድድር አለመኖሩ ነው። የገበያ ውድድር፤ ያለነጻነት፤ ያለህዝብ ድምጽና ቀጥተኛ ተሳትፎ ሊኖር አይችልም። የሰው ሃይል፤ የተፈጥሮ ሃብት፤ የውጭ እርዳታ፤ የሃገር ውስጥ ገቢ የሚባክነውም ለዚህ ነው። ስርአቱ ለፍትህ፤ ለሰላም፤ ለእርጋታ፤ አብሮና ተቻችሎ ለመኖር ጫና ማድረጉ፤ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ለማጥፋት፤ የሚደረግውን ጥረት ይገታዋል። ለዚህ መፍትሄ የሚሆነው መላውን የህብረተሰብ ክፍሎች በሃገራቸው ሙሉ ተሳታፊ ማድረግ ብቻ ነው። የገዥው ፓርቲ፤ እነዚህን ችግሮች በከፊልም ቢሆን፤ ቀንሷል ቢባል፤ ህወሓት/ኢህአዴግ ሃገራችን ከኋላ ቀርነት፤ ከርሃብ፤ ከስደት፤ ከጥገኝነት፤ ከተስፋ መቁረጥ ነጻ ለማድረግ አልቻለም። የፖለቲካ፤ የህብረተሰብ፤ የኢኮኖሚ ምህደሩ (Political, Social and Economic Space) መስፋት ያለበት ለዚህ ነው። የጋራ ችግሮችን በጋራ ለማሰወገድ የሚቻለው፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብቱ ተጠብቆ በሃገሩ ሰርቶ፤ ተከብሮ፤ ተንቀሳቅሶ፤ ኑሮውን ለማሻሻል ሲችል ብቻ ነው።
ሁሉም አለም አቀፍ ዘገባወች የሚያሳዩት፤ ገዡው ፓርቲ የፈጠራቸው የፖሊሲ ችግሮች ለሃገርና ሕዝብ ማነቆ መሆናቸውን ነው። World Economic Forum (2012-2013) ፤ ተቋሞችን፤ አስተዳደርን፤ ህግን፤ ነጻነትን፤ ሙስናና አድሎን፤ የሃብት ሽሽትንና ሌሎች መለኪያወችን ተጠቅሞ ያወጣው ዘገባ ባሳየው መሰረት፤ ኢትዮጵያ ከመቶ አርባ አራት አገሮች መቶ አስራ ስምንተኛ (118th out of 144 countries) ናት። በተለይ በጤና አገልግሎት፤ በትምህርት ጥራት፤ በገብያ ውድድርና ቅልጥፍና፤ በባንክ አገልግሎት፤ በሙስና፤ የሚታየው ዘገባ አሳፋሪ ነው። ዘላቂነትና ፍትሃዊ እድገት ካለ፤ እነዚህ መለኪያወች ከአመት ወደ አመት እየተሻሻሉ በፍጥነት ከሚያድጉ አገሮች ጋር ተወዳዳሪ መሆን ነበረባቸው፤ አይደሉም።
Freedom House ያወጣው Freedom in the World 2012 Index በተለይ፤ የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶች ዘገባ፤ የኢትዮጵያን ኋላ ቀርነት በግልጽ ያሳያል።
የአፈና “ወረርሽኝ” ተቋማዊ ሲሆን፤
ይህ ዘገባ፤ ነጻነት ያላቸውንና የሌላቸውን አገሮች በማወዳደር፤ “ነጻ የሆኑ ህብረተሰቦች ማለት ምንድን ነው” ብሎ ይጠይቃል። ትርጉሙ፤ in societies that are free, “There is open political competition, a climate of respect for civil liberties (and human dignity), significant independent civic life and independent media.” ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያ በፍጹም የለም። የከለከለው ገዥው ፓርቲ ነው። እንዲያውም፤ ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገች ነው በተባሉበት ባለፉት አስር አመታት አፈናው እየባሰ እንጅ እየተሻሻለ አልሄደም። ዘገባው ያቀረበውን እንይ። “Five of the ten countries that registered the most significant declines in the Freedom of the World Report over the two-year period (2010-2011) were in Africa: Ethiopia, Gambia, Burundi, Rwanda and Djibouti….Ethiopia continued a decade-long trend of authoritarianism with the government of Prime Minister Meles Zenawi making increased use of anti-terrorism laws against the political opposition and journalists.”
የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነን መንግስት በተለይ፤ በተቃዋሚ ፓርቲወችና በጋዜጠኞች ላይ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጫና፤ አፈና የሚያደርግበት ለምን ነው? ስልጣኑና የኢኮኖሚ ጥቅሙ እንዳይዛባ ነው። የፖለቲካ ውድድር ካለ፤ ተቃዋሚው አማራጮችን ለሕዝብ ያቀርባል፤ ካቀረበ፤ የመመረጥ እድሉ ከፍ ይላል፤ ምርጫ ዘጠና ሰባት ያሳየው ይህን ነው። የገዥው ፓርቲ የበላዮች ከሁሉም የሚፈሩት ነጻ የሆኑ ጋዜጠኞች እውነቱን ለሕዝብ ያለገደብ ማቅረባቸውን ነው። የሚድያ ቁጥጥር የሚጠቅመው ሕዝቡ እውነቱን በቀጥታ ለማግኘት እንዳይችል በመደረጉ ነው። ከጠበንጃ፤ ከመትረየስ የበለጠ መሳሪያ እውቀትና ያልተበረዘ ዜና ሕዝብ ማግኘቱ ነው። ለዲሞክራሲ ቁልፍ መሳሪያ ነጻ መዲያ መሆኑን የገዥው ፓርቲ የበላዮች ጠንቅቀው ያውቃሉ። የሚገቱት ለዚህ ነው።
ሌላ ቀርቶ፤ የኢትዮጵያን እድገት አድናቂ የሆኑ መንግስታትና አበዳሪ ድርጅቶች ያለውን ጫናና አፈና ያውቁታል፤ በውስጥ ይነጋገሩበታል፤ ያምኑበታል። ጠለቅ ብሎ ያየ ታዛቢ፤ አገር ወዳድ፤ የገዥው ፓርቲ ተራ አባል፤ የጦር ሃይሎች አባል፤ የውጭ ተመልካች፤ ህወሓት/ ኢህአዴግ እነዚህንና ሌሎችን አገራዊ ችግሮች ብቻውን ሊፈታቸው እንደማይችል ይገነዘባል። ችግሮቹ ካልተፈቱ፤ ዘላቂነትና ፍትሃዊ እድገት እንደማይኖርም ያምናሉ። በሁሉም ኢትዮጵያዊያን በኩል የአመለካከት ለውጥ አስፈላጊ የሚሆነው፤ አብሮ ተባብሮ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ሁሉን አቀፍ የሆነ የመንግስት ስርአት መፈጠር ያለበት ለዚህ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የማይፈልገው፤ እስካሁን እንደነበረው አመራር “በጠላትነት እየተያዩ፤ ሆድና ጀርባ ሁኖ” መኖርን ነው። ለምን? እንኳን በሃገር ደረጃ፤ በቤተሰብ ደረጃም ቢሆን፤ በጠላትንትና በጥላቻ ባህል የጋራ ችግሮችን ለመፍታት አይቻልም። የሌሎች አገሮች ምሳሌ እንደሚያሳየው፤ ፍትሃዊ፤ ሁሉን አቀፍ፤ ለሁሉም አገልጋይ በሆነ የመንግስት ስርአትና አመራር ፓርቲወች በጠላትነት አይተያዩም፤ ጠላትነት የሚመነጨው ዲሞክራሳዊ ስርአትን ከመፍራት ነው። ልዩነትን እንደ ጠላትነት ከመመልከት ልምድ ነው። አድሏዊ መንግስት ለፍትህ የቆመ ተቃዋሚ ሁሉ፤ ጠላት አድርጎ የሚያሳድደው፤ የሚገድለው፤ የሚያስረው፤ ከሰላም፤ከነጻነት፤ ከዲሞክራሲ ይልቅ መረጋጋትን (Permanent Instability and Suspence) ስለሚመርጥ ነው።
አዲስ የለውጥ ምእራፍ፤ አዲስ አቅጣጫ፤ ዛሬ፤
የዚህ አቅርቮት ዋና አላማ፤ የሃገራችን ሁለ ዘርፍ የሆኑ ችግሮች በጋራ ሊፈቱ ይችላሉ የሚል ነው። አገራዊ ችግሮችን በጋራ ለማሰወገድ ከተፈለገ፤ የአንድ ፓርቲ የበላይነት አገዛዝ በአስቸኳ መለወጥ አለበት። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የስልጣኑ ባለቤት መሆን አለበት። መንግስትና መሪወች የሕዝብ ተገዥ፤ የሕዝብ አገልጋይ፤ የህዝብ ድምጽ አዳማጭ መሆን አለባቸው። አዲስ የለውጥ ምእራፍ ማለት እንደዚህ ነው። ለእውነተኛ የዲሞክራሳዊ መንግስት መቋቋም እውቅትና ብልሃት ያለው ሽግግር ማድረግ አሰፈላጊ ነው የሚለውን መሰረተ ሃሳብ ህወሓት/ኢህአዴግና ተቃዋሚ ሃይሎች ከተጋሩ፤ (መጋራት አለባቸው ብየ አምናለሁ)፤ ወደዚህ የሚያደርሱ ቅድመ ሁኔታወችን (Favorable Conditions) መፍጠርና ማመቻቸት የሁሉም፤ በተለይ የገዡ ፓርቲ መሪወች ታሪካዊ ሃላፊነት ነው።ማሰብ ያለባቸው፤ አምባገነናዊ አገዛዝ ከአሁን በኋላ ለገዥውም ፓርቲ የበላዮች አያዋጣም። ሰላም፤ እርጋታ፤ አይኖርም። አንዱ በይ፤ አንዱ ጦም አዳሪ፤ አንዱ በስር ቤት ነዋሪ፤ አንዱ በቤተመግስት ወይንም ቪላ ኗሪ፤ ሆኖ ሰላምና እርጋታ ይኖራል ማለት ዘበት ነው። ለኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት፤ ለመላው ሕዝቧ ሰላም፣ ለፍትህ፤ ለብልጽግና፤ ለእኩልነት፤ ለነጻነት፤ ለከብር፤ ከርሃብ አለንጋ፤ ከጥገኝነትና ከስደት፤ ነጻ ለመሆን፤ ቁመናል የሚሉ መንግስታት፤ ተቋሞችና ግለሰቦች ሊረዱን የሚገባቸው የገንዘብ ወይንም የምግ እርዳታ በመስጠት አይደለም። ፍትህ ካለ የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱን ይችላል፤ አገሩን ዘመናዊ ያደርጋል። ሊረዱን የሚችሉት፤ ህወሓት/ኢህአዴግና ተቃዋሚ ሃይሎች በሙሉ በአስቸኳይ ሁሉን አቀፍ የሆነ፤ ለሰላም፤ ለእርቅ፤ ለፍትህ፤ ለዲሞክራሳዊ ስርአት ሽግግር፤ አገራዊ ስብሰባ እንዲያደርጉ አስተዋጾ በማድረግ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ይህን አዲስም እራፍ ከፋች ሊሆኑ ይችላሉ። ለታሪክ ትተውት የሚያልፉት አስተዋጾ ይህ ነው። ካለፉት ጠቅላይ ሚንስትር የሚለያቸውም ይህ ነው። የእኮኖሚ ተሃድሶ ሊመጣ የሚችለው የፖለቲካና የመንፈው ተሃድሶ ሲኖር ብቻ ነው። አለበለዚያ፤ የዛሬ አምስት አመት፤ አለም አቀፍ ዘገባወች የሚያሳዩት ተመሳሳይ ውጤትን ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ፤ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ የሃገራችን ችግሮች እኛው ተመካከረን፤ እኛው ተደራድረን፤ እኛው ተሰብሰበን፤ እኛው መፍትሄ ለመስጠት እንችላለን የሚል የአስተሳሰብ ውሳኔ ማድረግ አለብን። ይህን ለማድረግ ኢትዮጵያንና መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ማእከል ማድረግ አለብን (Place Ethiopia’s National Inerest and the Interests of all of the Ethiopian People on the Radar Screen and subordinate individual and partisan interest)፤ የቀረው ይከተላል። ይህን ካደረግን በአምስት አመታታ ውስጥ፤ ዛሬ ጋና ነጻ ከተባሉ የአፍሪካ አገሮች ከደረሰችበት ለመድረስ እንችላለን። ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማሪያም ወደዚህ አላማ ለመጓዝ ጥረት ማድረግ አለባቸው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብሯቸው እንደሚቆም አልጠራጠርም።
ሽግግር ሲባል ምን ማለት ነው?
ሁሉን አቀፍ አገራዊ ውይይት አካሂዶ፤ የእርቅ/የዲሞክራሳዊ ስርአት ግንባት ድልድይ የሆነ ጊዜአዊ መንግስት መመስረት ማለት ነው። ይህ በውይይት እንጅ በዛቻ፤ በፉከራ፤ በመለፍለፍ የሚገኝ አይደለም። ለዚህ ለተቀደሰ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሚመኘው አላማ፤ መንፈሳዊ አባቶች፤ የሃገር ሽማግሌወች፤ የታወቁ ምሁራን፤ ወዘተ ድልድይ ሁነው “ተሰብሰቡ፤ ተነጋገሩ፤ አገራችንና ጉራማይሌ ሕዝቧን አስቀድሙ፤ መወነጃጀልን አቁሙ፤ “ታሪክ ያላችሁና ጥበበኛ መሆናችሁን ለአለም ህብረተሰብ አስመስክሩ” ሊሉና የመተማመን ቅድመ ሁኔታን ሊያጠናክሩ ይችላሉ። የድርድር ምርኩዞች፤ አገራዊ አንድነት፤ ሰላም፤ እርቅ፤ ይቅር ባይነት፤ እኩልነት፤ የህግ የበላይነት፤ ነጻ ምርጫ፤ የፖለቲካ ውድድር፤ ዲሞክራሳዊ ስርአት፤ ሰብአዊ መብቶች፤ ሊሆኑ ይችላሉ። ሌሎችን የኢትዮጵያ ሕዝብ በውይይት፤ በምርጫ ሊወስናቸው ይችላል።
ይህን ስል፤ ህወሓት/ኢህአዴግ ጥቅሙን ወደ ጎን ትቶ፤ ለሰላምና፤ ለእርቅ፤ ለድርድርና ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ግንባታ በሩን በቀላሉ ይከፍታል የሚል “ቅዠት” ውስጥ አልገባም። ጉዞው ቀላል አይሆንም። በመጀመሪያ፤ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች፤ ግለሰቦች፤ ስብስቦች ሁሉ፤ መሰብሰብ፤ መደጋገፍ፤ በአንድ ድምጽ፤ ለአንድ አገራዊና ሕዝባዊ አላማ መቆም አለባቸው። አገር ውስጥ፤ አገር ውጭ የሚባለው ልዩነት መጥፋት አለበት። ይህን ካደረጉ፤ የአለምን ህብረተሰብ፤ በተለይ፤ የደጋፊ መንግስታትን አቋም ሊለውጡ ይችላሉ። ገዥውን ፓርቲ፤ ለድርድር ከሚያስገድዱበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ያለው እድል ከፍ ይላል። ሕዝቡ እንዲደፋፈር ያደርጋል፤ ወጣቱ ትውልድ በብዛት ወደዲሞክራሳዊ ግንባታው፤ ወደ ሰላማዊ አመጹ (Popular, peaceful resistance) እንዲገባ ያበረታታል። የፍርሃትን ባህል ይቀንሳል፤ ወዘተ። ይቻላል ብለን ማሰብ ይረዳል። የገዠውን ፓርቲ ለማሳፈር/ለማጋለጥ ለሚደረገው ትግል አስተዋጾ ያደርጋል። ከውጭ ያለነው አገር ቤት ከሚታገሉ ሃይሎች ጋር የጠነከረ ግንኙነት መፍጠር አለብን፤ የገንዘብ እርዳታ በዘላቂነት መስጠት አለብን።
ያልተሞከረው መሞከር አለበት የምለው ለዚዝ ጭምር ነው። ሆኖም፤ የሰላማዊ አገራዊ ሁሉን አቀፍ ስብሰባና ድርድር ጥሪ፤ ቀላል ይሆናል የሚል ግምት የለኝም። ምኞትና ህልም ሁኖ ሊቀር ይችላል፤ መሞከር አለበት የሚል እምነቴ ግን ጠንካራ ነው። ለዚህ ስኬታማነት ቅድመ ሁኔታወችን ተጠቅሞ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ሊያደርግ የሚገባውን ጥያዌወች ለአለም ሕዝብና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለመሰልቸት፤ ማቅረብ፤ ማስረዳት የተቃዋሚወችና የእያንዳዳችን ሁሉ ሃላፊነት ነው።
ከጦርነት ባህል፤ ወደ እርቅና ድርድር ባህል መራመድ ለሃገራችን ዘላቂነት፤ ለመላው ሕዝቧ፤ ፍትሃዊ/ተሳታፊያዊ እድገት ይጠቅማል። ዘመናዊ የፖለቲካ ባህል ማለትም ይህ ነው። ቂም በቀልነት፤ እብሪተኝነት፤ “እኔ ብቻ ነኝ አዋቂው” ባይነት ካልቆመ የትም አንደርስም።
ቅድመ ሁኔታ ምን ማለት ነው? ምን ያካትታል?
“የምርጫ ዘጠና ሰባት የፖለቲካ መንፈስ” አለ ለማለት የሚያስደፍሩ ምልእክቶች አሉ። ዋናው መለኪያ፤ ሕዝቡ ለዲሞክራሳዊ ለውጥ ያለው ጉጉት ነው። አሁንም አልጠፋም። ለዚህ የቆሙለት በእስር ቤት የሚሰቃዩ፤ በድብቅ የሚሰሩ፤ በውጭ የሚታገሉ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ በነጻነት እንዲሰሩ ከባድ ጫና ቢያደርግም፤ አገር ቤት ሁነው ቀንና ሌሊት የሚታገሉ የሰላማዊ ለውጥ ደጋፊወች፤ ጠበቃወች፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ጋዜጠኞች አሉ። በተለይ ወጣቶች። ቅድመ ሁኔታወች ይመቻቹ ስል፤ መግለጫ የማደርገው ከዚህ በፊት ቅንጅት/ህብረት ያቀረባቸውን ስምንት አንኳር ጥያቄወች ነው። ጥቅማቸው፤ ተገቢነታቸው አልተለወጠም። እነዚህም፤
i) ህወሓት/ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው የምርጫ ቦርድ በአዲስ መልክ ይዋቀር፤ ከገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሆኖ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያለ አድሎ ያገልግል፤
ii) ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲወች፤ የማህረሰብ ድርጅቶች፤ ግለሰቦች መገናኛ ብዙሃን የመጠቀም መብታቸው ይጠበቅ:: የፕሬስ ነጻነት ከስራ ላይ ይዋል፤ የፕሬስ ነጻነት ገደብ የሆነው፤ የሽብርተኝነት ህግ ተብሎ ንጹህ ኢትዮጵያዊያን የሚታሰሩበት ህግ ይወገድ፤
iii) የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ይፈቱ፤
iv) የጦር ሃይሎች በሙሉ፤ በፖለቲካ ውድድር ውስጥ ጣልቃ መግባታቸውን ያቁሙ፤ ከገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሁነው፤ አገራቸውንና መላውን ሕዝብ ያገልግሉ፤
v) የህግ ተቋሞች፤ ፍርድ ቤቶች በሙሉ ከማንም ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሁነው፤ ህብረተሰቡን ያገልግሉ፤
vi) ከገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ የሆነ ኮሚሽን ተቋቁሞ ሁሉንም ግድያወች ይመርምር፤
vii) የፓርላማ አስተዳደር/አሰራር ዲሞክራሳዊና ግልጽነት ባለው መንገድ ይስራ፤
viii) ከላይ ያሉትን ሁሉ የሚያስተናግድ/ የሚዳኝ ከገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ የሆነ ኮሚሽን ይቋቋም የሚሉ ናቸው።
እነዚህን ጥያቄወች ከስራ ላይ ለማዋል እስካሁን በአምባገነኑ መንግስት ያልተደረገ የፖለቲካ ባህል ለውጥ፤ ሂደትና አቀራረጽ አስፈላጊ ነው። በመጀመሪያ፤ ፈቃደኛነት ማሳየት ያለበት ገዥው ፓርቲ ነው። የኢህአዴ መንግስት፤ ኢትዮጵያንና መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ማእከልና ተቀዳሚ አድርጎ ፤ ለነገዋ ኢትዮጵያ፤ ለሰላም፤ ለሕዝብ ስልጣን የበላይነት፤ ለእውነተኛ እኩልነት፤ለእርቅ፤ ለመግባባት፤ በውይይት ልዩነቶችን ለመዳኘት መሞከር ታሪካዊ ጥሪ እንደሆን ካየው፤ እንዚህን ቅድመ ሁኔታወች በስራ ይተረጉማል የሚል ግምት አለኝ። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ይህን ለማድረግ ትምህርቱም፤ የስራ ልምዱም፤ ቅንነቱም፤ የአቀራረብ ችሎታውም አላቸው። ፈቃደኛ መሆናቸውን የምናየው ወደፊት ቢሆንም፤ ማበረታታ እንጅ ማነቆ መሆን የለብንም።
ሆኖም፤ ተቃዋሚ ሃይሎች በሙሉ ተባብረው ድምጽ ካላሰሙ፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመሩት መንግስት ወዶ አያደርገውም የሚሉ ብዙ ናቸው። የሃገራችንና የሕዝቧን ታላቅነት የሚያሳይ ይህ መንገድ መሆኑን መቀበለ ግዴታ መሆኑን ለአለም ሕዝብ ማሳሰብ ጠቃሚ የሚሆነው ለዚህ ነው። ውጭ ያለው ተቃዋሚ በቅንነት፤ ባንድነት ከሰራ፤ የአለምን ሕዝብ አስተሳሰብ ለመለወጥ ይችላል። ሰላም፤ እርቅ፤ ይቅር ባይነት፤ ለወደፊቱ ትውልድ ማሰብ፤ የአገርን፤ የህዝብን ችግሮች በጋራ ለማስወገድ መሞከር ያለመድነው ባህል መስሎ ይታያል፡፡ ራስን፤ ጥቅምን ካላስቀደምን በስተቀር፤ ባህሉ አለን። ኢትዮጵያ ለብዙ ሽህ አመታት ክብሯን፤ ነጻነቷን ይዛ የቆየችው ልዩኑነቶችን በማቻቻል፤ አብሮ መኖርን በማጠናከር፤ በጋራ ቁሞ፤ የውጭ ጠላትን በመከላከል ነው። ህወሓት/ኢህአዴግ ከተከለብን መርዝ አንዱ፤ በዘር መለያየቱ ነው። ወደኋል ዞር ብሎ የመቻቻል ባህልን አድሶ መጠቀም፤ የሃገራችን ሕዝብ ታላቅነት የሚያሳይ እንጅ የድክመት ምልክት አለመሆኑን በተግባር ማሳየት ያለብን እኛው ነን። በዘር ልዩኑት የተበከለ መርዝ ለእኛ ድክመት፤ ለሃገራችን ጥገኝነት፤ ኋላ ቀርነትና ድህነት መሳሪያ መሆኑን ሌላው ሳይቀር አገራችን አንጡራ ሃብቷን፤ የባህር በሯን አሰብን ማጣታችን ብቻ ይመሰክራል። ሁሉን አቀፍ ለውጥ የሚጠቅመው ያለፈውን ስህተት አንዳንደግም፤ ብሩህ የሆነ በር እንድንከፍት ስለሚረዳ ጭምር ነው። አብሮ ተባብሮ የሃግርን ችግሮች ማስወገድ፤ ታላቅ የሆነች፤ በፍጥነት የምታድግ ኢትዮጵያን ይፈጥራል፤ መላውን ሕዝቧን ከድህነት፤ ከስደት ነጻ ያወጣል።
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር፤ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለዚህ አዲስ ምእራፍ አስተዋጾ እንዲያደርጉ ማበረታታት የሚያስፈልግው ለዚህ ጭምር ነው። በርሳቸው የሚመራው የኢህአዴግ መንግስት ለድርድር ክፍት መሆን የድክመት ምልክት አይደለም፤ ለሃገር፤ ለመላው ሕዝብ የመቆም ምልክት ነው። ለእውነተኛ ዲሞክራሲ፤ ለጭቁን ብሄር/ብሄረሰብ ፍትህ፤ ለነጻነት፤ የመቆም ምልከት ማለት ይህ ነው። በአንጻሩ፤ ለሰላማዊ ድርድር፤ ለእውነተኛ የህዝብ ስልጣን የሚያሸጋግር መንገድ፤ ለፍትህ አለመዘጋጀት የአንድ ፓርቲ አምባገነን አገዛዝ አሁንም ይቀጥል እንደማለት ነው። ይህን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲረዱት፤ ተቃዋሚ ሃይሎች ሁሉ በጋራ፤ ሃየለማሪያም ደሳለኝ፤ ለፍትህ፤ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እስከቆሙ ድረስ፤ አብሯቸው እነደሚቆም ማሰማት ያለበት አሁን ነው።
የመከላከያ ተቋሞች አገራዊ ይሁኑ፤
የኢትዮጵያ የደህንነትና የመከላከያ ሰራዊት የአምባገነን መንግሥት ስርአት ጠባቂና ተከላካይ ሆኖ በ”ጥቁር ቀለም” ታሪክ እንዲፈረጅ መፍቀድ የለበትም። ቃል በገባው የህዝብ አደራ መሰረት፤ የአንድ ፓርቲ የበላይነት ማገልገል ሳይሆን፤ የወገኑን ብሶት በማየት፤ “የጉራማይሌ (Diverse/Mosaic)” ሕዝቡን አለኝታነትና ክብር፤ የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት ብቻ እንዲያስቀድም፤ መመሪያው እንዲያደርግ ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው። ዘጠና በመቶ የሚሆነውን ተራ አባል፤ መካከለኛ እዝ፤ ከአንድ ብሄር የተወጣጣው የበላይ እዝ ሊወክለው አይችልም፤ አይገባም፤ ብለን አደራውን እንዲወጣ፤ ሃይሉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጫና እንዳያደርግ፤ ወገኑን እንዳይገድል፤ መቀስቀስ አለብን። ለዚህ፤ የቅርብ ምሳሌ አለ።
ውጣ ውረድ ቢያሳይም፤ የግብጽን የጦር ሃይልና የስለላ ድርጅት ከሶሪያው የሚለየው፤ የህዝብ አመጽ ሲነሳ፤ ታንክ፤ የጦር አውሮፕላን፤ መትረየስ፤ የጠበንጃ አፈሙዝ ወደ ሰላማዊው የግብጽ ህዝብ አላዞረም። ባለማዞሩም፤ የእርስ በእርስ እልቂት ዝቅተኛ ነው፤ የጦር ሃይሉ ከህብረተሰቡ ጎን ቁሟል። አገራዊ እንጅ የገዡ ፓርቲ አገልጋይ አለመሆኑን አስመስክሯል። የኢትዮጵያ የጦር ሃይል የሚያኮራ ታሪክ ሊሰራ ይችላል ብየ የምገምተው፤ የራሱ የሚያኮራ ታሪክ ስላለው፤ አገር ወዳድ ስለሆነ፤ አብዛኛው ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ጠንካራ ስለሆነ፤ ጭምር ነው። የሰላም፤ የእርቅ፤ የነጻነት፤ የፍትህ፤ የዲሞክራሳዊ ስርአት ግንባት፤ የመወያየት፤ አብሮ ችግሮችን የመፍታት ጥሪን እንደሚደግፍ ተስፋ የማደርገው ለዚህ ነው። ጠንካራ ኢትዮጵያ ልትኖር የምትችለው ጠንካራና በነጻነት የሚኖር፤ ያለ አድልወ የሚሰራ፤ ሕዝብ ሲኖር ብቻ፤ ነው የሚለውን እሴት ሊቀበል እንደሚችል መገመት አለብን። ጠንካራ ሕዝብ ያለ ፍትህ፤ ያለ መብት፤ ያለ ክብር፤ ያለ ነጻነት፤ ያለ እኩልነት፤ ሊኖር አይችልም ብለን ለመላው አለም ማስረዳት ያለብን እኛው ነን። ይህን የኢትዮጵያ ጦር ሃይል ያውቃል። ጥሪው ሃይሉን የሚመለከተው ለዚህ ጭምር ነው።
ከለቅሶው ባሻገር እንይ፤
የኢትዮጵያ ሕዝብ አገር አቀፍ በሆነ ሁኔታ፤ ተገዶም ሆነ ፈቅዶ ለመለስ ማልቀሱ በአብዛኛው ሕዝብ ላይ ያለውን ብሶትና ጭንቀት፤ በወጣቱ ላይ የደረሰውን አሳፋሪ የስደት እጣ፤ በፍትህ ላይ ያለውን ተደጋጋሚ (Recurring) ጭነትና አፈና፤ በሃገራችን ላይ የሚታየውንና የሚያንዣበበውን ግልጽ አደጋ ሊበርዘው ወይንም ሊሽፍነው አይችልም።
የመለስን እንደማንኛውም ህያው ከዚህ አለም ማለፍ በሰብእነታቸው አስቦ ማዘን/መቀበል የሰው ፍጥሩ ሁሉ ባህርይ ነው። ሆድ የባሰውም ያለቅሳል። እያዘኑ ያለፈውንና የሚመጣውን ማሰብ አስተዋይነት ነው። ከሚያጠያይቁት ነገሮች አንዱ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ የመለስን “አስከሬን ለምን” ትእይንት አስመሰለው፤ አቀረቡት፤ ሌሎች እንደሚሉት፤ ለምን “አስከሬኑን መነገጃ አስመሰሉት? ለአሁኑና ለተከታታይ ትውልድ ምን መልእክት ለማስተላለፍ ተብሎ ነው? ህወሓት/ኢህአዴግ የቀናት አገር አቀፍ ለቅሶ “ሲያውጅ” የሚያስተላልፈው የአገዛዝ መልክት ስላለው ነውን? ይህ ከሆነ፤ መልእክቱ ምንድን ነው? ለነዚህም ከማውጣት ከማውረድ በላይ መልስ የለኝም። አልፏል። ሆኖም፤ ስብሰቡ፤ “ትእይንቱ” አያስገርምም ብለን ልናልፍ እንችላለን። አንዳዶች እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ ሰሜን ኮሪያን ሁናለች ብለን እንለፈው። ለመለስ ማለፍ ለምን የዚህን ያህል ለቅሶ አስፈለገ ብለን እንለፈው። በደርግም ጊዜ ሰው ተገዶ ተሰልፏል። ንግግሩ፤ ውይይቱ፤ የውጭ መንግስታት ፕሬዝደንቶችና ተወካዮች ለልቅሶው ለምን መጡ፤ መለስን ለምን አሞገሱ፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ፤ ኢትዮጵያዊያን በዘር፤ በሃይማኖት፤ በጾታ፤ በእድሜ፤ በገቢ፤ በኑሮ ሳይገቱ ለምን አለቀሱ፤ በልቅሶው ወቅት ለምን ሕዝቡ የእምቢተኛነት ስሜት አላሰማም፤ የሚለው አይደለም። የዚህ አይነት አስተያየት የትም አያደርሰንም።
በግል ሳየው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነቱን ደጋግሞ አስምሮበታል፤ እንኳን ለሃያ አመታት አምባገነን ሁኖ የገዛ፤ ለተራ ሰው ያለቅሳል፤ ያዝናል። አንዱም መለያችን ይህ ነው። አብረን ለማልቀስ ከቻልን፤ አብረን የሃገራችን ተጠቃሚወች መሆን መብታችን ነው። ሕዝቡ፤ ኢትዮጵያዊነቱን፤ ሰብእነቱን፤ አስመስክሯል። ሁኔታው ቢፈቅድለት ኖሮ፤ አጼ ሃይለስላሴ ሲያርፉ፤ አገር አቀፍና አለም አቀፍ በሆነ መልኩ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ባለቀሰ ነበር። የሚያሳፍረው፤ የደርግ መንግስት፤ በጊዜአቸው የሚያኮራ ስራ የሰሩትን፤ በአፍሪካና በአለም ከመለስ ዜናዊ በላይ ለሃገራችን እውቅና ከፍ ያለ አስተዋጾ ያደረጉትን መሪ፤ በድብቅ እንዲቀበሩ አደረገ፤ ክብራቸውን በመግፈፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ ክብር ገፈፈ። በዚያ ጊዜ የነበሩ እንደሚያስታውሱት፤ በብዙ ሽህ የሚቆጥሩ ኢትዮጵያዊያን በእየቤታቸው አልቅሰዋል። ከዚያ ወዲህ፤ ሁኔታወች አስደናቂ በሆነ መልክ ተለውጠዋል። ከግማሽ በላይ (More than 50 percent of the Ethiopian population of 94 million today) የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው አንድ መሪ ነው፤ መለስ ዜናዊን።
ከንግስት ዘውዲቱ በኋላ፤ (መቶ አመት ሊጠጋ ነው)፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጤና ምክንያት ከዚህ አለም ያለፈ መሪ ሲቀብር የመጀመሪያው መለስ ናቸው። ከሃዘኑ ባሻገር ልብ ብለን ማየት ያለብን፤ መለስ የተለቀሰላቸውና የተቀበሩት እንደ አንድ ብሄር ተወካይ ወይንም እንደ እንደ ትግራይ ተወላጅ ሳይሆን፤ “እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ መሪ፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ” ሆነው ነው። ይህን ስል፤ለሃያ አመታት የሰሩትን በደል፤ እንርሳ፤ ማለቴ አይደልም፤ ቢያንስ በአራት መጽሃፎች ላይ እርሳቸው የመሩት መግንስት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰውን በደል በማስረጃ አቅርቤዋለሁ፤ ሁለቱን መጽሃፎቸን እራሳቸው እንዳነበቡና “እንደተቹብኝ” ተነግሮኛል። ከደጋፊወቻቸው ጋር በይፋ ተከራክሪያለሁ።
ከጠባብ ብሄርተኛነት ወደ ኢትዮጵያዊነት፤
ለተመልካቾች እንቆቅልሽ የሆነው፤ የመለስ ኢትዮጵያዊነት እውቅና ያገኘው ከዚህ አለም ሲሞቱ መሆኑ፤ ነው። አንዱ የምንማረው ትምህርት፤ መለስ በኢትዪጵያዊነታቸው ከኢትዮጵያ መናገሻ ከተማ፤ ከኢትዮጵያ ዋና መታወቂያ ቤተክርስቲያን ከተቀበሩ (ማለትም፤ በአዲስ አበባ)፤ በናቁትና፤ “ጨርቅ ነው” ባሉት ሰንደቅ አላማ” ከተሸፈኑ፤ ህወሓት የተባለው በጠባብ ብሄርተኝነት የተመሰረተው የፖለቲካ ራእይም አብሮ ተቀበረ ማለት ነው። ጠባብ ዘረኝነት ከተቀበረ እልል ብለን መቀበል አለብን። ሌላም አይነት ዘረኝነት እንዳይደገም መከላከል አለብን። ትግራይ፤ አድዋ ቢቀበሩ ኖሮ፤ የአለምና የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ፤ ይደንቀውና ይበሳጭ ነበር የሚል ትርጉም ይሰጥ ነበር። ከዱሮውም እንቃወም የነበረው፤ በብሄር፤ ክልል በተባለ አስተዳደር መደራጀትን ነበር። ለአንድ ብሄር አድልወ ማድረግን ነበር፤ የራስን ብሄር ቡድን ማበልጸግን ነበር። ኢትዮጵያዊነት እስከሞት ድረስ የሚቆይ ሳይሆን፤ ከልጅነት እሰከሞት አብሮ የሚታይ መግለጫ ነው። ከአሁን በኋላ በብሄር መጠራት፤ በብሄር መደራጀት፤ ለብሄር ማሰብ፤ በብሄር መበልጸግ፤ የማይጠቅመው፤ ትርጉም የማይኖረው ለዚህ ነው። በዘር ልዩነት መነገድ በወገንና በሃገር ላይ በደል ሰርቶ እንደማለፍ ነው። መለስ፤ በህይወት በነበሩበት ወቅት፤ “እኔ በብሄሬ ሳይሆን፤ የምኮራው በኢትዮጱያዊነቴ ነው ቢሉ ኖሮ” ታሪካዊ ስራ ሰሩ ለማለት እችል ነበር። አላደረጉም። ሆኖም፤ የቀብራቸው ስነስርአት የለውጥ/የተሃድሶ ምልክት ነው። ወደፊት የምንፈልጋት ኢትዮጵያ፤ ለሁሉም እድል የምትሰጥ፤ ሁሉም የሚኮራባት፤ ሁሉም በፈቃዱ ችሎታ ያላቸውን መሪወቹን የሚመርጥባት፤ አልቅሶ የሚቀብርባት አንድ፤ ፍትሃዊ ሃገር መሆን ይኖርባታል። ከሆነ፤ ሆይ “ብለን እንመርጣለን፤ ወይ አምላክ ብለን” እንቀብራለን ማለት ነው።ነጻነት ማለት ይህ ነው።
ታዛቢወች ለቅሶውን “በአስከሬን መነገድ፤ ምን ትርጉም አለው” የሚሉት ያለፈውና ያሁኑ ምንም ግንኙነት ስለሌለው ነው። መለስ ለኢትዮጵያ ታሪክ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ንቀት ነበራቸው፤ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ንቀት ነበራቸው፤ ለተቃዋሚው ንቀት ነበራቸው፤ ለጋዜጠኞት ንቀት ነበራቸው፤ ለአስተማሪወች ንቀት ነበራቸው። ለራሳቸው ነገድ አድናቆት ነበራቸው። ሰድበው ለሰዳቬ አስተላልፈውናል፤ ሱዛን ራይስ ስትሰደበን፤ ከመለስ የተማረችውን መነሻ አድርጋ ነው፤ ፈጥራ አይደለም። በተለይ፤ ለተቃዋሚው ክፍል ያላትን ንቀት ነው ያቀረበችው። ከመለስ ባገኘችው ግንዛቬና ድምደማ መሰረት ነው የሚሉ ብዙ ታዛቢወች አሉ። እኔ የማሳስበው፤ ታዝበን ከወቀሳ፤ ወደ ኢትዮጵያዊ ለውጥ ማተኮር አለብን የሚል ነው። አለበለዚያ፤ ሙተውም መለስ እንደተፈለገው ከመቃብራቸው የእኛን አስተሳሰብ ይዳኙታል፤ ይገዙናል። እንደዚህ ከሆነ፤ ሁኔታው የሚያመልክተው የእኛን ደካማነት ነው። ማተኮር ያለብን ለወደፊቷ ኢትዮጵያ፤ ለወደፊቱ ትውልድ ነው። ኢትዮጵያዊያን የሚፈልጉት በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ፤ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን አገልጋይ የሆነ መንግስትና መሪ ነው። መጓዝም ያለብን በዚህ በኢትዮጵያዊነት መንገድ፤ ለመላው ኢትዮጵያዊያን አገልጋይ የሆነ ፍትሃዊ ስርአትን ለመገንባት ነው። ቀላል መንገድ አይደለም። የህወሓት/ኢህአዴግ ብዙ ዘርፍ ያለው አገዛዝ መለስ በማለፋቸው አልተለወጠም። በተለይ፤ የቁጥጥር ተቋማት። ቅድመ ሁኔታወች ተስተካክለው፤ ሁሉን የሚያካትት መንገድ ካልተቀየሰ፤ የአምባገነኑ ስርአት እንዳለ ይቆያል፤ አደጋው በዚያው ልክ ያይላል። አደጋው፤ ለህወሓት/ኢህአዴግም ጭምር ነው። ሰላምን የነሳ በሰላም ለመኖር አይችልም። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ይህን ይረዱታል ብየ እገምታለሁ።
ለዚህ ነው፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ አድናቂወች፤ ለኢትዮጵያ እርጋታ፤ ለመላው ሕዝቧ ሰላም፤ ከርሃብ አለንጋ፤ ከስደት፤ ከበሽታ፤ ከጠለላ ማጣት ወዘተ ነጻ መሆን ካሰቡ፤ የስርአቱን ደካማ ጎን ጭምር ማሳየት ይኖርባቸው የነበረው። ለማሳየትም የዲፕሎማቲክ ፕሮቶኮል ካልፈቀደ፣ አድናቆቱን ለዛ፤ ሚዛናዊና እውነተኛነት በተሞላበት፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ “አላዋቂ” በማያደርግበት መልክ ማቅረብ የነበረባቸው።
ተከታታዩ (ክፍል አስራ ሁለት) የአለም ጋዜጠኞች፤ የመንግስታት መሪወች፤ በተለይ፤ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ በተከታታይ የተካሄደውንና አሁንም የሚካሄደውን ጫና፤ ግፍና አፈና ለምን አላዩትም፤ ተቃዋሚው ክፍልስ ለዚህ ምን ስትራተጅ አውጥቷል የሚለውን ይዳስሳል።

ሽማግሌ ሲሸብት ይጨምታል፣ የእንጨት ሽበትስ? እንግዳ ታደሰ


ሰዕል የአንድ ታጋይ ኢትዮጵያዊ ወንድማችን፡፡
የአቦይ ስብሃትን አማራና ኦርቶዶክስ  የሚል ያልተሞረደ  አነጋገር  በገዛ ተጋሩ ላይ ሳደምጥ ፣እንደ ወራጅ ዉሃ አሳዳሪ ማጣት እያለች የምትዘፍን  አቀንቃኝ  ዜማ ትዝ አለኝ ፡፡ ሽበታቸውsebehat nega one of the founders of TPLF ዉብታቸው ሳይሆን ፣ ሽበታቸው ነውራቸው የሆነባቸውን የንጨት ሽበቶችን በማምሻ እድሜያቸው ላይ ስትመለከቱ ምን ይሰማችኋል ? ባህላዊ እሴቶቻችንና – ሃይማኖታችን በጸያፍ እንዳንናገር የሚያግዱንን ያልተሞረዱ አነጋገሮች እንዳመጣላቸው የሚናገሩ፣ ቂመኛ እና የድፍ ማስወገጃ ቦይ የሆኑትን ፣ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ያደፈ አነጋገርን ፣ ከውሃት አመሰራረት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሳይለወጡ የሚናገሩትን የአቦይን አነጋገር ስትሰሙ ምን ተሰማችሁ?
የአቦይ መንግሥት በቻይናዎች የሚደገፍ መንግሥት በመሆኑ ፣ ምናልባት ከቻይናዎች ጥቅስ ብንጠቅስላቸው ቶሎ ሊረዱት ስለሚችሉ እነሆ ጥቅሱ ፡፡
Harsh words and poor reasoning never settle anything. ችኩል ንግግሮችና ድኩማን ምክንያቶች መፍትሄ የማይሰጡ ስንኩሎች ናቸው ይመጥነው ይሆን ወደ አማርኛ ስንመልሰው?
በህዉሃት ሰፈር ቋንቋውም ተጠፋፍቶ ፣ አነጋገሩም አልተግባብቶ በሆነበት መንደር ፣ የሚባርቁ አነጋገሮች አገራችንን ለገጠማት ችግር አቧራውን አያስተኛም ፡፡ ይልቁንም ነገሮችን ወጥረው ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ይወስዱታል ፡፡ አቦይ ስብሃት አሳዳሪ ያጡ ፣ እንደፈለጋቸው የሚፏልሉ ፥ አገሪቱን ከመሸታ ቤት ሆነው የሚመሩ ሆነው እስከመቼ እንደሚቀጥሉ የታወቀ ነገር የለም ፡፡ አንዳንዶች በአሁኑ ወቅት ‘’ ሲኮምር ነጋ ‘’ ብለው ሸገር ላይ በቅጽል ስም የሚጠሯቸው ስው ሹመትና ስልጣን ምን እንደሆነ ያቶ’ ኃይለማርያም መንግሥት ቶሽ ካላላቸው ፣ እኝህ ሰው በብሄረሰቦች መሃከል የበለጠ መካረር ፈጥረው አገሪቱን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይመሯት ከፍተኛ ስጋት አለኝ፡፡
የአቶ ኃይለማርያምን መመረጥ አስከትሎ፣ ገዛ ተጋሩ በተባለው የትግርኛ ፓልቶክ ላይ፣ ከንግዲህወዲያ ስልጣን ከአማራውና ከኦርቶዶክሱ እጅ ወጥቷል፡፡ እጅግ ደስ! ደስ! ደስ! ይበላችሁ ብለዋል ፡፡ምናልባት አቦይ በዚህ አነጋገራቸው ፣ ወያኔ አገር ከያዘ በኋላ የተወለደውን ትውልድ ሊያወናብዱበት ይችሉ ይሆናል፡፡ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት መነሻው ከየት ነው? ንጉሳችን የነበሩት አጼ ዮሃንስ ይከተሉት የነበረው ኃይማኖት ምን ነበር ? አጼ ዮሃንስ በንግሥናቸው ዘመን ፣ አማርኛን የሥራ ቋንቋቸው እንዲሆን ያስገደዳቸው የትኛው አማራ ነበር? የትግራይ ህዝብ ባብዛኛው እምነቱ የየትኛው ሃይማኖት ተከታይ ነው? ወደ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ስንመጣ ፣ አጼ ኃይለሥላሴ ወላጅ አባታቸው ከየትኛው ነገድ ነበሩ? እናታቸውስ? ኮለኔል መንግስቱስ አባታቸው ከየት ነገድ ነበሩ? አቶ መለሥስ ከየትኛው ነገድ ነበሩ? ብዙ መዘርዘር ይቻላል ፡፡ ይህን ለታሪክ ተመራማሪዎች እንተወው ፡፡
ብሄራዊትግል – የትግራይህዝብነጻአውጭድርጅትየካቲት 1968 መግለጫ ,
ወያኔ ሀርነት ትግራይ በረሃ በነበረበት ወቅት ባወጣው ማንፌስቶው ገጽ 18 ላይ እንዲህ ይላል፡፡ ‘’የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ትግል  ፀረ የአማራ ብሄራዊ ጭቆና፣ ፀረ ኢምፔርያሊዝም እንዲሁም ፀረ ንኡስ ከበርቴ ለውጥ ነው፡፡ ስለዚህ  የአብዮታዊ ትግል ዓላማ ከባላባታዊ ሥራትና ከኢምፔርያሊዝም ነጻ የሆነ የትግራይ ዲሞክሪያሳዊ ሪፓብሊክ ማቋቋም ይሆናል’’፡፡ አራት ነጥብ፡፡
በዚህ ማንፌስቶ ላይ በዝርዝር ብንሄድበት፣ በአብዛኛው የሞላው ጥላቻ ከምኒሊክ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ፣ ጸረ ሸዋዊ የሚል ቃላትን ያጨቀ ጸረ አማራ ቃላቶችን ነው፡፡ አምሀራና ኢምፔርያሊዝም አንድ ናቸው ብሎ ጎረምሳው ስብሃት ነጋ ያኔ የጻፈው ዘረኛ ማንፌስቶ፣ አቦይ ሆነውም  ከነ-ሸበታቸው ወርዷል፡፡
ይህ ሁሉ ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? ከቤተሰብ በተወረሰ የዘረኝነት ውርስ ወይስ ከባንዳ ቤተሰቦች በተወረሰ ቅርስ ? የአቦይን ትውልደ ውርስ በሚያሳይ መልኩ፣ ኮለኔል አሥራት ቦጋለ ዜሮ ! ዜሮ!ምርጫው ዜሮ በምትል አንዲት የታተመችበት ዓመተ ምህረቷን በማትጠቅስ ትንሽ ጥራዝ ውስጥ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ስለአቦይ ጽፈዋል፡፡
የቶ ስብሃት ነጋ አጎት/ የእናቱ ታላቅ ወንድም- ደጃዝማች ተክሉ መሸሻ በኢጣልያን ወረራዘመን በደቡብ ኢትዮጵያ የኢጣልያ ባንዳ ጦር አዛዥ ሆኖ ጣልያን በደቡብ ኢትዮጵያየተሰለፈውን የኢትዮጵያ ጦር በታንክ በመድፍ ከአውሮፕላን በሚወርድ ቦንብና የመርዝ ጭስአጥቅቶ ድል ካደረገ በኋላ የደቡብ ኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የነበሩት ራስ ደስታ ዳምጠውቆስለው ከጦር ሜዳ በማፈግፈግ በጉራጌ አካባቢ መስቃ ከተባለው ሥፍራ ተኝተው በስቃይላይ እያሉ ደጃዝማች ተክሉ እግር በግር ተከታትሎ ቁስለኛውን በመያዝ ከግንድ ጋር አስሮበጭካኔ ደብድቦ ከገደላቸው በኋላ ራሳቸውን ረግጦ በመቆም ፎተግራፍ በመነሳት ለጣልያኑጌታው ግዳይ ያቀረበ ከሃዲ ባንዳ ነበር ፡፡
በሚል በዝችው ጥራዝ ገጽ 31 ላይ የጻፉ ሲሆን ፣ ለዚህም እንደዋቢ ማስረጃ HAILE SELASSIE’S WAR  ከተባለው የ-Anthony Mockler  መጽሃፍ ውስጥ ገጽ 173 ላይ ያገኙትን ታሪክ በማጣቀሻነት ገልጸዋል፡፡ የዚህ መጣጥፍ ጸሃፊ የድርጊቱን ትክክለኝነት ለማረጋገጥ ይህን የአንቶኒ ሞክለር መጽሃፍ ገጽ 173 ላይ ሲያነብ ፣ ድርጊት ፈጻሚው አንድ የትግራይ ደጃዝማች ባንዳ ተክሉ መሸሻ የተባለ ሰው እንደሆነ ሲያረጋግጥ ፣ የጃንሆይ ልጅ የሆኑት የልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለስላሴ ባለቤት ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው ከቆሰሉበት የጦር ሜዳ በመሸሽ በትውልድ መንደራቸው መስቃን ውስጥ ከተደበቁበት ጎጆ ውስጥ ጎትቶ ከግንድ ጋር በማሰር ይህ ሰው እንደገደላቸው አንቶኒ ጽፏል ፡፡ ባንዳው ተክሉ መሸሻ ግን የአቦይ ስብሃት አጎት እንደሆኑ አይጠቅስም ፡፡ ምናልባት የትግራይ ክልል ህዝብ ይህን ታሪክ ሊያረጋጥ ይችል ይሆናል፡፡
አቦይ በተደጋጋሚ በሚያገኙት የመገናኛ ብዙሃን ላይ , ሲጠየቁ ፣ እየሳቁ የዋህ ይመስላሉ፡፡ ግን ቻይናዎች እንደሚሉት – A man may smile and smile, but still be a villain. በጥርሱ እየሳቀ እያለ የሚያስጠነቅቀን ዘፈን የማን ነበር?

Monday, 24 September 2012

ቅኝቱን ያልሳተው አዲሱ ሹመት ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን)

2004 ዓ.ም ሃገራችን ብርቅዬና በሞያቸው አንቱ የተባሉ እንዲሁም ለሃገራቸው ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ እጅግ ውድ ልጆችዋን እንዳጣች ሁሉ በስተመጨረሻው አዲሱ አመት ከመጥባቱ በፊት እንደ መጅገር ተጣብቀው የህዝብና የአገር ደም ሲመጡ፣ ሃብት ንብረትዋን ሲመዘብሩ የነበሩት እስከ እኩይ ምግባራቸው ላይነቁ እስከ ወዲያኛው ማሸለባቸው የታወሳል፡፡ በማለቂያው እነዚህን እኩይዎች ነቀለልን እንጂ በመለስና በሰርዓቱ ሃገርና ህዝብ ሲታመሱ ነው  አሮጌው ዘመን ያለቀው፡፡ ዘመኑን ሙሉ እሱና ጀሌዎቹ ያረቀቁትን የአገሪቱን ህገ-መንግስት  አክብሮ ማስከበር እርም ሆኖባቸው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን  ተጠቅመው የተደራጁ የድርጅት አመራሮችን እንዲሁም የመፃፍና የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ስለዴሞክራሲ፣ ስለፍትህ፣ ስለመልካም አስተዳደር እጦት የፃፉትንና ሌሎችንም ንፁሃን ዜጎች ሰብስቦ የተለመድው ማጎሪያ የወረወራቸው ዘረኛው መለስ ጀምሮ ባልጨረሰው 2004 ዓ.ም መጀመሪያ ነበር፡፡ ይህ አመት በኢትዮጲያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በርከት ያሉ ትህይንቶች የተስተናግዱብተ አመት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ’’ከሁሉም በፊት ነፃነትና ዴሞክራሲ ለዜጎች መልካም አስተዳደር፣ ፍትህና እኩልነት በሃገሪቱ ይስፈን፣ ህዝብ በተለይ ወጣቱ የአባቶቹን አደራ ይጠብቅ እያለ በመጨረሻም በቃኝ ፍትህ፣ እኩልነትና ነፃነት በሌለበት ሃገር አልኖርም ’’ ብሎ በራሱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን ያቃጠለው ሰመዓቱ የኔሰው ገብሬ በመለስ እና በጭፍሮቹ እንደ አእምሮ በሽተኛ የተቆጠረው በዚሁ በሸኘነው አመት ወርሀ ህዳር ነበር፡፡ ሌላው በዚህ ጉደኛ አመት ከተደረጉ ህዝባዊ እንቅሰቃሴዎች ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ያነሱት የደሞዝ ጭማሪና ተዛማጅ ጥያቄ በአትሌት ሃይሌና በአምባገነኑ መለስ በጥቂት ተፈርጆ ቢፌዝበትም የአንድ ስሞን አንኳር የሃገሪቱ መነጋግሪያ ጉዳይ ሆኖ አልፏል፡፡ ሌላው ምንም እንኳን በአፋኙ ስርዓት መልስ ባያገኝም የአምባገነኑን መንደር አስጨንቆና ፋታ ነስቶ እስካሁን ሲንከባለል ዘመን የተሻገረው የሙሰሊሙ ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ ለሟቹ ዘረኛው መለስም ሆነ ለቀሩት የስርዓቱ ጭፍሮች ትልቅ እራስ ምታት እንደሆነ እስካሁን ዘልቋል፡፡ በዚህም የሙስሊም ማህበረሰብ ባነሳው የመብት ጥያቄ ምክንያት ብዙ ወገኖቻችን በግፈኛው የመለስ ብድን በግፍ ተገለዋል፣ አካላቸውን አጠተዋል፣ ታሰረዋል፡፡ ከወራት በፊት በአርሲ አሳሳ የተካሄደው ጭፍጨፋ ፣ በደሴ የተደረገው የግፍ ብትር ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ በዘመኑ መጨረሻ እንደ አበደ ውሻ ሁሉንም ይነክስ የነበረው መለስ ዜናዊ መጀመሪያ በጀግናው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከዛም በመለአከ ሞት እስከተሸነፈ ጊዜ ደረስ የሚይዝ የሚጨብጠው እስኪያጣ እጅግ በገዘፈ መልኩ የአውሬነት ባህሪ ይስተዋልበት ነበር፡፡ ለዚህም ነው ለዘመናት ተከብሮ የኖረውን የዋልድባ ታሪካዊ ገዳም በልማት ስም እንዲታረስና አለም በቃን ብለው የመነኑ መነኮሳትመጠጊያና መሸሸጊያ እስኪያጡ የሳደዳቸው፡፡ በመሰረቱ ይህ ገዳም የሁሉም ኢትዮጲያዊያን፣ የጳጳሳት፣ የመምህራን፣ የመነኮሳት፣ የዘማሪያን መሰረት ከመሆኑም ባሻገር የሃይማኖት መገለጫ፣ በማንነታችን መኩሪያና ማሳያ፣ የታሪካችን አሻራ ከመሆኑም ባሻገር የተለያዩ የቅዱሳን ገድል ያለባቸው በርካታ መፅሃፍትንና የተለያዩ የኢትዮጲያ ሃገራችን ቅርሶች ያሉበት ገዳም ፣ ከተውልድ ትውልድ ሲወራረስ የመጣውንና የበቁ አባቶች ፀሎትና ምልጃ የማይለየውን ይህንን ቅዱስ ቦታ በልማት ስም የተተናኮለው በመጨረሻው የጣር ሰአቱ ነበር፡፡

ቅኝቱን ያልሳተው አዲሱ ሹመት ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን) 21/09/2012
በተጨማሪም በዚሁ ባሳለፈነው አመት በደቡብ ኢትዮጲያ በጉራ ፈርዳ ለአመታት የኖሩ የአማራ ተወላጆች ከነቤተሰቦቻቸው በሃገራቸው የመኖር መብታቸው ተቀምተው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው ሃብት ንብረታቸውን ተነጥቀው እንደ ዘበት ’’አገራችሁ ሂዱ’’የተባሉት የዴሞክራሲ እና የፍትህ አባት እየተባለ የሚዘመርለት መለስ ዜናዊ አውቆ እና ፈቅዶ ነው ፡፡ ይህም ያሳለፍነው አመት አንድ ትእይንት ሆኖ አልፏል ፡፡ በሌላም በኩል መለስና ግብራበሮቹ በቃኝን የማያውቁ በመሆናቸው የሃገርና የህዝብን ሃብት እንደ ግል ንብረታቸው ከመቀራመትም ባለፈ ደሃ በመሆናችን በኛው ስም ለምነው ካገኙት ገንዝብ ላይ ሁሉ ይስረቃሉ፡፡ የዓለም የፋይናንስ ኢቴግሪቲ (Global financial integrity) ባደረገው ጥናት መሰረት እንደ እ.አ.አ ከ2000 እስከ 2009 ባለው 9 አመታት ውስጥ 11.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጲያ በህገወጥ መንገድ ተዘርፎ ከሃገር መውጣቱን ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ይህ ገንዘብ በኢትዮጲያ ሲመታ ምን ያህል ነው? ምንስ ሊሰራ ይችል ነበር በላችሁ በማሰብ አትታመሙ፡፡ በአጠቃላይ ወያኔ ላለፉት ሃያ አንድ አመታት ሰራሁ የሚለንን መንገድ፣ አነፅኩ የሚለንን ህንፃ ፣ ገነባሁ የሚላቸውን ማንኛውንም ግንባታዎች ከሶስት እጥፍ በላይ ሊከውን የሚችል ገንዘብ በሟቹ መለስና በዙሪያው ባሉ የወያኔ ሰወች እንደተመዘበረ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ከላይ ለመጠቆም የሞከረኩት ሁሉ ለአንድ ሚሊዮን ጊዜ በተለያዩ ሁኔታዎች የተነገሩና ሁሉም ስው የሚያቀው እውነታ ነው፡፡ ታዲያ እነኚህንና የተቀሩትን የዘረኛው መለስ ገድሎች ከሞተም በሗላ ሲሰርቅ አብረው በሰረቁት፣ ሲገድል ተማክረው በገደሉት፣ ፍትህ ሲያጎድል እና ንፁሃን ዜጎችን በግፍ፣ በሃይል ሲረግጥ ብርጭቆ እያጋጩ ደስታቸውን በገለፁ፣ የሴራው ተባባሪ በሆኑት ሁሉ ወይም በእሱ ብልሹ አሰራር ተለጣፊ ሆነው ኑሮአቸውን ያደራጁ፣ የመለስን ጩኸት ሲያስተጋቡ የነበሩ በቀቀኖች ጌታቸውን የሚያንቆለጳጰሱበት ቃላት አጥሮአቸው ተቸግረዋል፡፡ስንት ንፁሃን ዜጎች በየእስር ቤቱ ያጎረውን ሰውዬ…. የፍትህ እና የዴሞክራሲ ተሟጋች፣ ሃገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ የሸጠ እና እጅ መንሻ የሰጠውን…. ባለ ህራህይ፣ ለሃገር አሳቢ አርገው ሲስሉት እጀጉን የደንቃል፡፡ መለሰ የፍትህ እና የዴሞክራሲ አባት ከሆነ አሁን በሚነገርለት መጠን የዜጎችን መብት ያከበረና ያስከበረ ከነበረ የሽብሬ እና የነበዩ መገደል ትክክል ነበር ማለት ነው?፣ እስክንድር እና አንዱአለም እንዲሁም ሌሎች ንፁሃን ዜጎች በእስር መማቀቃቸውስ አግባብ ነው? መቼም ይህንን ለማወቅ ጠቢብ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ በመሰረቱ በአለም ላይ ከብዙሃኑ በተሻለ አስተሳሰብ ያለው ሰው ለመሆን ሁለት አማራጮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው እና ከባዱ የተሻለ ከሚያሰቡ ሰወች የተሻለ ሆኖ መገኘት ሲሆን ሁለተኛው እና በጣም ቀላሉ ደግሞ ደደቦችን በዙሪያህ በመሰብሰብ የተሻለ ሆኖ መታየት ነው፡፡ እናም በኔ አመለካከት ሟች መለስ ሁለተኛውን አማራጭ ተክኖበታል ለዚህ ነው ያልፈጠረበትን ያልሰራውን ገድል እየተረኩ በማህበር ተደራጅተው በደቦ አልቅሰው ሲያላቅሱ የከረሙት፡፡ ለዚህ ነው ሃገር ምድሩን ማቅ አሰለብሰው የለቅሶ ከተት አወጁት፡፡የመለስን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ የግፍና የአፈና ስርዓትን የሚያወድስ ወይም አርአያ አድርጎ የሚከተል ቅኝቱን ያልሳተ አዲሱ ሹመት የተሻለ ነገር ይዞ ይመጣል ማለት ከንቱ ቅዠት ነው፡፡ መለሰ በዘረጋው የዘረኝነትና የጥላቻ ሀዲድ ሊዘውሩን እንሆ አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝ ነግሰውብናል፡፡ በቃን ካላልን አሁንም ሊገዙን ሽርጉድ የሚሉት ያው የሟቹ መለስ ቅጥቅጦች ናቸው፡ ጉልቻ ቢለወጥ ነው ነገሩ . . . . . . . . . ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ ሞት ለወያኔ ለአሰተያየቶ፣-ftih_lewegen@yahoo.com

Sunday, 23 September 2012

የሞቱት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ቢሆኑስ ኖሮ? በሕግ አምላክ (ከስዊድን)

አቶ መለስ ዜናዊ Meles Zenawiሰው ሆኖ መኖር፣ ኖሮ - ኖሮ መሞት አይቀርም። ቢሆንም ገና በህይወት ያለ ሰውን ቢሞት ኖሮስ ብሎ የቀብር ስነሥርዓቱን መግለጽ በባህላችን አልተለመደም። ስለዚህም በርዕስ ምርጫዬ ኮሎኔል መንግሥቱ ቤተሰቦቻውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው እንደማይቀየሙኝ ተስፋ አደርጋለሁ። በርካታ ሰዎች በምስል አቅርቦትና በድምፅ ቀርፃ ያዩትንና የሰሙትን አስመልክቶ የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነሥርዓት እፁብ ድንቅና ወደርየለሽ ነው ይላሉ። እኔ ግን ወደርየለሽ የሚለውን አባባል አልጋራቸውም። ምክንያቱም ...

ሰው ሆኖ መኖር፣ ኖሮ - ኖሮ መሞት አይቀርም። ቢሆንም ገና በህይወት ያለ ሰውን ቢሞት ኖሮስ ብሎ የቀብር ስነሥርዓቱን መግለጽ በባህላችን አልተለመደም። ስለዚህም በርዕስ ምርጫዬ ኮሎኔል መንግሥቱ ቤተሰቦቻውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው እንደማይቀየሙኝ ተስፋ አደርጋለሁ። በርካታ ሰዎች በምስል አቅርቦትና በድምፅ ቀርፃ ያዩትንና የሰሙትን አስመልክቶ የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነሥርዓት እፁብ ድንቅና ወደርየለሽ ነው ይላሉ። እኔ ግን ወደርየለሽ የሚለውን አባባል አልጋራቸውም። ምክንያቱም ...

ምክንያቱም የአቶ መለስ የቀብር አሸኛኘትና አፈጻጸም ወደር የማይገኝለት ነው ሊባል የሚችለው ከየትኛው መሪ የቀብር ስነሥርዓት ጋር ተወዳድሮ ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳ አባባሉን ኢተዓማኒ ያደርገዋልና። ለዚህም ነው የሞቱት ኮሎኔል መንግሥቱ ቢሆኑ ኖሮስ ምን ዓይነት ትዕይንተ ሕዝብ ይታይ ነበር? የሚለውን ግምታዊ አስተሳሰብ በዓይነ ህሊና ለማሳየት የምሞክረው።

በቅድሚያ ግን የአቶ መለስ ዜናዊ እልፈተ ህይወትን ምክንያት በማድረግ ወያኔ (ኢህአዲግ) ለዓለም ሕዝብ ሊያሳይ የፈለገው ትዕይንተ ሕዝብ አሁንም የሕዝብ ንቀትን አመላካች ክንውን መሆኑን ማስመር እፈልጋለሁ። ህወሓትና አጫፋሪዎቹ አባቱን በድንገት እንዳጣ ህጻን ልጅ ”አባቴ! አባቴ!” ብለው እያለቀሱ የሸኙትን ያህል በውስጣዊ ሳቅ የተሰናበቱትም ያንኑ ያህል በርካቶች ናቸው። በለቅሶም በሳቅም ያልኩበት ምክንያት አለኝ። ሁሉንም ነገር አንተ እንዳልክ፣ ካንተ ወዲያ ለኢትዮጵያ፣ ካንተ ወዲያ ለእኩልነትና ለነፃነት ተሟጋች፣ የለም እያሉ በጨለምተኝነት ”አምላኪ መለስ” የነበሩት ቀቢፀ ተስፈኞች አዎ በእጅጉ አዝነዋል። እናም ከልብ አልቅሰው ተሰናብተዋል።

አንድነት፣ እኩልነት፣ ነፃ ምርጫ፣ ... ወዘተ የሚባለውን ስንክሳር ተዉትና በማናቸውም ሲስተም ገብታችሁ መዝረፍ ትችላላችሁ ተብለው አንድ ሺህ ብር ቆጥረው የማያውቁት ቢልዮን ብር በባንክ፣ ሚልዮን የኪስ ገንዘብ የያዙት አግበስባሾችም በእጅጉ አዝነዋል፣ እናም በደንብና በሥርዓት አልቅሰዋል። እነዚህኞቹ ዕንባ አይደለም ቢቻል ደምም ቢያለቅሱ አይወጣላቸውም። ስለዚህም ምርር፣ ስቅስቅ ብለው አልቅሰዋል። ከትግሬ መወለድ ልዩ ፍጥረትና ልዩ ክብር እንዳለው በአደባባይ ላይ በትዕቢትና በትምክኽተኛነት በመነገሩ የትናንቱን ኑሯቸውን ምንም ባይለውጠውም በትግሬነታቸው ብቻ ዘራፍ ሲሉ የነበሩትም ከሌሎች እኩል አልቅሰው ቀብረዋል። እነዚህኞቹ ደግሞ ምንም አላገኙ፤ ምንም አላጡ፣ ነገር ግን መለስ በመሞታቸው ሁሉም ጣቱን የሚቀስርባቸው እየመሰላቸው በሥነልቡና ፍርሃት ተሸማቀው በዕንባ ሲራጩ ተስተውለዋል። በአንፃሩም መሬቱ ይቅለላቸውና አቶ መለስ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ ግማሽ ልባቸው ወደ ኤርትራ፣ ግማሽ ልባቸው ወደ ትግራይ፣ የሥልጣን ልባቸው ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ተከፋፍሎ ሚዛናዊ ዳኝነታቸው ተዛብቶባቸዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያዊነት ደብዛን ለማጥፋት በፈፀሙት ብሔራዊ ስህተቶች አንጀቱ ሲቃጠል የነበረው፤ ነገር ግን ውጣና ቅበር የተባለው ህዝብም በእውን እያለቀሰ ከማለት በውስጡ እየሳቀ ሸኛቸው ቢባል ከእውነታው የራቀ አይሆንም። ምክንያቱም ሰው እንዲያለቅስም እንዲስቅም የሚያነሳሳው ኑሮው ነውና።

በሌላ መልኩ የአቶ መለስ ተለዋዋጭ ባህሪም ከአንድ መንግሥትና ፓርቲ መሪነት ወደ ሁለንተናነት እየተለወጠ በመምጣቱ ሁሉንም ነገር እርሳቸውና እርሳቸው ብቻ የሚያቅዱና የሚወስኑ በመሆናቸው ከአመራር ውጪ ሆኖ በጀሌነት አብሯቸው የነበረው ባለሥልጣን ሳይቀር ላይ ላዩን በጥቁር ልብስ ተዠብኖ ቢታይም ውስጡ ግን ”አብዝቶት ነበር ይበቃዋል!” በሚል በአዲስ ተስፋ ተሰናብቷቸዋል። ወጣም ወረደ አቶ መለስ ዜናዊ አስከሬናቸው ከቤተ መንግሥት በክብር ወጥቶ በሕዝባዊ አጀብ የተቀበሩ የዘመናችን መሪ በመሆናቸው በዚህ ዕድለኛ ናቸው። በዚህ ምክንያትም ቀብራቸው ዕፁብ ድንቅ በሚባል ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ ተፈጽሟል። ነገር ግን የርሳቸውን ሥርዓተ ቀብር ወደር የማይገኝለት ለማለት ለሌላ መሪ የተደረገውን ወይንም ሊደረግ የሚችለውን ሥርዓት መቃኘት ንፅፅሩን ሚዛናዊ ያደርገዋል። ለዚህም ነው የሞቱት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ቢሆኑስ ኖሮ? ያልኩት። ለመሆኑ እኒህ ሰው በበትረ ሥልጣናቸው ላይ እያሉ ቢሞቱ ኖሮ ደርግ (ኢሠፓ) ምን ምን በማለት አጅቦና አዝኖ ቀብራቸውን ያስፈጽም ነበር?

”ውድ ጓድ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም፣
የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ፣
የኢህዲሪ ፕሬዘዳንትና የአብዮታዊ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣
  • • ሲወርድ ሲዋረድ የቆየውን የኢትዮጵያን አንድነትና ዳር ድንበር አስከብሮ ለማቆየት በየማዕዘኑ ከተነሱ ጠላቶች ጋር የተደረገውን ፍልሚያ የመሩ የጦር መሪያችን፣
  • • በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲፈጠሩና ህዝቡ እንዲነቃ፣ እንዲደራጅና እንዲታጠቅ ያስቻሉ አሻግሮ ተመልካች፣
  • በገባርና በጢሰኛ መካከል ተንሰራፍቶ የነበረውን ኋላ ቀር ግንኙነት በጥሰው መሬት ለአራሹ ያደረጉ የድሃው ገበሬ አባት፣
  • የሶማሊያ ተስፋፊ ጦርነትን “እናት ሀገርህ ተደፍራለች! ተነስ፣ ታጠቅ፣ ዝመት፣ ...” በሚል ብሔራዊ ጥሪ ሕዝባዊ ሠራዊትና መደበኛ ጦር በማዝመት ድል መትተው የሀገር ክብርና ዳር ድንበርን ያስከበሩ የጦር አዝማችና መሪያችን፣
  • የውበት ፈርጣችን የሆኑትና በአንድነትና በፍቅር ተሳስረው የሚኖሩ ልዩ ልዩ ብሔረሰቦች እንዲታወቁ፣ እንዲጠኑና መብታቸውም እንዲከበር የሚያስችል የብሔረሰቦች ኢንስቲትዩትን ያቋቋሙ የእኩልነት በር ከፋች፣
  • በሕዝብ የመኖሪያ አቅራቢያዎች የመሠረታዊ ሸቀጦች ማከፋፈያንና የፍትሕ አካላትን (ፍርድ ሸንጎ) አቋቁመው የነጋዴ ብዝበዛንና የፍርድ ቤት ውጣውረድን ያስቆሙ ተቆርቋሪ ዜጋ፣
  • መኃይምነትን በማጥፋት ዘመቻ ዓለም አቀፍ አድናቆትን ያተረፉ አስተማሪያችን፣
  • ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ የመገናኛ አውታሮችንና አስተዳደራዊ ልማቶችን በሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት በአቻነት ያስፋፉ የልማት መሐንዲሳችን፣
  • የኢትዮጵያን ታሪካዊና ዙርያ ክብ ጠላቶች ለመመከት የሚያስችልና ምዕራባውያንን በከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለ የመከላከያ ኃይል የገነቡ የዘመናችን አፄ ቴዎድሮስ፣ … ወዘተ … ወዘተ …"

እየተባለ አሁን አቶ መለስን ለመሰናበትና ለመቅበር በደብዳቤ ጋጋታ ከወጣው የስም እዝንተኛ በእጅጉ የላቀ ትዕይንተ ሕዝብ በታየ ነበር። ለዚህ ነው ወደር የማይገኝለት የቀበር ስነሥርዓት ለማለት ከማን ጋር ተነፃፅሮ በማለት የጠየቅሁት።

አቶ መለስ ዜናዊ እንደማናቸውም ሰው በአንድ የታሪክ አጋጣሚ የሀገር መሪነት ሥልጣን ጨብጠዋል። እንደማንኛውም መሪም ጠንካራና ደካማ ጎኖች ታይተውባቸዋል። በመሪነት ዘመናቸው አፍላ ምዕራፍ ላይ በመደራጀት መብት፣ በነፃ ፕሬስ፣ በነፃ መሰብሰብና በመሳሰሉት በተለይም በ1997 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2005) ቅድመ ምርጫ ወቅት ተስፋ ሰጭና በጎ ጅምሮች ቢታዩም ውለው አድረው ብሔራዊ ኃላፊነት በጎደለው ትዕቢት የፈፀሟቸው የታሪክ ጠባሳዎች እጅግ በርካቶች ናቸው። እናም እንደዚህ ማለት ይቻላል፣

አቶ መለስ ዜናዊ፣
የኢፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣
የኢህዲግ ሊቀመንበርና የጦሩ የበላይ አዛዥ፣
  • የቆየውን የኢትዮጵያውያን አብሮነትና ብሔራዊ ስሜት በጎሣ ፖለቲካ ተክተው በተጋድሎ አንድነቷ ተጠብቆ የቆየችው ሀገር እንድትበጣጠስና ለእርስ በርስ ጦርነትም እንድትመቻች፣ የመከፋፈልና የመፈራረስ የመሰረት ድንጋይ የሆነውን ሕገ መንግሥት አውጥተው ያፀደቁ ናቸው።
  • የኢትዮጵያን የባህር ወደብ ለሻዕቢያ እጅ መንሻ ከመስጠት አልፎ መጠነ ሰፊ የሀገሪቱ አካል ተቆርሶ ለኤርትራ እንዲሰጥ በጥፋት የስምምነት ፊርማቸው ያጸደቁ መሪ ናቸው።
  • በህይወት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለሱዳን ምንደኞች በመስጠት የክልሉን ገብሬ ያፈናቀሉና ብሔራዊ ክብር ያሳጡ ግድየለሽ ናቸው።
  • ትጥቅ አልባ ተቃዋሚ ሠልፈኞችን በቅልብ ጦራቸው ያስረሸኑና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ተለጣፊ ስም በመስጠት በእስር እንዲሰቃዩ አመራር የሰጡ የሰብዓዊ መብት ረጋጭ አምባገነን ናቸው።
  • ዛሬ በሚታየው የሰለጠነ ፖለቲካ ሥርዓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያላቸውን አማራጭ ለህዝብ አቅርቦ በማስወሰን ፈንታ የተቃዋሚዎችን ጽ/ቤት በመዝጋት፣ መሪዎችን በመግደልና በማሰር የሕዝብ ድምጽን በገሀድ በመዝረፍ ሥልጣንን በብቸኝነት ይዘው ዲሞክራሲን ያፈኑ የስም መሪ ናቸው።
  • ለውጤት የማይነሳሳ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያደርግ የትምህርት ፖሊሲ በማውጣትና የሥራ ዕድል ባለመፍጠር ተስፋ የቆረጠና ችግር መፍታት የማይችል ትውልድ እንዲበራከት ያደረጉ ምሁር አምካኝ መሪ ናቸው።
  • ለዘመናት የብዙኀን ተቆርቋሪ ዜጎች ጥያቄ የነበረው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ተቀልብሶ የገጠር መሬት ለህወሓት/ኢህአዲግ የፖለቲካ መሣሪያነት እንዲውል ለማድረግ በመንግሥት ቁጥጥር ስር አውለው ገበሬውን ማዕከል አድርገናል በሚሉት ፍልስፍና የኢትዮጵያ ገበሬን የመሬት ባለቤትነት ያሳጡና ኑሮውን እያፈናቀሉ ለድንበር ዘለል ከበርቴዎች የሸጡት ናቸው።
  • በኦሮሞ፣ በኦጋዴን፣ በጋምቤላና በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች በተወርዋሪ ጦራቸው በአንድ ብሔረሰብ አባላት ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ያካሄዱና በዘር ማጥፋት ወንጀል መጠየቅ የነበረባቸው ወንጀለኛ ናቸው።

አቶ መለስ ዜናዊ እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ እጅግ በርካታ ብሔራዊ ጥፋቶች ፈጽመው አልፈዋል። መሬት ይቅለላቸው እንጂ በፌደራልና በክልል ሥልጣን ስም፣ በዲሞክራሲና በነፃ ምርጫ ስም፣ በነፃ ፕሬስና በብዙኀን ፓርቲ ስም በአጠቃላይ በማይተገበር ሕገ መንግሥት ስም ጥቂቶች ብዙኀኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር ከፋፍለው ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አፍነው የዲሞክራሲያዊ ግንባታውን ቀልብሰውታል።

አገራዊ - አገራዊ፣ ብሔራዊ - ብሔራዊ የሚሸተው የአብሮነት መዓዛ ተበርዞና ጠፍቶ ክልላዊ - ክልላዊ እንዲሸትና በአንድ ሀገር ሕዝቦች መካከል የነበረውን የአብሮነት ታሪክና ባህል በጎሣ ፖለቲካ መርዘውታል።

አቶ መለስ ዜናዊ ታላቅ ክብርና ሞገስ ያለው የኢትዮጵያዊነት ካባ አልሻም ብለው በትግሬነት ሰደርያቸው የተመፃደቁና ራሳቸውን ከብሔራዊ ክብር ወደ መንደር ያወረዱ፣ ቂም በቀል ከደም ሥራቸው ጋር የተሳሰረ፣ ጥላቻ፣ ፍርሃትና ተጠራጣሪነት ተደራርበው ዕረፍት ስላሳጧቸው ለዕልፈት በቅተዋል።

የሞተን አልቅሶ ወይም ሸኝቶ መቅበር ቀጣይ ነባራዊ ክንውን ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ከማንም በላቀ ምንም ያስከፋንና የበደለን ቢሆንም ሰው ከሞተ በኋላ ክብር እንሰጠዋለን። ይህም በጎ ባህል ነው!

የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ፋይዳም ይኸው የባህል ጉዳይ ነው። በዚህ ላይ ይፋዊ የሆነ የውጡና ቅበሩ ትዕዛዝም በነቂስ ተሰራጭቷል። ሰው ናቸው ኖረዋል፣ ሰው ናቸው ሞተዋል፣ ሰው ናቸው ሲሞቱ ተቀብረዋል፣ ሌላ ታሪክ የላቸውም። ታሪክን የሚሠራ ሕዝብ እንጂ ግለሰቦች አይደሉም። እናም የወደቀው የሀገራችንና የአንድነታችንን ታሪክ ለማቅናትና መልሶ ለመገንባት ተቃዋሚውም ሆነ ገዥው ፓርቲ በአብሮነት በጋራ ለመሥራት ግዜው የግድ ይላል።
ምክንያቱም የአቶ መለስ የቀብር አሸኛኘትና አፈጻጸም ወደር የማይገኝለት ነው ሊባል የሚችለው ከየትኛው መሪ የቀብር ስነሥርዓት ጋር ተወዳድሮ ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳ አባባሉን ኢተዓማኒ ያደርገዋልና። ለዚህም ነው የሞቱት ኮሎኔል መንግሥቱ ቢሆኑ ኖሮስ ምን ዓይነት ትዕይንተ ሕዝብ ይታይ ነበር? የሚለውን ግምታዊ አስተሳሰብ በዓይነ ህሊና ለማሳየት የምሞክረው።

በቅድሚያ ግን የአቶ መለስ ዜናዊ እልፈተ ህይወትን ምክንያት በማድረግ ወያኔ (ኢህአዲግ) ለዓለም ሕዝብ ሊያሳይ የፈለገው ትዕይንተ ሕዝብ አሁንም የሕዝብ ንቀትን አመላካች ክንውን መሆኑን ማስመር እፈልጋለሁ። ህወሓትና አጫፋሪዎቹ አባቱን በድንገት እንዳጣ ህጻን ልጅ ”አባቴ! አባቴ!” ብለው እያለቀሱ የሸኙትን ያህል በውስጣዊ ሳቅ የተሰናበቱትም ያንኑ ያህል በርካቶች ናቸው። በለቅሶም በሳቅም ያልኩበት ምክንያት አለኝ። ሁሉንም ነገር አንተ እንዳልክ፣ ካንተ ወዲያ ለኢትዮጵያ፣ ካንተ ወዲያ ለእኩልነትና ለነፃነት ተሟጋች፣ የለም እያሉ በጨለምተኝነት ”አምላኪ መለስ” የነበሩት ቀቢፀ ተስፈኞች አዎ በእጅጉ አዝነዋል። እናም ከልብ አልቅሰው ተሰናብተዋል።

አንድነት፣ እኩልነት፣ ነፃ ምርጫ፣ ... ወዘተ የሚባለውን ስንክሳር ተዉትና በማናቸውም ሲስተም ገብታችሁ መዝረፍ ትችላላችሁ ተብለው አንድ ሺህ ብር ቆጥረው የማያውቁት ቢልዮን ብር በባንክ፣ ሚልዮን የኪስ ገንዘብ የያዙት አግበስባሾችም በእጅጉ አዝነዋል፣ እናም በደንብና በሥርዓት አልቅሰዋል። እነዚህኞቹ ዕንባ አይደለም ቢቻል ደምም ቢያለቅሱ አይወጣላቸውም። ስለዚህም ምርር፣ ስቅስቅ ብለው አልቅሰዋል። ከትግሬ መወለድ ልዩ ፍጥረትና ልዩ ክብር እንዳለው በአደባባይ ላይ በትዕቢትና በትምክኽተኛነት በመነገሩ የትናንቱን ኑሯቸውን ምንም ባይለውጠውም በትግሬነታቸው ብቻ ዘራፍ ሲሉ የነበሩትም ከሌሎች እኩል አልቅሰው ቀብረዋል። እነዚህኞቹ ደግሞ ምንም አላገኙ፤ ምንም አላጡ፣ ነገር ግን መለስ በመሞታቸው ሁሉም ጣቱን የሚቀስርባቸው እየመሰላቸው በሥነልቡና ፍርሃት ተሸማቀው በዕንባ ሲራጩ ተስተውለዋል። በአንፃሩም መሬቱ ይቅለላቸውና አቶ መለስ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ ግማሽ ልባቸው ወደ ኤርትራ፣ ግማሽ ልባቸው ወደ ትግራይ፣ የሥልጣን ልባቸው ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ተከፋፍሎ ሚዛናዊ ዳኝነታቸው ተዛብቶባቸዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያዊነት ደብዛን ለማጥፋት በፈፀሙት ብሔራዊ ስህተቶች አንጀቱ ሲቃጠል የነበረው፤ ነገር ግን ውጣና ቅበር የተባለው ህዝብም በእውን እያለቀሰ ከማለት በውስጡ እየሳቀ ሸኛቸው ቢባል ከእውነታው የራቀ አይሆንም። ምክንያቱም ሰው እንዲያለቅስም እንዲስቅም የሚያነሳሳው ኑሮው ነውና።

በሌላ መልኩ የአቶ መለስ ተለዋዋጭ ባህሪም ከአንድ መንግሥትና ፓርቲ መሪነት ወደ ሁለንተናነት እየተለወጠ በመምጣቱ ሁሉንም ነገር እርሳቸውና እርሳቸው ብቻ የሚያቅዱና የሚወስኑ በመሆናቸው ከአመራር ውጪ ሆኖ በጀሌነት አብሯቸው የነበረው ባለሥልጣን ሳይቀር ላይ ላዩን በጥቁር ልብስ ተዠብኖ ቢታይም ውስጡ ግን ”አብዝቶት ነበር ይበቃዋል!” በሚል በአዲስ ተስፋ ተሰናብቷቸዋል። ወጣም ወረደ አቶ መለስ ዜናዊ አስከሬናቸው ከቤተ መንግሥት በክብር ወጥቶ በሕዝባዊ አጀብ የተቀበሩ የዘመናችን መሪ በመሆናቸው በዚህ ዕድለኛ ናቸው። በዚህ ምክንያትም ቀብራቸው ዕፁብ ድንቅ በሚባል ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ ተፈጽሟል። ነገር ግን የርሳቸውን ሥርዓተ ቀብር ወደር የማይገኝለት ለማለት ለሌላ መሪ የተደረገውን ወይንም ሊደረግ የሚችለውን ሥርዓት መቃኘት ንፅፅሩን ሚዛናዊ ያደርገዋል። ለዚህም ነው የሞቱት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ቢሆኑስ ኖሮ? ያልኩት። ለመሆኑ እኒህ ሰው በበትረ ሥልጣናቸው ላይ እያሉ ቢሞቱ ኖሮ ደርግ (ኢሠፓ) ምን ምን በማለት አጅቦና አዝኖ ቀብራቸውን ያስፈጽም ነበር?

”ውድ ጓድ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም፣
የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ፣
የኢህዲሪ ፕሬዘዳንትና የአብዮታዊ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣
  • • ሲወርድ ሲዋረድ የቆየውን የኢትዮጵያን አንድነትና ዳር ድንበር አስከብሮ ለማቆየት በየማዕዘኑ ከተነሱ ጠላቶች ጋር የተደረገውን ፍልሚያ የመሩ የጦር መሪያችን፣
  • • በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲፈጠሩና ህዝቡ እንዲነቃ፣ እንዲደራጅና እንዲታጠቅ ያስቻሉ አሻግሮ ተመልካች፣
  • በገባርና በጢሰኛ መካከል ተንሰራፍቶ የነበረውን ኋላ ቀር ግንኙነት በጥሰው መሬት ለአራሹ ያደረጉ የድሃው ገበሬ አባት፣
  • የሶማሊያ ተስፋፊ ጦርነትን “እናት ሀገርህ ተደፍራለች! ተነስ፣ ታጠቅ፣ ዝመት፣ ...” በሚል ብሔራዊ ጥሪ ሕዝባዊ ሠራዊትና መደበኛ ጦር በማዝመት ድል መትተው የሀገር ክብርና ዳር ድንበርን ያስከበሩ የጦር አዝማችና መሪያችን፣
  • የውበት ፈርጣችን የሆኑትና በአንድነትና በፍቅር ተሳስረው የሚኖሩ ልዩ ልዩ ብሔረሰቦች እንዲታወቁ፣ እንዲጠኑና መብታቸውም እንዲከበር የሚያስችል የብሔረሰቦች ኢንስቲትዩትን ያቋቋሙ የእኩልነት በር ከፋች፣
  • በሕዝብ የመኖሪያ አቅራቢያዎች የመሠረታዊ ሸቀጦች ማከፋፈያንና የፍትሕ አካላትን (ፍርድ ሸንጎ) አቋቁመው የነጋዴ ብዝበዛንና የፍርድ ቤት ውጣውረድን ያስቆሙ ተቆርቋሪ ዜጋ፣
  • መኃይምነትን በማጥፋት ዘመቻ ዓለም አቀፍ አድናቆትን ያተረፉ አስተማሪያችን፣
  • ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ የመገናኛ አውታሮችንና አስተዳደራዊ ልማቶችን በሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት በአቻነት ያስፋፉ የልማት መሐንዲሳችን፣
  • የኢትዮጵያን ታሪካዊና ዙርያ ክብ ጠላቶች ለመመከት የሚያስችልና ምዕራባውያንን በከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለ የመከላከያ ኃይል የገነቡ የዘመናችን አፄ ቴዎድሮስ፣ … ወዘተ … ወዘተ …"

እየተባለ አሁን አቶ መለስን ለመሰናበትና ለመቅበር በደብዳቤ ጋጋታ ከወጣው የስም እዝንተኛ በእጅጉ የላቀ ትዕይንተ ሕዝብ በታየ ነበር። ለዚህ ነው ወደር የማይገኝለት የቀበር ስነሥርዓት ለማለት ከማን ጋር ተነፃፅሮ በማለት የጠየቅሁት።

አቶ መለስ ዜናዊ እንደማናቸውም ሰው በአንድ የታሪክ አጋጣሚ የሀገር መሪነት ሥልጣን ጨብጠዋል። እንደማንኛውም መሪም ጠንካራና ደካማ ጎኖች ታይተውባቸዋል። በመሪነት ዘመናቸው አፍላ ምዕራፍ ላይ በመደራጀት መብት፣ በነፃ ፕሬስ፣ በነፃ መሰብሰብና በመሳሰሉት በተለይም በ1997 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2005) ቅድመ ምርጫ ወቅት ተስፋ ሰጭና በጎ ጅምሮች ቢታዩም ውለው አድረው ብሔራዊ ኃላፊነት በጎደለው ትዕቢት የፈፀሟቸው የታሪክ ጠባሳዎች እጅግ በርካቶች ናቸው። እናም እንደዚህ ማለት ይቻላል፣

አቶ መለስ ዜናዊ፣
የኢፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣
የኢህዲግ ሊቀመንበርና የጦሩ የበላይ አዛዥ፣
  • የቆየውን የኢትዮጵያውያን አብሮነትና ብሔራዊ ስሜት በጎሣ ፖለቲካ ተክተው በተጋድሎ አንድነቷ ተጠብቆ የቆየችው ሀገር እንድትበጣጠስና ለእርስ በርስ ጦርነትም እንድትመቻች፣ የመከፋፈልና የመፈራረስ የመሰረት ድንጋይ የሆነውን ሕገ መንግሥት አውጥተው ያፀደቁ ናቸው።
  • የኢትዮጵያን የባህር ወደብ ለሻዕቢያ እጅ መንሻ ከመስጠት አልፎ መጠነ ሰፊ የሀገሪቱ አካል ተቆርሶ ለኤርትራ እንዲሰጥ በጥፋት የስምምነት ፊርማቸው ያጸደቁ መሪ ናቸው።
  • በህይወት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለሱዳን ምንደኞች በመስጠት የክልሉን ገብሬ ያፈናቀሉና ብሔራዊ ክብር ያሳጡ ግድየለሽ ናቸው።
  • ትጥቅ አልባ ተቃዋሚ ሠልፈኞችን በቅልብ ጦራቸው ያስረሸኑና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ተለጣፊ ስም በመስጠት በእስር እንዲሰቃዩ አመራር የሰጡ የሰብዓዊ መብት ረጋጭ አምባገነን ናቸው።
  • ዛሬ በሚታየው የሰለጠነ ፖለቲካ ሥርዓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያላቸውን አማራጭ ለህዝብ አቅርቦ በማስወሰን ፈንታ የተቃዋሚዎችን ጽ/ቤት በመዝጋት፣ መሪዎችን በመግደልና በማሰር የሕዝብ ድምጽን በገሀድ በመዝረፍ ሥልጣንን በብቸኝነት ይዘው ዲሞክራሲን ያፈኑ የስም መሪ ናቸው።
  • ለውጤት የማይነሳሳ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያደርግ የትምህርት ፖሊሲ በማውጣትና የሥራ ዕድል ባለመፍጠር ተስፋ የቆረጠና ችግር መፍታት የማይችል ትውልድ እንዲበራከት ያደረጉ ምሁር አምካኝ መሪ ናቸው።
  • ለዘመናት የብዙኀን ተቆርቋሪ ዜጎች ጥያቄ የነበረው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ተቀልብሶ የገጠር መሬት ለህወሓት/ኢህአዲግ የፖለቲካ መሣሪያነት እንዲውል ለማድረግ በመንግሥት ቁጥጥር ስር አውለው ገበሬውን ማዕከል አድርገናል በሚሉት ፍልስፍና የኢትዮጵያ ገበሬን የመሬት ባለቤትነት ያሳጡና ኑሮውን እያፈናቀሉ ለድንበር ዘለል ከበርቴዎች የሸጡት ናቸው።
  • በኦሮሞ፣ በኦጋዴን፣ በጋምቤላና በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች በተወርዋሪ ጦራቸው በአንድ ብሔረሰብ አባላት ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ያካሄዱና በዘር ማጥፋት ወንጀል መጠየቅ የነበረባቸው ወንጀለኛ ናቸው።

አቶ መለስ ዜናዊ እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ እጅግ በርካታ ብሔራዊ ጥፋቶች ፈጽመው አልፈዋል። መሬት ይቅለላቸው እንጂ በፌደራልና በክልል ሥልጣን ስም፣ በዲሞክራሲና በነፃ ምርጫ ስም፣ በነፃ ፕሬስና በብዙኀን ፓርቲ ስም በአጠቃላይ በማይተገበር ሕገ መንግሥት ስም ጥቂቶች ብዙኀኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር ከፋፍለው ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አፍነው የዲሞክራሲያዊ ግንባታውን ቀልብሰውታል።

አገራዊ - አገራዊ፣ ብሔራዊ - ብሔራዊ የሚሸተው የአብሮነት መዓዛ ተበርዞና ጠፍቶ ክልላዊ - ክልላዊ እንዲሸትና በአንድ ሀገር ሕዝቦች መካከል የነበረውን የአብሮነት ታሪክና ባህል በጎሣ ፖለቲካ መርዘውታል።

አቶ መለስ ዜናዊ ታላቅ ክብርና ሞገስ ያለው የኢትዮጵያዊነት ካባ አልሻም ብለው በትግሬነት ሰደርያቸው የተመፃደቁና ራሳቸውን ከብሔራዊ ክብር ወደ መንደር ያወረዱ፣ ቂም በቀል ከደም ሥራቸው ጋር የተሳሰረ፣ ጥላቻ፣ ፍርሃትና ተጠራጣሪነት ተደራርበው ዕረፍት ስላሳጧቸው ለዕልፈት በቅተዋል።

የሞተን አልቅሶ ወይም ሸኝቶ መቅበር ቀጣይ ነባራዊ ክንውን ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ከማንም በላቀ ምንም ያስከፋንና የበደለን ቢሆንም ሰው ከሞተ በኋላ ክብር እንሰጠዋለን። ይህም በጎ ባህል ነው!

የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ፋይዳም ይኸው የባህል ጉዳይ ነው። በዚህ ላይ ይፋዊ የሆነ የውጡና ቅበሩ ትዕዛዝም በነቂስ ተሰራጭቷል። ሰው ናቸው ኖረዋል፣ ሰው ናቸው ሞተዋል፣ ሰው ናቸው ሲሞቱ ተቀብረዋል፣ ሌላ ታሪክ የላቸውም። ታሪክን የሚሠራ ሕዝብ እንጂ ግለሰቦች አይደሉም። እናም የወደቀው የሀገራችንና የአንድነታችንን ታሪክ ለማቅናትና መልሶ ለመገንባት ተቃዋሚውም ሆነ ገዥው ፓርቲ በአብሮነት በጋራ ለመሥራት ግዜው የግድ ይላል።